የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w93 11/1 ገጽ 24-25
  • የገሊላን ባሕር መጥታችሁ ጎብኙ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የገሊላን ባሕር መጥታችሁ ጎብኙ!
  • መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሀ7-መ የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት አበይት ክንውኖች—ኢየሱስ በገሊላ ያከናወነው ታላቅ አገልግሎት (ክፍል 2)
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አሰኘው
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ጌንሳሬጥ—‘አስደናቂና ውብ’ ሥፍራ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
መጠበቂያ ግንብ—1993
w93 11/1 ገጽ 24-25

የተስፋይቱ ምድር ገጽታዎች

የገሊላን ባሕር መጥታችሁ ጎብኙ!

በመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎች አእምሮ ውስጥ የገሊላን ባሕር ያህል ቶሎ የሚታወስ ሌላ ቦታ ሊኖር አይችልም። ነገር ግን ዓይኖችህን ጨፍነህ በዚህ ዘወትር ትኩስ ውኃ በሚያገኘው ባሕር ውስጥ የዮርዳኖስ ወንዝ በየት ገብቶ በየት እንደሚወጣ ወይም እንደ ቅፍርናሆምና ጥብርያዶስ ያሉ ቁልፍ ቦታዎች የት ቦታ ላይ እንደሚገኙ መገመት ትችላለህን?

ከዚህ በታች ያለውን ከአየር ላይ የተነሣውን አካባቢ ተመልከትና ከተሰጡት መግለጫ ቁጥሮች ጋር እያስተያየህ ለማጥናት በቂ ጊዜ መድብ። ቁጥር ከተሰጣቸው ቦታዎች ውስጥ ስንቶቹን ለይተህ አወቅሃቸው? ብዙዎቹን ባወቅሃቸው መጠን በዚያው ልክ ያነበብከው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይበልጥ ግልጽና ትርጉም ያለው ይሆንልሃል። ይህን ለማግኘት አጠር ላለ እውቀት ሰጪ ጉብኝት አብረኸን ተጓዝ።

ይህ ከአየር ላይ የተነሣ ፎቶግራፍ ወደ ሰሜናዊ ምሥራቅ የሚመለከት አካባቢ ነው። ከቁጥር 1 እንጀምር። ይህ የትኛው የባሕሩ ክፍል ነው? አዎን፣ በሰማርያና በጊልያድ መካከል አቋርጦ ወደ ሙት ባሕር ውስጥ ለመግባት የዮርዳኖስ ወንዝ የሚወጣበት ደቡባዊ ጫፍ ነው። በስተ ግራ በኩል የዚህን ባሕር ጫፍ ቀረብ ብለህ ልታየው ትችላለህ። እንዲሁም ይህንን ቦታ በ1993 የይሖዋ ምስክሮች የቀን መቁጠሪያ ላይም ማየት ትችላለህ።

የገሊላ ባሕር ከሜዲትራኒያን ባሕር 200 ሜትር ያህል ዝቅ ብሎ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ይገኛል። ከአየር ላይ የተነሣውን ፎቶግራፍ እየተመለከትክ ስትመረምር ከምሥራቃዊው የባሕሩ ዳርቻ ጀምሮ ከፍ ብሎ የሚታዩትን ተራራዎች ልብ በላቸው። (ቁጥር 7 አካባቢ) በአቅራቢያው ወይም በምዕራቡ የባሕር ዳርቻ ኮረብታዎችና ተራሮች መገኘታቸው ባሕሩ ጎድጎድ ባለ ቦታ ላይ መቀመጡንና ባሕሩም 21 ኪሎ ሜትር ርዝማኔና 12 ኪሎ ሜትር ስፋት እንዳለው ያጎላልናል። በባሕሩ ዳርቻ ለመንደሮችና እንደ ጥብርያዶስ ላሉ ከተሞችም ጭምር የሚበቃ ሰፊ ቦታ ነበረው። (ቁጥር 2) በጥብርያዶስ የነበሩ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ 5,000 ሰዎችን በተአምር ወደ መገበበት ቦታ በታንኳ ተሻግረው መምጣታቸውን አስታውስ። — ዮሐንስ 6:​1, 10, 17, 23

ከጥብርያዶስ ተነሥተህ በባሕሩ ጥግ ብትጓዝ በጣም ለም የሆነውን የጌንሳሬጥን አካባቢ ታገኛለህ። (ቁጥር 3)a እዚህ ቦታ ላይ ኢየሱስ የተራራውን ስብከት ያደረገበትና እዚህ በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ጴጥሮስንና ሌሎቹን ሦስት ወንዶችን “ሰዎችን አጥማጆች” እንዲሆኑ የጠራቸው በአቅራቢያው ከሚገኘው የባሕር ዳርቻ መሆን አለበት። (ማቴዎስ 4:​18–22) ጉዞው ሲቀጥል የኢየሱስ የሥራ እንቅስቃሴ ማዕከል ወደሆነችውና እንዲያውም “የገዛ ከተማው” ተብላ ወደ ተጠራችው ቅፍርናሆም (ቁጥር 4) ትመጣለህ። (ማቴዎስ 4:​13–17፤ 9:​1, 9–11፤ ሉቃስ 4:​16, 23, 31, 38–41) ባሕሩን ዞረህ ወደ ምሥራቅ ጉዞህን ስትቀጥል ላይኛው የዮርዳኖስ ወንዝ ወደ ባሕሩ የሚገባበትን ቦታ ታቋርጣለህ። (ቁጥር 5) (ከታች ያለውን ተመልከት) ከዚያም ወደ ቤተሳይዳ አካባቢ ትመጣለህ። (ቁጥር 6)

እነዚህን ጥቂት ቦታዎች ብቻ በመጠቀም ስለ ገሊላ ባሕር ያገኘኸው እውቀት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን እንድትከታተልና በዓይነ ሕሊናህ እንድትመለከት እንዴት ሊረዳህ እንደሚችል ማስረዳት እንችላለን። ኢየሱስ በቤተሳይዳ አካባቢ 5,000 ሰዎችን ከመገበና ሕዝቡም ንጉሥ ሊያደርጉት ሙከራ ካደረጉ በኋላ ሐዋርያቱን ወደ ቅፍርናሆም በታንኳ ላካቸው። በጉዞአቸው ላይ እያሉ አውሎ ነፋስ ከተራራው ወረደባቸውና ሐዋርያቱን በፍርሃት እንዲዋጡ ያደረገ ማዕበል አስነሣ። ነገር ግን ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣና ነፋሱን ጸጥ አሰኘላቸው ወደ ጌንሳሬጥም በደህና እንዲደርሱ አስቻላቸው። (ማቴዎስ 14:​13–34) ከጥብርያዶስ የመጡት ሰዎች አሁንም በድጋሚ ወደ ቅፍርናሆም ተሻገሩ። — ዮሐንስ 6:​15, 23, 24

የምሥራቃዊውን የባሕር ዳርቻ ይዘህ መጓዝህን ስትቀጥል ወደ “ጌርጌሴኖን አገር” ትደርሳለህ። ኢየሱስ እዚህ ቦታ ከሁለት ሰዎች ውስጥ አጋንንት እንዳወጣ ትዝ ይበልህ። እነዚህ መናፍስት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ወደ አሳማዎች መንጋ በመግባታቸው ከአፋፉ ወደ ባሕሩ ውስጥ ገቡ። ከእነዚህ ሰዎች አንዱ በአቅራቢያው በሚገኘው አሥር ከተማ በሚባል አገር ሄዶ ለግሪክኛ ተናጋሪዎች ምስክርነት ሰጠ። ኢየሱስ ወደዚህ ቦታ የሄደውም ሆነ የተመለሰው የገሊላን ባሕር በታንኳ በማቋረጥ ነበር። — ማቴዎስ 8:​28 እስከ 9:​1፤ ማርቆስ 5:​1–21

ጉብኝትህን ወደ ባሕሩ ታችኛ ጫፍ ቀጥለህ ስታጠናቅቅ ኮረብቶችን አቋርጦ በመምጣት ለታችኛው የዮርዳኖስ ወንዝ ብዙ ውኃ በሚያመጣለት ትልቅ ወንዝ (ያምሩክ ተብሎ ይጠራል) አጠገብ ታልፋለህ።

መጽሐፍ ቅዱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ስለተከናወኑ ነገሮች ለምሳሌ ከትንሣኤው በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያት ዓሣ ሲያጠምዱ የተገለጠበትን ቦታ ለይቶ አይጠቅስም። (ከታች) ቅፍርናሆም አጠገብ ነበር ብለህ ታስባለህን? ያም ሆነ ይህ ስለዚህ ልዩ ባሕር ያገኘኸው እውቀት ቦታው እዚህ አካባቢ ሊሆን እንደሚችል በዓይነ ሕሊናህ እንደትመለከተው ይረዳሃል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a “ጌንሳሬጥ — ‘አስደናቂና ውብ’ ስፍራ” የሚለውን በጥር 1, 1992 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን ርዕስ ተመልከት።

[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

1

2

3

4

5

6

7

ሰ

ደ

ም

ምዕ.

[ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[ምንጭ]

Garo Nalbandian

[ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ