የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 1/15 ገጽ 3-4
  • የመንፈስ ቅዱስን ምንነት ለይቶ ማወቅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመንፈስ ቅዱስን ምንነት ለይቶ ማወቅ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቅዱሳን ጽሑፎችና መንፈስ ቅዱስ
  • “በመንፈስ ቅዱስ ስም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • በአምላክ መንፈስ መመራት​—በመጀመሪያው መቶ ዘመንና በዛሬው ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የአምላክ መንፈስ ሕይወትህን እንዴት ሊነካው እንደሚችል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • መንፈስ ቅዱስ—የእግዚአብሔር አንቀሳቃሽ ኃይል
    በሥላሴ ማመን ይገባሃልን?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 1/15 ገጽ 3-4

የመንፈስ ቅዱስን ምንነት ለይቶ ማወቅ

መንፈስ ቅዱስ የእያንዳንዳችንን ሕይወት የሚነካ መሆኑን ታውቅ ነበርን? በሕይወትህ ላይ ትልቅ መሻሻል ሊያመጣ እንደሚችል ተገንዝበህ ነበርን? ይህ አባባል ሊያስገርምህ ይችል ይሆናል። እንዲያውም “መንፈስ ቅዱስ ማን ወይም ምንድን ነው?” ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።

የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት አባል ከሆንክ ሕፃን ልጅ ክርስትና የሚያነሣ ቄስ “በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም” ሲል ሰምተህ ይሆናል። (ማቴዎስ 28:19) አብዛኞቹ ቀሳውስት መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሆነ ሲጠየቁ “መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በምንም መንገድ የማይተናነስ የሥላሴ ሦስተኛ አካል ነው” ይላሉ።

ይሁን እንጂ በመጀመሪያዎቹ የዘመናችን አቆጣጠር መቶ ዓመታት እንዲህ ያለ አስተሳሰብ አልነበረም። በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ከሞቱ ከሦስት መቶ ዓመታት በኋላ የናዚያንዙሱ ግሪጎሪ እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር፦ “አንዳንዶች መንፈስ ቅዱስ ኃይል (ኢኔርጂያ) ነው ሲሉ አንዳንዶች ፍጡር ነው፣ አንዳንዶች አምላክ ነው ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ ስለ ምንነቱ በትክክል እንደማያውቁ ይናገራሉ።”

ዛሬ ግን አብዛኞቹ የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት ስለ መንፈስ ቅዱስ ያላቸው እምነት በሥላሴ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን እምነት ይደግፋልን? ወይም በሰዎች ወግ ላይ ብቻ የተመሠረተ እምነት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክና ስለ ኢየሱስ በሚናገርበት ሁኔታ ስለ መንፈስ ቅዱስ ፈጽሞ አይናገርም። ለምሳሌ ያህል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ የተፀውዖ ስም አልተሰጠም።

ይህ ከግምት ውስጥ የማይገባ አነስተኛ ነገር ነውን? አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ለተፀውዖ ስሞች ከፍተኛ ቦታ ይሰጣል። አምላክ ስለ ስሙ ሲናገር “እኔ [ይሖዋ (አዓት)] ነኝ፣ ስሜ ይህ ነው። ክብሬን ለሌላ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም” ብሏል። (ኢሳይያስ 42:8) የኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስፈላጊነት ገና ከመወለዱ በፊት መልአኩ ለማርያም “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” በማለቱ ተረጋግጧል። (ሉቃስ 1:31) የአብና የወልድ ስም ይህን ያህል አስፈላጊ ከሆነ ለምን መንፈስ ቅዱስ የተፀውዖ ስም አይኖረውም? ይህ ነጥብ ብቻውን በእርግጥ መንፈስ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል ነውን? የሚል ጥያቄ ሊያስነሣ መቻሉ አያጠራጥርም።

ቅዱሳን ጽሑፎችና መንፈስ ቅዱስ

በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ወይም “በብሉይ ኪዳን” ውስጥ “መንፈስ ቅዱስ” ወይም “መንፈሴ” የሚል ቃል ተጠቅሷል። (መዝሙር 51:11፤ ኢዩኤል 2:28, 29) መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ላይ ሊወርድ፣ ሊሞላውና ሊሸፍነው እንደሚችል የሚገልጹ ሐሳቦች እናነባለን። (ዘፀዓት 31:3፤ መሳፍንት 3:10; 6:34) ከአምላክ ቅዱስ መንፈስ ከፊሉ ከአንድ ሰው ተወስዶ ለሌላ ሰው ሊሰጥ ይችላል። (ዘኁልቁ 11:17,25) መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ላይ ሊሠራና በሰው አቅም የማይቻል ነገር እንዲፈጽም ሊያደርገው ይችላል።​—መሳፍንት 14:6፤ 1 ሳሙኤል 10:6

እንደነዚህ ካሉት መረጃዎች ምን ብሎ መደምደም ይቻላል? መንፈስ ቅዱስ አንድ የተለየ አካል አለመሆኑን ነው። የአንድ ሕያው አካል ክፍል እንዴት ከአንድ ግለሰብ ተወስዶ ለሌላ ግለሰብ ሊሰጥ ይችላል? ከዚህም በላይ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ታማኝ አይሁዳውያን መንፈስ ቅዱስን ከአብ ጋር እኩል እንደሆነ አካል አድርገው ይመለከቱ እንደነበረ የሚያረጋግጥ ማስረጃ የለም። መንፈስ ቅዱስን ያመልኩ እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ከዚህ ይልቅ ያመለኩት ኢየሱስ ራሱ “አባቴ” እና “አምላኬ” ያለውን ይሖዋን ብቻ ነበር።​—ዮሐንስ 20:17

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ወይም “አዲስ ኪዳን” የሚባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልም “ብሉይ ኪዳን” ተብሎ እንደሚጠራው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው ሊሞላ ወይም በአንድ ሰው ላይ ሊኖር እንደሚችል ይናገራል። (ሥራ 2:4፤ ሉቃስ 2:25-27) መንፈስ ቅዱስ ‘ተሰጥቷል’፣ ‘ፈስሶአል’፣ ‘ተከፋፍሏል’። (ሉቃስ 11:13፤ ሥራ 10:45፤ ዕብራውያን 2:4) በ22 እዘአ የጴንጠቆስጤ ዕለት ደቀ መዛሙርት ከአምላክ መንፈስ ‘ጥቂቱን’ ተቀብለው ነበር። (ሥራ 2:17 አዓት) በተጨማሪም ቅዱሳን ጽሑፎች በመንፈስ ቅዱስ ስለ መጠመቅና ስለ መቀባት ይናገራሉ።​—ማቴዎስ 3:11፤ ሥራ 1:5፤ 10:38

እንደነዚህ ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫዎች መንፈስ ቅዱስ ራሱን የቻለ ሕያው አካል አለመሆኑን ያረጋግጣሉ። መንፈስ ቅዱስ አካላት ካልሆኑ ሌሎች ነገሮች ጋር ተጨምሮ መጠቀሱ ለዚህ ተጨማሪ ማስረጃ ይሆነናል። ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ እስጢፋኖስ “እምነትና መንፈስ ቅዱስ” እንደሞላበት ይናገራል። (ሥራ 6:5) በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ የአምላክ አገልጋይ መሆኑን “በንጽሕና፣ በእውቀት፣ በትዕግሥት፣ በቸርነት፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ ግብዝነት በሌለው ፍቅር” አረጋግጧል።​—2 ቆሮንቶስ 6:4-6

እውነት ነው፣ አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን ራሱን የቻለ ሕያው አካል አስመስሎ ይናገራል። ለምሳሌ ኢሳይያስ ዓመፀኛ ሰዎች ‘የአምላክን መንፈስ ቅዱስ እንዳስመረሩ’ ተናግሯል። (ኢሳይያስ 63:10) ጳውሎስም መንፈስ ቅዱስ ‘ሊያዝን’ እንደሚችል ተናግሯል። (ኤፌሶን 4:30) በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ እንደሚያስተምር፣ እንደሚሠራ፣ እንደሚናገርና እንደሚመሰክር የሚናገሩ ጥቅሶች በርካታ ናቸው። (ዮሐንስ 14:26፤ 16:13,14፤ 1 ዮሐንስ 5:7,8) ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ጥበብ፣ ሞትና ኃጢአት የመሰሉትን ሕይወት የሌላቸው ነገሮች ልክ ሕያው አካል እንዳላቸው አስመስሎ ይናገራል። (ምሳሌ 1:20፤ ሮሜ 5:17,21) ቅዱሳን ጽሑፎች አንዳንድ ነገሮችን በገሀድ ለመግለጽ ሲፈልጉ በዚህ አገላለጽ ይጠቀማሉ።

ዛሬም ቢሆን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ስንናገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ወይም እንዲህ ያለ መሠረተ ትምህርት ያስተምራል እያልን በተመሳሳይ ራሱን የቻለ ሕያው አካል አስመስለን እንናገራለን። እንዲህ ስንል ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሕያው አካል ነው ማለታችን አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ በተመሳሳይ ሁኔታ ሲናገርም ሕያው አካል መሆኑን መግለጹ አይደለም።

ታዲያ መንፈስ ቅዱስ ምንድን ነው? ራሱን የቻለ ሕያው አካል አይደለም። አምላክ ፈቃዱን ለመፈጸም የሚጠቀምበት አንቀሳቃሽ ኃይሉ ነው። (ዘፍጥረት 1:2) ይሁን እንጂ ሕይወታችን በመንፈስ ቅዱስ የሚነካው እንዴት ነው? በየግላችን መንፈስ ቅዱስ ከሚያከናውናቸው ነገሮች ልንጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ