የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 4/15 ገጽ 28-30
  • የምትችለውን ያህል እየሠራህ ነውን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምትችለውን ያህል እየሠራህ ነውን?
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ልናደርግ የምንችለው መጠን ሊጨምር ይችላል
  • ሌሎችን በመርዳት ረገድ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ
  • በግል ቀርቦ በመርዳት አሳቢነት በማሳየት የተቻለንን ሁሉ ማድረግ
  • ያንተ አቅም የሚፈቅደውን ሁሉ አድርግ
  • “የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ራሳችንን ስንወስን የገባነውን ቃል “ዕለት ዕለት” መጠበቅ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ለይሖዋ ምርጥህን በመስጠት ተደሰት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 4/15 ገጽ 28-30

የምትችለውን ያህል እየሠራህ ነውን?

“የምችለውን ሁሉ ለማድረግ እሞክራለሁ።” ብዙ ጊዜ እንዲህ ከተባለ በኋላ “ግን” በማለት የተቻለው ሁሉ እንዳይደረግ የሚያግዱ ሰበቦች ይደረደራሉ። ለይሖዋ ስላደረግነው ውሳኔስ ምን ሊባል ይቻላል? አቅማችን በሚፈቅደው ሁሉ ይሖዋን ለማገልገል የገባነውን ቃል በመፈጸም ላይ ነንን?

ራስን መወሰን ማለት ‘ራስን ለአንድ መለኮታዊ አካል አምልኮ ወይም አገልግሎት ወይም ለአንድ ቅዱስ ሥራ ሙሉ በሙሉ መለየት’ ማለት ነው። ኢየሱስ ራስን ለይሖዋ መወሰን ማለት ምን እንደሆነ ሲያመለክት “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን፣ ይካድ መስቀሉንም [የመከራውንም እንጨት አዓት] ተሸክሞ ይከተለኝ” ብሎአል። (ማቴዎስ 16:​24) አንድ ራሱን የካደና ራሱን ለአምላክ የወሰነ ሰው በሕይወቱ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ጉዳይ መለኮታዊውን ፈቃድ መፈጸም ነው።

ራሳችንን የወሰንን ሕዝብ እንደመሆናችን መጠን ለውሳኔያችን እውነተኞች መሆንና አለመሆናችንን መመርመር ይገባናል። ጴጥሮስ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን “መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ። እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም” በማለት ራሳችንን መመርመር የሚገባን ለምን እንደሆነ አመልክቶአል። (2 ጴጥሮስ 1:​10) አዎ፣ ከፊት ይልቅ ብንተጋ ወይም የተቻለንን ሁሉ ብናደርግ መንፈሳዊ ውድቀት አይደርስብንም።

ልናደርግ የምንችለው መጠን ሊጨምር ይችላል

ራሳቸውን የወሰኑ የአምላክ አገልጋዮች በሙሉ ይሖዋን ለማስደሰት የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል። ይሁን እንጂ የአምላክን ፈቃድ በመፈጸም ረገድ ለማድረግ የምንችለው ሥራ መጠን ሊያድግ ይችላል። አንድ የሦስት ዓመት ልጅ እናቱን ለመርዳት መልእክት ከማድረስ የበለጠ ነገር ሊያደርግ አይችልም ይሆናል። እያደገ ሲሄድ ግን ከዚህ የበለጠ ሥራ ሊሠራ ይችላል። መንፈሳዊ ዕድገታችንም ከዚህ የተለየ አይደለም። ከዚህ በፊት የምችለውን ሁሉ አድርጌአለሁ ለማለት ያስችለን የነበረው የሥራ መጠን ዛሬ እንዲህ ለማለት አያስችለን ይሆናል። ለይሖዋ የበለጠ ለመሥራት እንገፋፋለን።

ለይሖዋ ያለን አድናቆት እየጨመረ ሲሄድ የበለጠ ለመሥራት ያለን ፈቃደኛነት ይነሳሳል። ይሖዋ ላደረገልን ነገሮች ያለን አድናቆት የሚጨምረው ቃሉ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን በግል በማጥናት ነው። ለምሳሌ ያህል ይሖዋ የሰው ልጆችን ከኃጢአት ነፃ ለማውጣት ልጁን እንዴት እንደላከ በጥሞና ስንመረምርና ስናሰላስል የቤዛው ምንጭ የሆነውን አምላክ ለማገልገል እንነሳሳለን። (ዮሐንስ 3:​16, 17፤ 1 ዮሐንስ 4:​9–11) ‘የይሖዋን ጥሩነት በይበልጥ በቀመስን’ መጠን ልባችን እርሱን ለማገልገል ይገፋፋል። — መዝሙር 34:​8

ጀተር የተባለች የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ይህን ተገንዝባለች። የምታጠናውን ነገር በጥልቀት ለመመርመር እንድትችል በቤትዋ ውስጥ አንድ ትንሽ ክፍል ለዚህ ዓላማ መደበች። ክፍሉን ምርምር በምታደርግበት ጊዜ ሙሉ ትኩረት እንዲኖራት በሚያስችል መንገድ አደራጀች። የመጠበቂያ ግንብ ጽሑፎችን ማውጫዎች እና የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ጥራዞችን በቀላሉ ልትደርስ በምትችልበት መደርደሪያ ላይ አስቀመጠች። “በጣም የሚያስደስት ትምህርት ቆፍሬ ሳገኝ ይህን ትምህርት ለሌሎች ለማካፈል እቸኩላለሁ” ብላለች።

ይሁን እንጂ አንድ ሰው አልፎ አልፎ ጥሩ ምግብ መመገቡ በተለመዱት የምግብ ሰዓቶች በየቀኑ ሳይመገብ ሊኖር እንደማያስችለው ሁሉ አንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት መመርመር በየቀኑ መንፈሳዊ ምግብ የመመገብን አስፈላጊነት አያስቀርም። ሩት የዚህን አስፈላጊነት ተገንዝባለች። ልታስታውስ ከምትችልበት ጊዜ አንስቶ ቤተሰብዋ በእያንዳንዱ ጠዋትና ምሽት ከምግብ በኋላ አንድ ላይ ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስ ያነባል። አሁንም 81 ዓመት የሆናትና በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከ60 ዓመት በላይ ያሳለፈች ብትሆንም ሁልጊዜ በ12 ሰዓት ከእንቅልፍዋ ተነስታ መጽሐፍ ቅዱስ ታነባለች። ሩት የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት እንደደረሳት ጊዜዋን ገዝታ እነዚህን መጽሔቶች ታነባለች። አንድን ርዕሰ ትምህርት በጉባኤ ከማጥናትዋ በፊት ቢያንስ ሦስት ወይም አራት ጊዜ ደጋግማ ታነባለች። “በእምነት ጠንካራ ሆኖ ለመኖር የአምላክን ቃል መመገብ ያስፈልጋል” ትላለች። በተጨማሪም ለበርካታ ዓመታት በሚሲዮናዊነት አገልግሎት እንድትጸና ረድቶአታል።

ሌሎችን በመርዳት ረገድ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ

የአምላክን ቃል አዘውትረን በጥልቀት ስናጠና አምላክን ለማገልገል ያለን ቅንዓት ያድጋል። የበለጠ እንድንሠራ የሚገፋፋ ኃይል በውስጣችን ይፈጠራል። (ከኤርምያስ 20:​9 ጋር አወዳድር።) እንዲህ ያለው ቅንዓት ሂሮሂሳ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ እንዲፈጽም ገፋፍቶታል። (2 ጢሞቴዎስ 4:​5) እሱንና አራት ታናናሽ እህቶቹንና ወንድሞቹን ያሳደገችው እናቱ ብቻዋን ሆና ነው። ሂሮሂሳ ገና በአሥራዎቹ ዓመታት ዕድሜ ውስጥ ሳለ ጀምሮ ሌሊት በዘጠኝ ሰዓት ተነስቶ ጋዜጣ በማደል ቤተሰቡን ይረዳል። ለሌሎች ሰዎች ስለ ይሖዋ በመናገር የበለጠ ለመሥራት ስለፈለገ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ወይም አቅኚ ለመሆን አመለከተ። በወጣትነት ዕድሜው ሌሎች ሰዎች ይሖዋን በማወደስ ረገድ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ለመርዳት በመቻሉ በጣም ተደስቶአል።

ሌሎችን በመርዳት ረገድ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ በአገልግሎታችን ውጤታማ መሆንን ይጨምራል። አንድ ጊዜ ኢየሱስ “ይህን ብታውቁ፣ ብታደርጉትም ብፁዓን [ደስተኞች አዓት] ናችሁ” በማለት ደቀ መዛሙርቱን አበረታቶአል። (ዮሐንስ 13:​17) የይሖዋ ድርጅት አገልግሎታችንን ስለማሻሻል የሚሰጠውን ሐሳብ በሥራ ላይ በማዋል ረገድ ናኦሚ ጥሩ ምሳሌ ትሆናለች። ከቤት ወደ ቤት በምትሄድበት ጊዜ ከዚህ በፊት የማታውቃቸውን ሰዎች ማነጋገር ያስቸግራት ነበር። ብዙ ጊዜ በራፉ ላይ እንደቆመች የምትናገረው ይጠፋት ነበር። በጉባኤዋ ያሉ ሽማግሌዎች ምክንያቱን ማስረዳት በተባለው መጽሐፍ ውስጥ “በመስክ አገልግሎት የሚያገለግሉ መግቢያዎች” በሚለው ርዕስ ሥር የቀረቡትን ሐሳቦች ሥራ ላይ እንድታውል መከሩአት።a “ቤተሰብ/ልጆች” በሚለው ርዕስ ሥር የተገለጸውን መግቢያ በቃል ካጠናች በኋላ ደጋግማ ተለማመደችው። ይህን በማድረግዋ በ30ዎቹ ዓመታት ዕድሜ ውስጥ ከምትገኝ የቤት እመቤት ጋር ውይይት ለመጀመር ቻለች። ይህች ሴት ናኦሚ ተመላልሶ መጠየቅ እስክታደርግላት ጊዜ እንኳን ሳትቆይ ወደ መንግሥት አዳራሹ መጣች። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተጀመረላት። አሁን ይህች የቤት እመቤትና ባለቤትዋ የተጠመቁ ክርስቲያኖች ሆነው ከልጆቻቸው ጋር በጥሩ የቤተሰብ ሕይወት በመደሰት ላይ ይገኛሉ።

በግል ቀርቦ በመርዳት አሳቢነት በማሳየት የተቻለንን ሁሉ ማድረግ

በተጨማሪም “በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ” ያለውን ሐዋርያው ጳውሎስን ለመምሰል እንችላለን። — 1 ቆሮንቶስ 9:​22, 23

ሃትሱሚ ይህን የመሰለውን ዝንባሌ አሳይታለች። በሕዝባዊ አገልግሎትዋ ያገኘቻት አንዲት ሴት በቤትዋ በራፍ በሚገኘው መነጋገሪያ አማካኝነት ጊዜ ስለሌላት ልታነጋግራት እንደማትችል በትህትና ነገረቻት። የሴትዬዋ አነጋገር ጨዋነት የተሞላ ስለነበረ ሃትሱሚ ደጋግማ ጠየቀቻት። ሴትዬዋ ግን አንድም ጊዜ ከቤትዋ ወጥታ ከሃትሱሚ ጋር ሳትገናኝ በመነጋገሪያው አማካኝነት ብቻ ትመልስላት ነበር። ይህ ሁኔታ ሁለት ዓመት ተኩል ለሚያክል ጊዜ ቀጠለ።

አንድ ቀን ሃትሱሚ የምትሄድበትን ጊዜ ቀይራ ከሰዓት በኋላ መሸት ሲል ሄደች። መልስ የሚሰጣት ሰው አልነበረም። ተመልሳ ልትሄድ ስትነሳ ከኋላዋ “ማነሽ?” የሚል ድምፅ ሰማች። ሴትዬዋ ወደ ቤትዋ መመለስዋ ነበር። የሃትሱሚን ስም ስትሰማ ወዲያው “ስትጠይቂኝ የነበርሽው አንቺ ነሽ ማለት ነው! ይህን ያህል ስላሰብሽልኝ አመሰግንሻለሁ” አለቻት። ሴትዬዋ ለሃትሱሚ ያልከፈተችላት በሌላ አካባቢ ትኖር በነበረበት ጊዜ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ታደርግ የነበረውን ጥናት ስላቋረጠች አፍራ እንደሆነ ነገረቻት። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደገና ተጀመረላትና ጥሩ እድገት አሳየች። ከቤት ወደ ቤት በምናደርገው አገልግሎት ለምናገኛቸው ሰዎች ይህን የመሰለ አሳቢነት እናሳያ ለንን?

ያንተ አቅም የሚፈቅደውን ሁሉ አድርግ

ይሖዋ በሚቻለን ሁሉ እርሱን ለማገልገል በምናደርገው ጥረት ይደሰታል። እርሱ ልጁ ሥጦታ ይዞለት እንደሚመጣ አባት ነው። ልጁ የሚያመጣው ሥጦታ እንደ ልጁ ዕድሜና አቅም በየጊዜው የተለያየ ሊሆን ይችላል። አባትዬው ልጁ ከልቡ ተነሳስቶ ያመጣለትን ሥጦታ በደስታ እንደሚቀበል ሁሉ ይሖዋም መንፈሳዊ እድገታችን በሚፈቅድልን መጠን በሙሉ ልባችን የምናቀርብለትን አገልግሎት በደስታ ይቀበላል።

እርግጥ እኛ ማድረግ የምንችለውን ሌሎች ሊያደርጉት ከሚችሉት ጋር ማወዳደር ምንም ጥቅም የለውም። ጳውሎስ እንዳለው እያንዳንዱ ሰው የሚያገኘው “ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን” ነው። (ገላትያ 6:​4) “ይህን አየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ [የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ አዓት ]” የሚለውን የሐዋርያው ጴጥሮስ ምክር በመከተል እንቀጥል። — 2 ጴጥሮስ 3:​14

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር የታተመ።

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የመስክ አገልግሎትን ስለማሻሻል የሚሰጡትን ሐሳቦች ሥራ ላይ በማዋል ረገድ የምትችለውን ሁሉ እያደረግህ ነውን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ