የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 9/1 ገጽ 8
  • ሕዝበ ክርስትናና የባሪያ ንግድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሕዝበ ክርስትናና የባሪያ ንግድ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሕዝበ ክርስትና ፍሬ በአፍሪካ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • በባርነት ላይ የተካሄደ ረዥም ተጋድሎ
    ንቁ!—2002
  • ባሪያዎች የተጓዙበትን መንገድ መጎብኘት
    ንቁ!—2011
  • ‘በዋጋ ተገዝታችኋል’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 9/1 ገጽ 8

ሕዝበ ክርስትናና የባሪያ ንግድ

በ19ኛው መቶ ዘመን የካቶሊክና የፕሮቴስታንት ሚስዮናውያን የባሪያን ንግድ በመቃወም ረገድ አንድ ሆነው ነበር። ይሁን እንጂ ይህን አቋማቸውን ያልጠበቁባቸው ጊዜያት ነበሩ። ከዚያ በፊት በነበሩት መቶ ዓመታት በሰዎች ላይ ከፍተኛ ሥቃይ ያስከትል የነበረውን የባሪያ ንግድ ከመደገፍም አልፈው በቀጥታ በንግዱ ተካፍለው ነበር።

በኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ የሚያልፈው የባሕር መንገድ በ15ኛው መቶ ዘመን ከተገኘ በኋላ ሚሲዮናውያን ወደ ምዕራባዊና ምሥራቃዊ የአፍሪካ የባሕር ዳርቻዎች መምጣት ጀመሩ። ከሦስት መቶ ዘመናት በኋላ ግን በአፍሪካ የሚስዮናዊነት ሥራ ወደ ማክተሙ ተዳርሶ ነበር። ወደ ሚስዮናውያኑ ሃይማኖት የተለወጡት በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ። ለዚህም አንዱ ምክንያት ሕዝበ ክርስትና በባሪያ ንግድ መካፈልዋ ነበር። ሲ. ፒ. ግሩቭስ የተባሉ ጸሐፊ በአፍሪካ የክርስትና መተከል በሚል መጽሐፋቸው ውስጥ የሚከተለውን ገልጸዋል፦

“የተጧጧፈ የባሪያ ንግድ የመጣው ከክርስትና ሚስዮናዊ እንቅስቃሴ ጋር ነበር። ይህ ንግድ ስህተት እንደሆነ ተደርጎ አይታይም ነበር። እንዲያውም እያንዳንዱ ሚስዮን የየራሱ ባሪያዎች ነበሩት። በአንጎላ ዋና ከተማ በሎአንዳ [የዛሬዋ ሉዋንዳ] የነበረ የካቶሊክ ኢየሱሳዊ ገዳም 12,000 ባሪያዎች ነበሩት። በአንጎላና በብራዚል መካከል የባሪያ ንግድ በተስፋፋ ጊዜ የሎአንዳ አቡን በመርከብ ማቆሚያው የባሕር ዳር በድንጋይ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠው እንደ ማዕበል አስቸጋሪ የሆነው ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ከፍተኛ ደስታ እንደሚያገኙ በመግለጽ በመርከቡ ተጭነው ለሚሄዱት ሰዎች ኤጲስቆጶሳዊ ቡራኬአቸውን ሰጥተው ነበር።”

ሲ. አር. ቦክሰር አፍሪካ ከጥንት ዘመናት እስከ 1800 በተሰኘ መጽሐፋቸው እንደገለጹት ኢየሱሳዊ ሚስዮናውያን “በጥቁሮች የባሪያ ንግድ ላይ ምንም ዓይነት ተቃውሞ” አላነሱም ነበር በማለት አረጋግጠዋል። ቦክሰር በመጨመርም በሉዋንዳ ባሪያዎች ወደ እስፓኝና የፖርቱጋል ቅኝ ግዛቶች ለመሄድ በመርከብ ከመሳፈራቸው በፊት “በአቅራቢያው ወደሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ይወሰዱ ነበር። . . . እዚያም በመቶ በመቶ እየሆኑ በአንድ ላይ በደብሩ ቄስ ይጠመቁ ነበር” ይላሉ። ከዚያም ባሪያዎቹ “ቅዱስ ውኃ” ወይም ፀበል ከተረጩ በኋላ “አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችኋል። የካቶሊክን እምነት ወደምትማሩበት ወደ እስፓኒያርዶች አገር ልትሄዱ ነው። ከእንግዲህ በኋላ ስለ አገራችሁ አታስቡ . . . በበጎ ፈቃድ ሂዱ” ተብሎ ይነገራቸው ነበር።

በእርግጥ የባሪያን ንግድ ይደግፉ የነበሩት የሕዝበ ክርስትና ሚስዮናውያን ብቻ አልነበሩም። ጂኦፍሬይ ሙርሃውስ ሚስዮናውያን በተሰኘ መጽሐፋቸው ላይ “የባሪያ ንግድ እስከ አሥራ ስምንተኛው መቶ ዘመን የመጨረሻ አጋማሽ ድረስ የጠቅላላውን ዓለም ድጋፍ ያገኘ ሥራ ሆኖ ነበር” በማለት ይገልጻሉ። ሙርሃውስ በአንድ የአሥራ ስምንተኛው መቶ ዘመን የነበረና የአፍሪካ ጥቁር ባሪያዎች ንግድ ከሰብአዊነትና ከተገለጹልን ሃይማኖታዊ ሕጎች ጋር የሚስማማ መሆኑ ተረጋግጦአል በሚል ርዕስ አንድ ትንሽ ጽሑፍ የጻፈን ቶማስ ቶምፕሰን የተባለ አንድ ፕሮቴስታንት ሚስዮናዊ በምሳሌነት ይጠቅሳሉ።

ያም ሆነ ይህ ሕዝበ ክርስትና በባሪያ ንግድ በመሳተፏ በሚልዮን በሚቆጠሩ የአፍሪካ ባሮች ላይ ለደረሰው አሰቃቂ ሥቃይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር አብራ በኃላፊነት የምትጠየቅ ናት። ኢንሳይክሎፒድያ ብሪታኒካ “በመርከብ ከአፍሪካ ከመነሳታቸው በፊት የሞቱት ባሪያዎች ሳይቆጠሩ 12.5 በመቶዎቹ ወደ ዌስት ኢንዲስ በሚጓዙበት ጊዜ ይሞታሉ። በጃማይካ 4.5 በመቶዎቹ በወደብ ላይ ሳሉ ወይም ለሽያጭ ከመቅረባቸው በፊት ይሞታሉ። ወደሚፈለገው ቦታ ከደረሱ በኋላ ደግሞ በመጀመሪያ ከተጫኑት ሲሶ የሚሆኑት ተስማሚ ባሪያዎች እንዲሆኑ በሚደረግበት ጊዜ ይሞታሉ” በማለት ይገልጻል።

ይሖዋ አምላክ በቅርቡ ሕዝበ ክርስትናንም ሆነ ሌላ ዓይነት የሐሰት ሃይማኖቶችን ሁሉ ችላ ብለው ለተመለከቱአቸው፣ እንዲያውም ለባረኩአቸው አሰቃቂ የደም ጥፋተኞች ድርጊት ሁሉ ይጠይቃቸዋል።—ራእይ 18:8, 24

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ምስል]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ባሪያዎች ወደ መርከብ ይታጨቁ የነበሩበትን ሁኔታ የሚያሳይ ሥዕል

[ምንጭ]

Schomburg Center for Research in Black Culture / The New York Public Library / Astor, Lenox and Tilden Foundations

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ