ተጨማሪ መረጃ ለ
ውይይቱን ማቋረጥ ይሻል ይሆን?
አንድ ሰው ከእኛ ጋር በተያያዘ ጥያቄ የፈጠረበትን ነገር ቢያነሳ ወይም ግልጽ ያልሆነለትን ነጥብ እንድናስረዳው ቢፈልግ ውይይቱን ለማቋረጥ አንቸኩልም። ግለሰቡ ይህን ያደረገው በቅንነት እስከሆነ ድረስ “ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ [ያላቸውን]” ሰዎች መርዳት እንፈልጋለን።—ሥራ 13:48
ሆኖም ሰውየው ከተቆጣ፣ መከራከር ከፈለገ ወይም በዚያ ሰዓት ሊያነጋግረን ካልፈለገስ? በሰከነ መንገድና በአክብሮት ውይይቱን አቋርጥ። (ምሳሌ 17:14) በሰላም ለመለያየት ጥረት አድርግ፤ ምክንያቱም ግለሰቡ በቀጣይ ጊዜ ለመወያየት ፈቃደኛ እንዲሆን እንፈልጋለን።—1 ጴጥ. 2:12