የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 8/1 ገጽ 31
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጥምቁ ዮሐንስ ማን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • መጥምቁ ዮሐንስ በእርግጥ በሕይወት የኖረ ሰው ነው?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ጥያቄ አቀረበ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ኢየሱስ እየጨመረ ዮሐንስ ግን እየቀነሰ ሄደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 8/1 ገጽ 31

የአንባብያን ጥያቄዎች

ኢየሱስን ያጠመቀው ዮሐንስ መጠራት ያለበት “ዮሐንስ መጥምቁ” ተብሎ ነው ወይስ “አጥማቂው ዮሐንስ”?

ሁለቱም መጠሪያዎች ትክክለኛ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ ያላቸው ናቸው።

ዮሐንስ “የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ [ለይሖዋ አዓት] እንዲያሰናዳ” የተላከ ነበር፤ ይህንንም “ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት” በመስበክ አከናውኗል። (ሉቃስ 1:​17፤ 3:​3) ሐዋርያው ማቴዎስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ ብሎ በይሁዳ ምድረበዳ እየሰበከ መጣ። . . . ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ . . . ወደ እርሱ ይመጡ ነበር። ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።” — ማቴዎስ 3:​1–6

ማቴዎስ ዮሐንስን “መጥምቁ” ብሎ እንደጠራው ልብ በል። ከሁኔታዎቹ መረዳት እንደሚቻለው ማቴዎስ ታሪኩን ያዘጋጀው ለአይሁዳውያን እንደሚስማማ አድርጎ ስለነበር አይሁዳውያኑ “መጥምቁ” ማን መሆኑን እንደሚያውቁት በማሰብ መሆን አለበት። “መጥምቁ” የሚለውን የተጠቀመበት እንደ ሌላው ስሙ አድርጎ ነው። የሄሮድስ አገልጋዮች እንዳደረጉት ሁሉ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ “መጥምቁ ዮሐንስ” የሚለውን ተጠቅመዋል።a — ማቴዎስ 11:​11, 12፤ 14:​2፤ 16:​14

ደቀ መዝሙሩ ማርቆስም “መጥምቁ ዮሐንስ” የሚለው በተመሳሳይ የተሠራበት መሆኑን ይዘግባል። (ማርቆስ 6:​25፤ 8:​28) ነገር ግን ማርቆስ ዮሐንስን ሲያስተዋውቅ “አጥማቂው ዮሐንስ” ብሎ ጠርቶታል። (ማርቆስ 1:​4 1980 ትርጉም) በማርቆስ 1:​4 ላይ የሚገኘው የግሪክኛ ቃል በሌሎች ቁጥሮች ላይ ከሚገኘው በጥቂቱ ይለያል። ማርቆስ 1:​4 “የሚያጠምቀው” ተብሎ ሊተረጎም ይችል ይሆናል። ማርቆስ ያጐላው ዮሐንስ የሚሠራውን ሥራ ነበር፤ የማጥመቅ ሥራ የሚሠራ ማለትም አጥማቂ ነበር።

ይሁን እንጂ እነዚህ የዮሐንስ መጠሪያዎች የተለያየ አገባብ አላቸው ብለን ማሰብ ያለብን አይመስልም። በማርቆስ 6:​24, 25 ላይ ስለ ሰሎሜ እንዲህ እናነባለን:- “ወጥታም ለእናትዋ:- ምን ልለምነው? አለች። እርስዋም:- የመጥምቁን የዮሐንስን [የአጥማቂውን የዮሐንስን አዓት] ራስ አለች። ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ ብላ ለመነችው።” ሁለቱም መጠሪያዎች በተወራራሽነት ተሠርቶባቸዋል።

አንዳንድ ሰዎች “መጥምቁ” /The Baptist/ የሚለውን በመዝገበ ቃላት ላይ ባለው ሁለተኛ ትርጉሙ ይረዱታል። ይኸውም “በጉባኤ በመደራጀታቸው እና አማኞችን በማጥለቅ በሚያካሂዱት ጥምቀት ተለይተው የሚታወቁ ወንጌላውያን ከሆኑት የፕሮቴስታንት ቅርንጫፎች የአንዱ አባል ወይም ተከታይ የሆነ” የሚል ነው። ዮሐንስ ግን እንደዚህ አልነበረም።

እንግዲያው “መጥምቁ ዮሐንስ” እና “አጥማቂው ዮሐንስ” የሚሉት ሁለቱም መጠሪያዎች ትክክለኛ እና ተገቢ ናቸው።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a የአይሁዳውያን ታሪክ ጸሐፊ የነበረው ፍላቪየስ ጆሴፈስ ዮሐንስ፣ ሌላው ስሙ “መጥምቁ” በማለት ጽፏል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ