የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 8
  • ትዕግሥት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትዕግሥት
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አድርጓል?
  • ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
  • ኢየሱስን ምሰል
  • ትዕግሥት ማሳየታችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ቪዲዮዎችን ተጠቅሞ ማስተማር
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
  • የኢየሱስ ሞት ከሚያስገኛቸው በረከቶች ተጠቀም
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ስለ ሰዎች ማሰብ
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 8

ተመላልሶ መጠየቅ

ኢየሱስ በአናፂ መደብር ውስጥ ወንድሙን ያዕቆብን ሲያገኘው። ያዕቆብ ኢየሱስን በማየቱ ተደንቋል።

ዮሐ. 7:3-5፤ 1 ቆሮ. 15:3, 4, 7

ምዕራፍ 8

ትዕግሥት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “ፍቅር ታጋሽ . . . ነው።”—1 ቆሮ. 13:4

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

ኢየሱስ በአናፂ መደብር ውስጥ ወንድሙን ያዕቆብን ሲያገኘው። ያዕቆብ ኢየሱስን በማየቱ ተደንቋል።

ቪዲዮ፦ ኢየሱስ ወንድሙን በትዕግሥት ረድቶታል

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ዮሐንስ 7:3-5ን እና 1 ቆሮንቶስ 15:3, 4, 7ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. የኢየሱስ ወንድሞች መጀመሪያ ላይ ለመልእክቱ ምን ምላሽ ሰጥተው ነበር?

  2. ለ. ኢየሱስ በወንድሙ በያዕቆብ ላይ ተስፋ እንዳልቆረጠ የሚያሳየው ምንድን ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. አንዳንዶች ምሥራቹን ለመቀበል ከሌሎች ረዘም ያለ ጊዜ ስለሚወስድባቸው ታጋሽ መሆን ያስፈልገናል።

ኢየሱስን ምሰል

3. የተለየ አቀራረብ ሞክር። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ካቅማማ አትጫነው። የሚቻል ከሆነ፣ ቪዲዮዎች ወይም አንዳንድ ርዕሶች ተጠቅመህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱ ምን እንደሚመስል እንዲሁም እሱን እንዴት እንደሚጠቅመው አስገንዝበው።

4. አታወዳድር። የእያንዳንዱ ሰው ሁኔታ ይለያያል። የቤተሰብህ አባል ወይም ተመላልሶ መጠየቅ የምታደርግለት ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመር ካቅማማ ወይም አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መቀበል ከከበደው ምክንያቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስብ። በጣም የሚወደውን ሃይማኖታዊ ትምህርት መተው ከብዶት ይሆን? ዘመዶቹ ወይም ጎረቤቶቹ ጫና እያደረጉበት ነው? ስለተነጋገራችሁበት ነገር እንዲያስብበትና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ያለውን ጥቅም እንዲረዳ ጊዜ ስጠው።

5. ስለ ግለሰቡ ጸልይ። ምንጊዜም አዎንታዊና ዘዴኛ ለመሆን እንዲረዳህ ይሖዋን ጠይቀው። ግለሰቡ ፍላጎት ከሌለውና ውይይቱን ማቋረጥ የሚያስፈልግህ ከሆነ ይህን ማስተዋል እንድትችል ጸልይ።—1 ቆሮ. 9:26

ተጨማሪ ጥቅሶች

ማር. 4:26-28፤ 1 ቆሮ. 3:5-9፤ 2 ጴጥ. 3:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ