የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 10/15 ገጽ 30-31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለብዙሃኑ ባሕል ሊኖረን የሚገባው ሚዛናዊ አመለካከት
    ንቁ!—2000
  • ታስታውሳለህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • አንድ ክርስቲያን ከቀብር ሥነ ሥርዓት ጋር ለተያያዙ ልማዶች የሚኖረው አመለካከት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • አምላክን ከማያስደስት ወግና ልማድ ራቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 10/15 ገጽ 30-31

የአንባብያን ጥያቄዎች

◼ አንድ ሰው በሚሞትበት ጊዜ ክርስቲያኖች ለሟቹ ቤተሰቦች አበባ መስጠት ወይም ወደ ቀብሩ ስፍራ አበባ መላክ ተገቢ ነውን?

በአንዳንድ አገሮች እንዲህ ማድረግ የተለመደ ነገር ነው። ነገር ግን በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ አበባ መጠቀም አንዳንዴ ሃይማኖታዊ ትርጉም አለው። ስለዚህ ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ተመሳሳይ ዝምድና ያላቸው የሚመስሉ ሌሎች ባሕሎችም ስላሉ ጉዳዩን ዘርዘር ባለ መልኩ እንመርምረው። ዘ ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ ሪሊጅን (የሃይማኖት ኢንሳይክሎፔዲያ (1987) የሰጠውን ትችት አስተውሉ፦

“አበባዎች ከተባዕትና ከእንስት አማልክት ጋር ስለሚያያዙ ከቅዱሱ ዓለም ጋር ይዛመዳሉ። ፍሎራ የተባለችው የሮማ የጸደይ ወራትና የአበባዎች እንስት አምላክ ውበትና መዓዛ ትሰጣለች። . . . ምግብና አበባ በማቅረብ. . . የአማልክትን ሞገስና እርዳታ ማግኘት ይቻላል።

“አበባዎችን ከቀብር ሥነ ሥርዓት ጋር ማዛመድ በዓለም በሙሉ ያለ ነገር ነው። ግሪኮችና ሮማውያን ሙታንንና መቃብራቸውን በአበባ ይሸፍኑ ነበር። በጃፓን አገር ቡድሂስቶች ሲሞቱ ነፍሶቻቸው ወደ ጽጌረዳ አበባ ይወሰዳሉ። የመቃብር ድንጋዮቹም ከድንጋይ በተጠረበ አበባ ላይ እንዲቀመጡ ይደረግ ነበር። . . . ታሂታውያን ሰው ሲሞት ከሕይወት በኋላ ላለው የተቀደሰ ኑሮ በቀላሉ እንዲያልፍ በማለት በዘንባባ ዝንጣፊዎች የተጠቀለለ የአበባ እቅፍ በአስከሬኑ አጠገብ ያስቀምጣሉ። የአበባ ሽቶም በሬሳው ላይ ያርከፈክፉበት ነበር። . . . በተለዩ የተቀደሱ ወቅቶችም አበባዎች በዕጣን ወይም በሽቶ መልክ ተዘጋጅተው ይቀርቡ ነበር።”

አንዳንድ ክርስቲያኖች አበባዎች ከሐሰት ሃይማኖት ጋር በተያያዘ መንገድ ይሠራባቸው እንደነበር ሲያውቁ አበባ መስጠት ወይም ወደ ቀብሩ መላክ እንደሌለባቸው ተሰምቷቸዋል። የኢየሱስ ተከታዮች “የዓለም ክፍል ስላልሆኑ” የነዚህ ክርስቲያኖች ስሜት ዓለማዊ ልማዶችን ለማስወገድ ያላቸውን ፍላጎት ያንፀባርቃል። (ዮሐንስ 15:19) ይሁን እንጂ ይህን ርዕሰ ጉዳይ የሚመለከቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና የአካባቢው ሰዎች ስሜት በጉዳዩ ላይ ተጽዕኖ አላቸው።

አበባዎች ሕያዋን ሰዎች እንዲደሰቱባቸው አምላክ ከሰጣቸው መልካም ስጦታዎች መሃል አንዱ ክፍል ናቸው። (ሥራ 14:15-17፤ ያዕቆብ 1:17) እሱ የፈጠራቸው አበባዎች ውበት ለእውነተኛ አምልኮ አገልግሎት ሰጥተዋል። የመገናኛው ድንኳን መቅረዝ “በለውዝ አበባዎችና ጉብጉቦች” ያጌጠ ነበር። (ዘፀዓት 25:31-34) በቤቱ ግንብ ግድግዳ ላይ ከተቀረጹት መሃል ያበባ ጉንጉኖችና የዘንባባ ዛፎች ይገኙበታል። (1 ነገሥት 6:18, 29, 32) በግልጽ እንደሚታየው አረማውያን በአበባዎች ወይም በአበባ ጉንጉኖች ይጠቀሙ የነበሩ መሆናቸው እውነተኛ አምላኪዎች በአበባዎች ከመጠቀም ፈጽሞ እንዲርቁ አላደረጋቸውም።​—ሥራ 14:13

የሆነው ሆኖ የቀብር ሥርዓቶችንም ሆነ ሌሎች ልማዶችን ስለመከተል ለሚነሣው ጥያቄ ምን ሊባል ይቻላል? መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ልማዶችን የሚጠቅስ ሲሆን አንዳንዶቹ ለእውነተኛ አምላኪዎች የማይገቡ ሌሎቹ ደግሞ የአምላክ ሕዝቦችም ይከተሏቸው የነበሩ ናቸው። 1 ነገሥት 18:28 እውነተኛ አምላኪዎች ሊከተሉት የማይገባውን የበአል አምላኪዎችን “በታላቅ ቃል የመጮህና ሰውነታቸውን የማድማት” ልማድ ይጠቅሳል። በሌላ በኩል ደግሞ ሩት 4:7 “በእስራኤል ስለነበረው” ሁኔታ ሲናገር “በጥንት ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ መካከል የነበረውን የመቤዠት ልማድ” አይነቅፍም።

በአምላክ ተቀባይነት ያላቸው ልማዶች በጣም ጥብቅ በሆኑ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ውስጥም ሊጀምሩና ሊያድጉ ይችላሉ። ለምሳሌ አምላክ የማለፍ በዓልን ሥርዓት ሲያወጣ ወይንን መጠቀም አልተጠቀሰም ነበር። ነገር ግን በአንደኛው መቶ ዘመን የጽዋ ወይን መጠቀም የተለመደ ሆኖ ነበር። ኢየሱስና ሐዋርያቱ ይህን ሃይማኖታዊ ባሕል አልተቃወሙም። ተነቃፊ ሆኖ ስላላገኙት ተቀብለውታል።​—ዘፀዓት 12:6-18፤ ሉቃስ 22:15-18፤ 1 ቆሮንቶስ 11:25

በአንዳንድ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችም እንዲሁ ነው። ግብፃውያን ሬሳ እንዳይበሰብስ በመድሃኒት የማሸት ልማድ ነበራቸው። ታማኙ አበው ዮሴፍም በጥላቻ “ይህ ዓረማዊ ልማድ ስለሆነ እኛ ዕብራውያን ከእሱ መራቅ አለብን” አላለም። ከዚህ ይልቅ “ባለ መድሃኒቶች አገልጋዮቹ አባቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ።” ይህን ያስደረገበትም ምክንያት ያዕቆብ በተሰፋይቱ ምድር ለመቀበር እንዲችል ሬሳው ሳይፈራርስ እንዲቆይ ብሎ እንደነበር ግልጽ ነበር። (ዘፍጥረት 49:29 እስከ 50:3) ቆየት ብሎም አይሁዳውያን ሬሳ ማጠብና በሞተበት ዕለት መቅበርን የመሳሰሉት የተለዩ የቀብር ሥነ ሥርዓቶች አዳብረው ነበር። የቀድሞ ክርስቲያኖች እነዚህን የአይሁድ ልማዶች ተቀብለዋቸዋል።​—ሥራ 9:37

ይሁን እንጂ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በማትሞት ነፍስ ማመንን የመሰሉ ሃይማኖታዊ ትርጉሞች ያሉት መሆኑ ከታየስ ምን መደረግ አለበት? አንዳንዶች “ከሞት በኋላ ወዳለው የተቀደሰ ኑሮ በቀላሉ እንዲሄድ ለማድረግ በዘንባባ ዝንጣፊዎች የተጠቀለሉ አበባዎችን በሬሳው አጠገብ ያስቀምጡና የአበባ ሽቶ በሬሳው ላይ ያርከፈክፉበት ነበር” በማለት ኢንሳይክሎፔዲያው የተናገረውን ቃል አስታውስ። እንዲህ ዓይነት ልማድ መኖሩ የአምላክ አገልጋዮች ከዚህ ጋር ከሚመሳሰል ማንኛውም ነገር መራቅ አለባቸው ማለት አይደለም። አይሁዳውያን “ከሞት በኋላ ባለ የተቀደሰ ኑሮ” ባያምኑም መጽሐፍ ቅዱስ “የኢየሱስን ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት” ይላል።​—ዮሐንስ 12:2-8፤ 19:40

ክርስቲያኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር የሚጋጩ ልማዶችን ማስወገድ አለባቸው። (2 ቆሮንቶስ 6:14-18) ያም ሆኖ ሁሉም ዓይነት ዕቃዎች፣ ቅርጾችና ልማዶች በአንድ ወቅት ወይም በአንድ ቦታ የሐሰት ትርጉም ተሰጥቷቸው የነበሩ ወይም ቅዱስ ጽሑፋዊ ካልሆኑ ትምህርቶች ጋር ተያይዘው የነበሩ ናቸው። ዛፎች ይመለኩ ነበር። የልብ ቅርጽ እንደ ቅዱስ ነገር ይታይ ነበር። ዕጣንም በዓረማዊ ሥነ ሥርዓቶች ይሠራበት ነበር። ታዲያ አንድ ክርስቲያን ፈጽሞ ዕጣን መጠቀም፣ በማንኛውም ጌጥ ውስጥ የዛፍ ምስል ማስገባት ወይም የልብ ቅርጽ ያለው ጌጥ ማድረግ የለበትም ማለት ነውን?a ይህ ተገቢ አስተሳሰብ አይደለም።

አንድ እውነተኛ ክርስቲያን ሊያስብበት የሚገባው፦ ልማዱን መከተሌ ለሌሎች ቅዱስ ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆኑ እምነቶችን ወይም ልማዶችን እንደምትከተል የሚያመለክታቸው ነውን? የወቅቱ ሰዓትና ቦታ መልሱን ሊለውጠው ይችላል። አንድ ልማድ (ወይም ቅርጽ) በሺህ ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት የሐሰት ሃይማኖታዊ ትርጉም ኖሮት ሊሆን ይችላል ወይም ደግሞ ይኸው ሐሰት ሃይማኖታዊ ትርጉም ዛሬም በአንድ ሩቅ አገር ሊኖር ይችላል። ነገር ግን በመመራመር ጊዜህን ሳታባክን በፊት ራስህን “በምኖርበት አካባቢ የተለመደው አመለካከት ምንድን ነው?” ብለህ ጠይቅ።​—1 ቆሮንቶስ 10:25-29

አንድ ልማድ (ወይም እንደ መስቀል የመሰለ አንድ ቅርጽ) የሐሰት ሃይማኖታዊ ትርጉም እንዳለው የታወቀ ከሆነ አስወግደው። ስለዚህ አበባዎችን በመስቀል ወይም በቀይ የልብ ቅርጽ ሠርቶ (አሠርቶ) መላክ ሃይማኖታዊ ትርጉም ያዘለ ከሆነ ክርስቲያኖች አያደርጉትም። ወይም በአካባቢው አበባዎች በቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ወይም በመቃብር ቦታ ላይ የሐሰት ሃይማኖታዊ ትርጉም በሚያሰጥ ሁኔታ ሥራ ላይ የሚውሉበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። እንዲህ ከሆነ ክርስቲያኖች እንዲህ ካለው ድርጊት ይርቃሉ። ይሁን እንጂ እንዲህ ስለተባለ በቀብር ስነሥርዓት ላይ የአበባ እቅፍ መስጠት ወይም በሆስፒታል ለተኛ ወዳጅ አበባ መላክ ስሕተት ነው ወይም በሐሰት ሃይማኖት ላይ የተመሠረተ ተግባር ነው ማለት አይደለም።b

በተቃራኒው በብዙ አገሮች አበባ የማበርከቱ ልማድ በሠፊው የተለመደና ተገቢ እንደሆነ የደግነት ድርጊት የሚታይ ነው። አበቦች አንድ ዓይነት ውበትን በመስጠት አንድን አሳዛኝ ወቅት የበለጠ ደስ የሚል እንዲሆን ያደርጋሉ። የኀዘኑ ተካፋይ የመሆንንና የአሳቢነትን መንፈስ የሚያሳዩ ሊሆኑ ይችላሉ። በሌላ አካባቢዎች ደግሞ እነዚህ ዓይነት ስሜቶች የሚገለጡት ለታመሙት ወይም ለኀዘንተኞቹ ምግብ ማቅረብን በመሳሰሉት የለጋስነት ሥራዎች ሊሆን ይችላል። (ዶርቃ ለሌሎች ያላትን አሳቢነት በመግለጿ ስትሞት ለሷ የታየውን ፍቅር አስታውሱ። (ሥራ 9:36-39) አበባዎችን የመስጠቱ ልማድ በግልጽ ከሐሰት እምነቶች ጋር የተያያዘ በማይሆንበት ጊዜ አንዳንድ የይሖዋ ምስክሮችም ሆስፒታል ውስጥ ለተኛ ወይም የሞት አደጋ ለደረሰበት ቤተሰብ የፈኩ አበቦችን ይወስዳሉ። በተጨማሪም በግለሰብ ደረጃ ስሜታቸውንና ሐዘናቸውን ተግባራዊ በሆኑ ሌሎች መንገዶች ይገልጹ ይሆናል።—ያዕቆብ 1:27፤ 2:14-17

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

a አረማውያን ከጥንት ጀምሮ ዕጣን በአምልኮ ሥርዓታቸው ይጠቀሙ ነበር። ነገር ግን ለአምላክ ሕዝቦችም በእውነተኛ አምልኮ ዕጣንን መጠቀም ስህተት አልነበረም። (ዘፀዓት 30:1, 7, 8፤ 37:29፤ ራእይ 5:8) እንደዚሁም በታህሣስ 22, 1976 ንቁ! ላይ “የጣኦት አምልኮ ጌጦች ናቸውን?” የሚለውን ርዕሰ ትምህርት ተመልከቱ።

b አንዳንድ ሰዎች አበባ ሊልክ የሚፈልግ ሰው በአበባው ፋንታ ገንዘቡን ለጉባኤው እንዲያበረክተው ወይም ለሆነ በጎ አድራጎት እንዲያውለው አስቀድመው ስለሚያሳውቁ የቤተሰቡ ፈቃድ እንደሆነ ማወቅና ማክበር ያስፈልጋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ