የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 6/97 ገጽ 1
  • “የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ”
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የምትችለውን ያህል እየሠራህ ነውን?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • “ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል!”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ለይሖዋ ምርጥህን በመስጠት ተደሰት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ እየፈጸምክ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1997
km 6/97 ገጽ 1

“የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ”

1 ራሳችንን ለይሖዋ በወሰንን ጊዜ ምርጣችንን ልንሰጠው ቃል ገብተናል። ሐዋርያው ጴጥሮስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች በይሖዋ ፊት ያላቸውን አቋም ጠብቀው ለመኖር የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ማበረታታቱ ተገቢ ነበር። (2 ጴ⁠ጥ. 1:​10 NW ) ዛሬም፣ ለይሖዋ በምናቀርበው አገልግሎት እርሱን ለማስደሰት የተቻለንን ሁሉ ለማድረግ እንደምንፈልግ የተረጋገጠ ነው። ይህ ምን ማድረግን ይጠይቃል? ከይሖዋ ጋር ያለን ዝምድና እያደገ ሲሄድና ስላደረገልን ነገሮች ሁሉ ስናሰላስል በእርሱ አገልግሎት የተቻለንን ሁሉ እንድናደርግ ልባችን ይገፋፋናል። የአገልግሎታችንን ጥራት ለማሻሻልና የሚቻል ሲሆንም መጠኑን ከፍ ለማድረግ እንፈልጋለን።​— መዝ. 34:​8፤ 2 ጢ⁠ሞ. 2:​15

2 በአገልግሎት ብዙ ለመሥራት የፈለገ አንድ ወጣት ወንድም የአምላክን ቃል አዘውትሮ ማጥናት ለይሖዋ ያለውን አድናቆት እንደጨመረለትና ቅንዓቱን እንዳቀጣጠለለት ተገንዝቧል። ይህም አቅኚ ሆኖ ለማገልገል እንዲያመለክት አነሳስቶታል። የማታውቃቸውን ሰዎች ለማነጋገር ትቸገር የነበረች አንዲት እህት ማመራመር በተባለው መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ መግቢያዎች በመጠቀሟ ወዲያው በአገልግሎቷ ከፍተኛ ስኬት ማግኘት ጀመረች። ይህች እህት እውነትን ለተቀበሉ አንድ ባልና ሚስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት ችላለች።

3 ማድረግ በምትችሉት ነገር ተደሰቱ:- አንዳንዶቻችን እንደ ጤና መታወክ፣ የቤተሰብ ተቃውሞ፣ ድህነት ወይም ደግሞ በአገልግሎት ክልላችን ያሉት ሰዎች የሚያሳዩትን እምቢተኝነት የመሳሰሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይገጥሙናል። በእነዚህ መጨረሻ ቀኖች በሰፊው የሚታዩ ሌሎች ችግሮችም ለአገልግሎታችን ጋሬጣ ሊሆኑብን ይችላሉ። (ሉቃስ 21:​34 የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ፤ 2 ጢ⁠ሞ. 3:​1) ታዲያ ይህ ራሳችንን ለይሖዋ ስንወስን የገባነውን ቃል ሳንፈጽም ቀርተናል ማለት ነውን? የምናገለግለው የአቅማችንን ያህል ከሆነ እንደዚያ ማለት አይሆንም።

4 ሌሎች ማከናወን በሚችሉት ነገር ላይ ተመስርተን በራሳችን ላይ መፍረድ ጥበብ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ቅዱሳን ጽሑፎች ‘እያንዳንዳችን የራሳችንን ሥራ እንድንፈትን’ ያበረታቱናል። በግላችን የተቻለንን ያህል ሙሉ በሙሉ ራሳችንን ማቅረባችን ይሖዋን ደስ ከማሰኘቱም ሌላ ለእኛም ‘የደስታ ምንጭ’ ይሆንልናል።​—ገላ. 6:​4፤ ቆላ. 3:​23, 24

5 ‘ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆነን በሰላም በእርሱ ዘንድ እንድንገኝ የቻልነውን ሁሉ እንድናደርግ’ የሚናገሩትን የጴጥሮስን ቃላት እንከተል። (2 ጴ⁠ጥ. 3:​14) ይህ ዓይነቱ መንፈስ ስጋት እንዳይሰማንና ይሖዋ ብቻ ሊሰጠን የሚችለውን የአእምሮ ሰላም እንድናገኝ ያስችለናል።​—መዝ. 4:8

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ