የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb18 የካቲት ገጽ 3
  • የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • “ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የክርስትና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው?
    ንቁ!—2007
  • አንድ እውነተኛ የክርስትና እምነት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
mwb18 የካቲት ገጽ 3

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 12-13

የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ

ኢየሱስ የስንዴውንና የእንክርዳዱን ምሳሌ የተናገረው የስንዴውን ክፍል ማለትም ቅቡዓን ክርስቲያኖችን ከመላው የሰው ዘር መካከል የሚሰበስበው እንዴትና መቼ እንደሆነ ለመጠቆም ነው፤ ስንዴው መዘራት የጀመረው በ33 ዓ.ም. ነው።

መዝራት የተጀመረበትን፣ የመከር ወቅት የጀመረበትንና ስንዴው ወደ ጎተራ የሚገባበትን ወቅት የሚያሳይ የጊዜ ሰሌዳ

13:24

‘አንድ ሰው በእርሻው ላይ ጥሩ ዘር ዘራ’

  • ዘሪው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ

  • የጥሩው ዘር መዘራት፦ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ቅዱስ መቀባት

  • እርሻው፦ የሰው ልጆች ዓለም

13:25

“ሰው ሁሉ ተኝቶ ሳለ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው ላይ እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ”

  • ጠላት፦ ዲያብሎስ

  • የሰዎቹ መተኛት፦ የሐዋርያት መሞት

13:30

“እስከ መከር ጊዜ ድረስ አብረው ይደጉ”

  • ስንዴው፦ ቅቡዓን ክርስቲያኖች

  • እንክርዳዱ፦ አስመሳይ ክርስቲያኖች

‘በመጀመሪያ እንክርዳዱን ሰብስቡ፤ ከዚያም ስንዴውን ሰብስቡ’

  • ባሪያዎቹ/አጫጆቹ፦ መላእክት

  • የእንክርዳዱ መሰብሰብ፦ የአስመሳይ ክርስቲያኖች ከቅቡዓን ክርስቲያኖች መለየት

  • ወደ ጎተራው ማስገባት፦ የቅቡዓን ክርስቲያኖች እንደገና በተቋቋመው ጉባኤ ውስጥ መሰብሰብ

የመከሩ ወቅት በጀመረበት ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያኖችን ከአስመሳይ ክርስቲያኖች ተለይተው እንዲታወቁ ያደረጋቸው ምንድን ነው?

የዚህን ምሳሌ ትርጉም መረዳቴ በግለሰብ ደረጃ የሚጠቅመኝ እንዴት ነው?

ይህን ታውቅ ነበር?

ስንዴውና እንክርዳዱ አብረው ሲያድጉ

እንክርዳድ መርዛማ እህል ሲሆን ይህ እህል በቡቃያነት ደረጃ ካለ ስንዴ ጋር በጣም ይመሳሰላል። ስንዴውና እንክርዳዱ አብረው ማደግ እንደጀመሩ የእንክርዳዱ ሥር ከስንዴው ሥር ጋር ስለሚጠላለፍ ስንዴውን አስቀርቶ እንክርዳዱን ብቻ መንቀል አይቻልም። እንክርዳዱ ካደገ በኋላ ግን በቀላሉ መለየትና ማስወገድ ይቻላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ