የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 12/15 ገጽ 28-29
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የክፍል ትምህርት
    ትምህርት ቤትና የይሖዋ ምሥክሮች
  • አምላክ ባስተማረህ መንገድ ሂድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • በመንፈሳዊ ጠንካራ የሆነ ቤተሰብ መገንባት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 12/15 ገጽ 28-29

የአንባብያን ጥያቄዎች

◼ ክርስቲያን ቤተሰቦች ልጃቸው ሃይማኖታዊ ትምህርት በግዳጅ በሚሰጥበት ትምህርት ቤት መማር ካለበት ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?

ክርስቲያን ወላጆች ልጃቸው በሐሰት ሃይማኖት ትምህርት እንዲታጠብ የማድረግ ፍላጎት የላቸውም። ይሁን እንጂ ልጆች በሐሰት ሃይማኖታዊ ድርጊቶች ወይም የአምልኮ ስነ ሥርዓቶች ባይካፈሉም የሃይማኖት ትምህርት በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ ከመገኘት ሊቀሩ የማይችሉባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

ለልጆች በሚሰጥ ሃይማኖታዊ ትምህርት ወይም መመሪያ ረገድ የአምላክ ወዳጅ የነበረው አብርሃም ጥሩ ምሳሌ ትቷል። ልጁን ያሳደገው በሐሰት ሃይማኖታዊ ስሕተትና በአስጸያፊ “ቅዱስ” ድርጊቶች ወይም ልማዶች በተከበበችው በከነዓን ምድር ነበር። (ከዘጸአት 34:11-15፤ ዘሌዋውያን 18:21-30፤ ዘዳግም 7:1-5, 25, 26፤ 18:9-14 ጋር አወዳድር) ዳሩ ግን አብርሃም ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ሃይማኖታዊ ትምህርት ይሰጥ ነበር። አምላክም “ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የይሖዋን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ” እርግጠኛ ነበር።​—ዘፍጥረት 18:19

ኢየሱስም በወጣትነቱ ዘመን በእውነተኛው አምልኮ ረገድ ከቤተሰቡና ከጉባኤው ባገኛቸው ትምህርቶች ተጠቅሞ ነበር። በዚህም ምክንያት “በጥበብና በቁመት በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።”​—ሉቃስ 2:52

በአብዛኛው የምድር ክፍሎች ክርስቲያን ወጣቶች ዓለማዊ ትምህርት የሚማሩት በሕዝብ ትምህርት ቤቶች ነው። የሚሰጠው ትምህርት ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትና ከታወቀ ሐቅ ጋር የማይስማማ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ያህል ብዙ ክርስቲያን ወጣቶች ሳይንስ ወይም ባዮሎጂ የሥርዓተ ትምህርቱ ክፍል በመሆኑ ተከታትለዋል። አብዛኞቹ ለዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሐሳብና ከዚህ ንድፈ ሐሳብ ጋር ለሚዛመዱት ሕይወት በምድር ላይ ስለተገኘበት ሁኔታ የሚገልፁ አስተሳሰቦች ተጋልጠዋል።

ይሁን እንጂ ለዚህ ዓይነቱ ሥርዓተ ትምህርት መጋለጣቸው እነዚህ ክርስቲያን ወጣቶች የአምላክ የለሹ ዝግመተ ለውጥ ደጋፊዎች እንዲሆኑ አላደረጋቸውም። ለምን? ምክንያቱም ቀደም ሲል በቤትና በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ አምላክ በመንፈሱ መሪነት ባስጻፈው ቃሉ ላይ የተመሠረተና “መልካሙንና ክፉውን ለመለየት ልቡናቸውን (የማስተዋል ዓይናቸውን)” ለማሠልጠን የረዳቸውን መረጃ አግኝተዋል። (ዕብራውያን 5:14) ብዙ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እምነት ከሚያጠነክረው ሕይወት እንዴት መጣ? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት?a በተሰኘው መጽሐፍ አማካኝነት ስለ ዝግመተ ለውጥ አጥንተዋል። እነዚህ ተማሪዎች በዚህ መንገድ የታጠቁ በመሆናቸው በክፍል ውስጥ ስለ ዝግመተ ለውጥ የሚሰጠውን ትምህርት የሚታመን ጉዳይ አድርገው አልተቀበሉትም። ሆኖም በክፍል ውስጥ በሚሰጡት መልስና በፈተናዎቻቸው በደንብ ያዳመጡ መሆናቸውንና የቀረቡላቸውን ዝርዝር ጉዳዮች ለመማር መቻላቸውን ሊያሳዩ ችለው ነበር። አንዳንዶች እንዲያውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሰው ፈጣሪ ከቀረቡት እውነቶች ጋር የሚስማሙ አማራጭ ማብራሪያዎችን የመስጠት አጋጣሚ አግኝተዋል።​—1 ጴጥሮስ 3:15

ይሁንና ስለ አንድ በአካባቢው ያለ ትልቅ ሃይማኖት ወይም በአጠቃላይ ስለ ሃይማኖት ለማስተማር ስለተወሰኑ ክፍለ ጊዜዎችስ ምን ሊባል ይቻላል?

እንዲህ ዓይነት ትምህርቶችን የሚያስተምሩ አስተማሪዎች ለሚያስተምሩት ሃይማኖት ወገናዊነት ሳይሰማቸው በገለልተኛነት ወይም እንዲሁ ለመንገር ያህል ብቻ የሚያቀርቡት ላይሆን ይችላል። እንዲያውም መምህሩ ወይም መምህርዋ በዚያ ሃይማኖት የሚመላለሱና የተማሪዎችን አእምሮና ልብ ለመለወጥ የሚሞክርበት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የይሖዋ ምስክሮች ልጆቻቸው ከሃይማኖታዊ ትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ነፃ እንዲሆኑ ይመርጣሉ። ይህም የትምህርት ጊዜያቸውን የሌሎች ትምህርቶች የቤት ሥራዎቻቸውን ሠርተው ለመጨረስ ወይም በትምህርት ቤቱ ቤተመጻሕፍት ለማጥናት ይበልጥ ጠቃሚ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙበት ሊያስችላቸው ይችላል።

ይሁን እንጂ በአንዳንድ ቦታዎች እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች የእሺታ መልስ ይነፈጋቸዋል። ምናልባትም ትምህርት ቤቱ ሕዝባዊ ባለ ሥልጣኖች ሁሉም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመጨረስ ወይም ለመመረቅ ከፈለጉ የሃይማኖት ትምህርቱንም እንዲከታተሉና እንዲያሟሉ ያስገድዱ ይሆናል። በዚህ ረገድ እያንዳንዱ ቤተሰብ ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን ይኖርበታል።

በቀድሞ ጊዜ የነበሩ አንዳንድ የአምላክ አገልጋዮች ያለ ፈቃዳቸው ለሃይማኖታዊ ትምህርቶች ወይም ተግባሮች የተጋለጡባቸውና ለአምላክ ታማኝ ሆነው የጸኑባቸው ሁኔታዎች ነበሩ። ሙሴ እንዲህ ያለ ሁኔታ ሳያጋጥመው አልቀረም። የፈርዖን የልጅ ልጅ እየተባለ አድጎ ስለነበር “የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተምሮአል።” (ሥራ 7:20-22) ያ ጥበብም በመጠኑ በግብጽ የተለመዱ የነበሩትን እምነቶችና ሃይማኖታዊ ድርጊቶች ሳይጨምር አይቀርም። ነገር ግን በግልጽ እንደሚታየው ሙሴን ከቤተሰቡና ምናልባትም ከሌሎች ዕብራውያን የላቀ ትምህርት ጠብቆታል።​—ዘፀአት 2:6-15፤ ዕብራውያን 11:23-26

እንደዚሁም የዳንኤል ባልንጀሮች የነበሩትንና በባቢሎን ልዩ ትምህርት ተሰጥቶአቸው የመንግሥት ሠራተኞች የተደረጉትን የሦስቱን ዕብራውያን ወጣቶች ምሳሌም አስብ። (ዳንኤል 1:6, 7) የፈለጉትን ነገር ለማድረግም ሆነ እምቢ ለማለት ነፃነት አልነበራቸውም። በአንድ ወቅት ንጉሡ ናቡከደነፆር የብሔራዊ ታማኝነት ትርዒት በሚታይበት በዱራ ሜዳ ባቆመው የወርቅ ምስል ፊት ከሌሎች ባለ ሥልጣኖች ጋር እንዲቀርቡ አውጆ ነበር። እነዚህ ዕብራውያን እንዴት ያለ ምላሽ ሰጡ? እዚያ ቦታ ላለመሄድ እንደሚመርጡ እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። ሆኖም መቅረት አይቻልም ነበር።b ይሁን እንጂ ለእምነታቸውና ሁሉን ቻይ ለሆነው አምላክ በታማኝነት ጸንተዋል። በቦታው እንዲገኙ አምላካዊው ሕሊናቸው ቢፈቅድላቸውም በማንኛውም ዓይነት የሐሰት አምልኮ ተግባር ከመካፈል ወይም ከመጠመድ በቁርጠኝነት እምቢ ብለዋል።​—ዳንኤል 3:1-18

ሁሉም ተማሪዎች በሃይማኖት ትምህርቱ ክፍለ ጊዜ እንዲገኙ ግዳጅ ካለና መደበኛውን ፈተና ለማለፍ እንዲችሉ ያህል ብቻ የሚማሩ ከሆነ በናቡከደነፆር ትእዛዝ ሦስቱ ዕብራውያን እንዳደረጉት ከእውነተኛ የክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ የሆኑ ልጆችም ሊገኙ ይችላሉ። ነገር ክርስቲያን ወጣቶችም አምላክን ያስቀድማሉ። ሦስቱ ዕብራውያን ሌሎች ለወርቁ ምስል ተደፍተው እንዳይሰግዱ ለማድረግ ጣልቃ እንዳልገቡ ሁሉ ክርስቲያን ወጣቶቹም በሚነገረው በእያንዳንዱ የተሳሳተ ዓረፍተ ነገር ላይ ወይም ሌሎች በሚካፈሉበት ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆነ ተግባር ላይ ክርክር መግጠም አያስፈልጋቸውም። ይሁን እንጂ ክርስቲያን ወጣቶች በአምልኮ ድርጊቶች አይካፈሉም። በጸሎት፣ በሃይማኖታዊ መዝሙሮችና እንዲህ በመሳሰሉት ነገሮች አይተባበሩም።

እነዚህ ወጣቶች ከትምህርት ሰዓት ውጭ በሆነው ጊዜያቸው ‘በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጧቸው የሚችሉትን የቅዱሳን መጻሕፍት’ የሚያንጽ እውቀት ለመውሰድ ራሳቸውን ማትጋት ይኖርባቸዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:15) ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የሐሳብ ግንኙነት ወይም ልውውጥ በማድረግ የክፍል ትምህርቱን ይዘት ዘወትር መከታተል ይኖርባቸዋል። ይህም በዕድሜ ትልልቅ የሆኑትን ክርስቲያኖች ልጆቻቸው እንዳይወናበዱ ወይም እንዳይሳሳቱ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት መታረም ወይም መብራራት የሚያስፈልገው ምን እንደሆነ እንዲመለከቱ ይረዳቸዋል።

[የግርጌ ማስታወሻዎች]

a በመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትንንሽ ጽሑፎች ማኅበር ኒውዮርክ የተዘጋጀ።

b መጽሐፍ ቅዱስ ዳንኤል በዱራ ሜዳ ስለመገኘቱና አለመገኘቱ አይገልጽም። ምናልባት በመንግሥቱ ውስጥ የነበረው ከፍተኛ ማዕረግ እዚያ ከመሄድ ነፃ አድርጎት ይሆናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ