የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 9/1 ገጽ 24-25
  • እህል ብሉ—እንጀራ ብሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እህል ብሉ—እንጀራ ብሉ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሕይወትን ዳቦ ቀምሰኸዋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • “ምን እንበላለን?”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረው ሕይወት​—ገበሬው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 9/1 ገጽ 24-25

የተስፋይቱ ምድር ገጽታዎች

እህል ብሉ—እንጀራ ብሉ

በአንድ ወቅት ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በቤት ሳሉ ብዙ ሕዝብ ወደ እነርሱ ስለመጡ “እህል መብላት እንኳን አቃታቸው።” (ማርቆስ 3:20) በሌላ ጊዜ ደግሞ ኢየሱስ “ምሳ ሊበላ” ወደ አንድ ፈሪሳዊ ቤት ገብቶ ነበር።(ሉቃስ 14:1) ይህን ስታነቡ ወደ አእምሮአችሁ የሚመጣው ምን ዓይነት እህል ወይም ምሳ ነው?

የጥንት እስራኤላውያን ቢሆኑ ኖሮ ይህን የመሰለ መግለጫ ሲያነቡ የሚያስቡት ስለ እንጀራ ነበር። ምክንያቱም “ምሳ መብላት” ወይም “እህል መብላት” የሚለው የዕብራይስጥና የግሪክኛ አገላለጽ ቃል በቃል “እንጀራ መብላት” ማለት ነበር። የእስራኤላውያን ዋነኛ ምግብ ከስንዴ ወይም ከገብስ የሚዘጋጅ እንጀራ ስለሆነ ስለ እህል መብላት ሲነሳ እንጀራ ስለመብላት ማሰባቸው ተገቢ ነበር።

በዛሬው ጊዜ ብዙ ሰዎች ስለ ዕብራውያን አበው የሚያስቡት የበግ እረኞች እንደሆኑ ሲሆን ስለ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ሲነሳ ደግሞ ዓሣ አጥማጆች እንደሆኑ ነው። በእርግጥ አንዳንዶቹ ዓሣ አጥማጆች ቢሆኑም ሁሉም ዓሣ አጥማጆች አልነበሩም። ስንዴ በብዙ ሰዎች ሕይወት ዋና ቦታ ነበረው። ከዘፍጥረት 26:12፤ 27:37፤ እና 37:7 መረዳት እንደምንችለው ይስሐቅና ያዕቆብ አንዳንድ ጊዜ ስንዴ ያመርቱ እንደነበር ግልጽ ነው። በኢየሱስ ዘመን በገሊላ ውስጥ እርሻ ዋናው መተዳደሪያ ሥራ ስለነበረ ሐዋርያት ከሆኑት መካከል አንዳንዶቹ የስንዴ አምራች ገበሬዎች ነበሩን?

በተስፋይቱ ምድር ስንዴ ማምረት በጣም የተስፋፋ ስለነበረና መጽሐፍ ቅዱስም በብዛት ስለሚጠቅሰው ከኢየሱስ ሐዋርያት መካከል አንዳንዶቹ ስንዴ አምራች ገበሬዎች ሊሆኑ ይችሉ ነበር። (ዘዳግም 8:7-9፤ 1 ሳሙኤል 6:13) የስንዴ አምራች ገበሬ መሆን ምን ዓይነት ሥራዎችን ያጠቃልል ነበር?

በጥቅምትና በኅዳር መጀመሪያ ላይ የሚጥለው ዝናብ መሬቱን ካለሰለሰው በኋላ የስንዴው ገበሬ ያርስና ዘሩን ይዘራል። የኋለኛው ዝናብ ሰብሉ እንዲበቅል ይረዳው ነበር፣ ከዚያም በሚያዝያና በግንቦት የበጋው ሙቀት ከመጀመሩ በፊት ስንዴው ደርሶ አዝመራው ይነጣል። የስንዴ ምርት በጣም የታወቀ ከመሆኑ የተነሳ የወራት አመልካች እንደሆነ ለማንበብ ትችላላችሁ። (ዘፍጥረት 30:14፤ መሳፍንት 15:1) በስተግራ የሚገኘው ፎቶግራፍ የተነሳው ከዓመቱ በየትኛው ወቅት እንደሆነ ለማወቅ ትችላላችሁን?a የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የገብስ እሸት የሸመጠጡበት ወቅት መቼ ነበረ?—ማቴዎስ 12:1

ስንዴ ማምረት ለገበሬዎች ከፍተኛ ድካም የሚጠይቅ ሥራ ነበር። ከታች ባለው ገጽ ላይ እንደምትመለከቱት አጫጆች ዛላውን በማጭድ አጭደው በነዶ በነዶ በማሰር ይከምሩታል። እርግጥ አንዳንድ ዛላዎች መሬት ላይ ሊወድቁ ይችሉ ነበር፤ ሩት ልትቃርም የቻለችው ለዚህ ነበር። (ሩት 2:2, 7, 23፤ ማርቆስ 4:28, 29) ቀጥሎ የስንዴው ነዶዎች ወደሚወቁበት እንደ ኦርና አውድማ ወዳሉ አውድማዎች ይወሰዳሉ። በኦርና አውድማ ላይ ምን ነገር ተፈጽሞአል? መጽሐፍ ቅዱስ “የአውድማ ዕቃና የበሬ ዕቃ” እንደነበረ ይጠቅሳል። (2 ሳሙኤል 24:18-22፤ 1 ዜና መዋዕል 21:23) የስንዴው ነዶዎች በጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ወይም ተረግጦ በተጠቀጠቀ መሬት ላይ ይዘረጋና በሬ ወይም ሌላ እንስሳ ስንዴውን እየዞረ እንዲረግጥ ይደረጋል። እንስሳው ከእንጨት ወይም ከሌላ ነገር የተሠራ የአውድማ ዕቃ ማለትም የመውቂያና የማበራያ መሣሪያ እንዲስብ ሊደረግ ይችላል።—ኢሳይያስ 41:15

ከዚያ ከላይ እንደሚታየው እህሉን በላይዳ ወይም በመንሽ ወደ አየር በመወርወር ለማዝራት ወይም ገለባውን ከፍሬው ለመለየት ዝግጁ ይሆናል። (ማቴዎስ 3:12) ገበሬው ቀኑ ነፋስ ሲል ወደ ምስቱ ላይ ለማዝራት ይመርጥ ይሆናል። እህሉ ከተሰበሰበና ከጠጠሮች ለመለየት ከተበጠረ በኋላ በጎተራ ለመከተት ወይም በጣም አስፈላጊ የሆነውን እንጀራ ለማዘጋጀት ዝግጁ ይሆናል።—ማቴዎስ 6:11

ከስንዴው እንጀራ የማዘጋጀት ተግባር የምታከናውኚ የቤት እመቤት ወይም ሚስት ብትሆኚ ኖሮ በየቀኑ እህሉን ለመፍጨት ወፍጮና መጅ በመጠቀም መገርደፍ ይኖርብሽ ነበር። ወይም ደግሞ ሣራ ሥጋ ለብሰው ለተገለጡት መላእክት “ቂጣ” ለመጋገር ወይም እሥራኤላውያን ለይሖዋ የእህል መስዋዕት ለማቅረብ ይጠቀሙበት እንደነበረው “መልካም ዱቄት” ለማዘጋጀት አልመሽ መፍጨት ያስፈልግሽ ነበር። (ዘፍጥረት 18:6፤ ዘጸአት 29:2፤ ዘሌዋውያን 2:1-5፤ ዘኁልቁ 28:12) ሣራ የስንዴ ዱቄቱን በውኃ ለውሳ ሊጥ አቡክታለች።

ከታች በስተግራ በኩል የሊጥ ሙልሙሎችና አንዱ ደግሞ እስኪበስል በስሱ ተጋግሮ ወይም ተጠፍጥፎ ሲጠብቅ ትመለከታላችሁ። እንዲህ ዓይነት ትላልቅና ክብ ቂጣዎች ከታች የምታዩአት ሴት እንደምታደርገው በድንጋይ ላይ ወይም በብረት ምጣዶች ላይ ሊጋገሩ ይችላሉ። ይህም ሣራ ለመላእክት እንግዶች ሊጡን ከለወሰች በኋላ ቀጥላ ምን እንዳደረገችና ከጥቂት ጊዜ በኋላም የሎጥ ቤተሰብ ያደረጉትን በዓይነ ሕሊናችሁ እንድታዩ ይረዳችኋልን? እንዲህ እናነባለን፦ “[መላእክቱ] ወደ እርሱ አቀኑ፣ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፣ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ።”—ዘፍጥረት 19:3

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ከ1992 የይሖዋ ምሥክሮች የቀን መቁጠሪያ ጋር አወዳድሩት።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[በገጽ 24 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[በገጽ 25 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[በገጽ 25 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Garo Nalbandian

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ