የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 1
  • ስለ ሰዎች ማሰብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስለ ሰዎች ማሰብ
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አድርጓል?
  • ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
  • ኢየሱስን ምሰል
  • ተፈጥሯዊ አነጋገር
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችል ውይይት መጀመር
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ከሰዎች ጋር የመወያየት ችሎታህን ማሻሻል
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር​—ከሰዎች ጋር ውይይት በመጀመር መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 1

ውይይት መጀመር

ኢየሱስ በውኃ ጉድጓድ አጠገብ ከአንዲት ሴት ጋር ሲነጋገር።

ዮሐ. 4:6-9

ምዕራፍ 1

ስለ ሰዎች ማሰብ

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ፍቅር . . . የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም።”—1 ቆሮ. 13:4, 5

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

ኢየሱስ በውኃ ጉድጓድ አጠገብ ከአንዲት ሴት ጋር ሲነጋገር።

ቪዲዮ፦ ኢየሱስ እና የውኃ ጉድጓድ አጠገብ ያገኛት ሴት

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ዮሐንስ 4:6-9ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ኢየሱስ ሴትየዋን ከማዋራቱ በፊት ስለ እሷ ምን የታዘበው ነገር አለ?

  2. ለ. ኢየሱስ “እባክሽ፣ የምጠጣው ውኃ ስጪኝ” አላት። ይህን ማለቱ ውይይት ለመጀመር ውጤታማ እንደነበር ይሰማሃል? ለምን?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. የምናነጋግረውን ሰው ትኩረት የሚስብ ነገር ማንሳታችን፣ ጥሩ ውይይት ለማድረግ መንገድ ይከፍታል።

ኢየሱስን ምሰል

3. እንደሁኔታው ሁን። የግድ እኔ በተዘጋጀሁበት ርዕሰ ጉዳይ ካልተወያየሁ አትበል። በወቅቱ ሰዎች የሚያሳስባቸውን ጉዳይ አንስተህ ውይይት ጀምር። ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  1. ሀ. ‘ዜና ላይ ምን እየተባለ ነው?’

  2. ለ. ‘ጎረቤቶቼ፣ የሥራ ባልደረቦቼ ወይም አብረውኝ የሚማሩት ልጆች እያወሩበት ያለው ሰሞንኛ ጉዳይ ምንድን ነው?’

4. ጥሩ አድርገህ ታዘብ። ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  1. ሀ. ‘ግለሰቡ ምን እያደረገ ነው? ስለ ምን እያሰበ ሊሆን ይችላል?’

  2. ለ. ‘አለባበሱ፣ ውጫዊ ገጽታው ወይም ቤቱ፣ ስለሚያምንበት ነገር ወይም ስለ ባሕሉ ምን የሚጠቁመው ነገር አለ?’

  3. ሐ. ‘ግለሰቡን አሁን ባነጋግረው ይመቸዋል?’

5. አዳምጥ።

  1. ሀ. ብዙ አታውራ።

  2. ለ. ግለሰቡም እንዲናገር ዕድል ስጠው። የሚቻል ከሆነ ጥያቄ ጠይቅ።

ተጨማሪ ጥቅሶች

ማቴ. 7:12፤ 1 ቆሮ. 9:20-23፤ ፊልጵ. 2:4፤ ያዕ. 1:19

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ