የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 10/1 ገጽ 2-3
  • አምላክ ይህን ያህል የታገሠው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ይህን ያህል የታገሠው ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ያስብልናል!
  • አንድ ንብ እውነተኛ ንብ የማይሆነው መቼ ነው?
    ንቁ!—1998
  • የንብ እርባታ “ጣፋጭ” ታሪክ
    ንቁ!—1998
  • የአበባ ዱቄት—ለሕይወት አስፈላጊ የሆነ ብናኝ
    ንቁ!—2007
  • ማር—ንቦች ለሰዎች የሚሰጡት ገጸ-በረከት
    ንቁ!—2005
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 10/1 ገጽ 2-3

አምላክ ይህን ያህል የታገሠው ለምንድን ነው?

እስቲ የአንድን በረሃብ የተጎዳ ልጅ በሐዘን የተዋጠ ፊት ተመልከት። የመነመነውን ሰውነቱንና ያበጠውን ሆዱን ተመልከት። ምግብ በጣም እንደሚያስፈልገውና በእጁም ባዶ ሳህን መያዙን ልብ በል። ምናልባት እናቱ በጎደጎዱት ዓይኖችዋ ታየው ይሆናል፤ የእርስዋም ፊት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይታይበታል። ከዚህ በኋላ ሐዘንህን ለማፈን ሞክር፤ እንባዎችህንም ለመቆጣጠር ታገል።

እንዲህ ያለው ትዕይንት ሳህል ተብሎ በሚታወቀው 3.6 ሚልዮን ስኩኤር ኪሎ ሜትር ስፋት ባለው በድርቅ የተመታ ክልል በሚልዮኖች ለሚቆጠር ጊዜ ተደጋግሟል። ይህ ክልል ከደቡባዊ የሰሐራ በረሃ ይኸውም በአትላንቲክ ዳርቻ ከምትገኘው ከሴኔጋል በቀይ ባሕር ዳርቻ እስካለችው እስከ ኢትዮጵያ ድረስ 4800 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ነው። በእርግጥ ረሃብ በሌሎች አገሮች ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሰዎችንም ያጠቃል። የዓለም የጤና ድርጅት በመላዋ ምድር ላይ የሚገኙ 1.1 ሺህ ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች ከባድ ሕመም ወይም የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ዘግቧል።

እርግጥ ነው፤ ረሃብ የሰው ሥቃይ አንዱ ገጽታ ብቻ ነው። ሰው ምድርን በክሏል፤ በዚህም ሁላችንም ተነክተናል። የፖለቲካ ሥርዓቶችም በብዙ ሰዎች ላይ መከራንና ሞትን ያስከተሉትን የፍትሕ መጓደልና ጦርነት ደግፈዋል። አምላክ እነዚህን ነገሮች የሚፈቅደው ለምንድን ነው? ስለ እኛስ ያስባልን?

አምላክ ያስብልናል!

ፈጣሪያችን ስለ እኛ ያስባል። አምላክ እንደሚያስብልንና ነገሮችን ለጥቅማችንና በሁሉም ፍጥረቱ ውስጥ ስምምነት እንዲኖር በሚያስችል ሁኔታ ለማስተካከል ስላለው ችሎታ ብዙ ማረጋገጫ አለ። ለምሳሌ ያህል በዚህ ገጽ ላይ ያለውን አንዲት ንብ በአንድ የፍራፍሬ ዛፍ ላይ የሚገኝን አበባ ስትቀስም የሚያሳይ ስዕል ተመልከት። ንቢቱ ለምግብነት የሚያስፈልገውን የአበባ ማር የምታገኘው ከዛፉ ነው። ዛፉ ደግሞ የንቢቱ አካል ተሸክሞ የሚያመጣው ፖለን (የአበባ ዱቄት) ያስፈልገዋል። በዚህ መንገድ የዘር ውህደት ይከናወንና ዛፉ ፍሬ ሊያፈራ ይችላል። በዚህ ዓይነት የሚራቡት ዛፎች ሁሉም ባይሆኑም በዚህ ረገድ ግን አምላክ ልዩ የሆነ ትብብር እንዲኖር አድርጓል። የእርሱም ጥሩነት ለደስታችንና ለጥቅማችን ስንል የምንበላውን ፍሬ አስገኝቷል።

ንቢቱ ራስዋ ከ30,000 የሚበልጡ በደንብ የተደራጁ የንብ ሠራዊት ክፍል ነች። ከእነዚህ አንዳንዶቹ ቀፎውን ይጠብቃሉ፤ ሌሎቹም ያጸዱታል ወይም ንፁህ አየር እንዲገባ ያራግባሉ። አሁንም ሌሎቹ ማርና የአበባ ዱቄት ያጠራቅማሉ፣ እጭዎቹን ይመግባሉ፣ ወይም አዲስ ማር የሚገኝባቸውን ቦታዎች ይቃኛሉ። እነዚህ ታታሪ ንቦች ያዘጋጁትን ጣፋጭና ገንቢ የሆነውን ማር ተመግበን ለመጠቀም እንድንችል ዝግጅት ያደረገው አምላክ ራሱ ነው።

በንቦችና በዕፅዋት መካከል እንዲሁም በጥቃቅን ነፍሳት መካከል የሚታየው ተዓምራዊ ኅብረት ፈጣሪ ሕያዋን ነገሮችን እርስ በርሳቸው እንዲስማሙ የማድረግ ፍጹም ችሎታ እንዳለው ከሚያሳዩት ብዙ ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ ብቻ ነው። እንዲያውም “አምላክ የብጥብጥ አምላክ ሳይሆን የሰላም አምላክ ነው።” (1 ቆሮንቶስ 14:33) እንዲህ ከሆነ ታዲያ የሰው ልጅ ብዙ ሐዘንና ሥቃይ ባስከተለ ብጥብጥ ውስጥ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው? አምላክ ስለ እኛ የሚያስብ ከሆነ ይህንን ሁኔታ ሳያስተካክል ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የቆየው ለምንድን ነው? አምላክ ያን ያህል የታገሠው ለምንድን ነው?

የአምላክ ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። ይህ አስደናቂ መጽሐፍ ይሖዋ አምላክ የታገሠበት በቂ ምክንያት እንዳለው ይነግረናል። ይህ ምክንያት ምንድን ነው? የአምላክስ ትዕግሥት የሚቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Cover photo: Frilet/​Sipa

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ