የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 2/15 ገጽ 3-4
  • አምላክ ዕድላችንን አስቀድሞ ወስኖታልን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ዕድላችንን አስቀድሞ ወስኖታልን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል የሚለው አባባል ትርጉም
  • ዕድል ተወስኗል የሚለውን እምነት የጠነሰሰው አውጉስቲን
  • የአውጉስቲን ወራሾች
  • ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል ወይስ ነፃ ምርጫ?
  • ዕድል ተወስኗል የሚለው እምነት ከአምላክ ፍቅር ጋር ሊስማማ ይችላልን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የወደፊት ዕጣችን አስቀድሞ ተጽፏልን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ዕድልህ አስቀድሞ ተወስኗል?
    ንቁ!—2007
  • ካልቪኒዝም በ500 ዓመት ውስጥ ምን ማከናወን ችሏል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 2/15 ገጽ 3-4

አምላክ ዕድላችንን አስቀድሞ ወስኖታልን?

“ብዙውን ጊዜ የተዛባ ትርጉም የሚሰጠው ዕድል ተወስኗል የሚለው አነጋገር ጭራሹኑ ባይሠራበት ኖሮ በሰው አእምሮ ውስጥ የሚጉላሉ እጅግ ብዙ ጥያቄዎች በተወገዱ ነበር።” “ዕድል ተወስኗል” በሚለው አባባል ተጠቅመህ ወይም ሰዎች ሲጠቀሙበት ሰምተህ ከሆነ ለምን እንዲህ እንደተባለ ገርሞህ ይሆናል።

በቅርቡ በወጣው ቴኦ በተባለው የፈረንሳይ ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያ መሠረት “ዕድል ተወስኗል” የሚለውን አባባል ባንጠቀምበት የተሻለ ነው። ሌላ መጽሐፍ ደግሞ “ዛሬ በአብዛኞቹ ፕሮቴስታንቶች ዘንድ እንኳ ዕድል ተወስኗል የሚለው እምነት በሃይማኖታዊ ክርክር ውስጥ ከቁብ የሚቆጠር አይመስልም” ብሏል።

የሆነ ሆኖ ዕድል ተወስኗል ስለሚለው እምነት የሚነሳው ጥያቄ በታሪክ ውስጥ የብዙ ሰዎችን አእምሮ ሲከነክን ቆይቷል። ዕድል ተወስኗል የሚለው እምነት ተሃድሶን ላስከተለው ክርክር ዋና ፍሬ ነገር የነበረ ሲሆን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንም ጭምር ለአሥርተ ዓመታት የጋለ ክርክር የሚደረግበት ርዕስ ነበር። ዛሬ አከራካሪነቱ ቢቀንስም እስካሁን ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል። ዕጣው አስቀድሞ ተወስኖ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ የማይፈልግ ማን አለ?

ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል የሚለው አባባል ትርጉም

“ዕድል ተወስኗል” የሚለው ሐረግ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ምን ትርጉም አለው? ዲክሲዮናር ደ ቴኦሎዢ ካቶሊክ የተባለው መዝገበ ቃላት ዕድል ተወስኗል የሚለው እምነት “አምላክ በስም የተጠቀሱ ሰዎችን ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራበት ዕቅድ” እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል። የተመረጡት ማለትም “በስም የተጠቀሱት” ሐዋርያው ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። . . . አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” ብሎ የገለጻቸው ናቸው ተብሎ በሰፊው ይታሰባል።—ሮሜ 8:28–30

አንዳንድ ሰዎች ከመወለዳቸው በፊት እንኳ ኢየሱስ በሰማይ ባለው ክብር እንዲካፈሉ በአምላክ እንደተመረጡ ይታመናል። ይህም አምላክ ሊያድን የሚፈልገውን በራሱ ውሳኔ ብቻ ይመርጣል ወይስ የአምላክን ስጦታ ለማግኘትና ይዞ ለመቆየት ሰዎች ነፃ ምርጫና የሚያበረክቱት ድርሻ አላቸው? ወደሚለው መቋጫ የሌለው ውዝግብ ወዳስከተለው ጥያቄ ይመራል።

ዕድል ተወስኗል የሚለውን እምነት የጠነሰሰው አውጉስቲን

ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቀደም ብለው ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል ስለሚለው እምነት ቢጽፉም ለካቶሊክም ሆነ ለፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ትምህርቱን የጠነሰሰው አብዛኛውን ጊዜ አውጉስቲን (354–430 እዘአ የኖረ) እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል። እንደ አውጉስቲን አባባል ከሆነ አምላክ ዘላለማዊ በረከት የሚቀበሉትን ጻድቃን ከብዙ ጊዜ በፊት ወስኗል። በሌላ አንጻር የቃሉ ትክክለኛ ትርጉም እንደሚያሳየው አምላክ ጻድቃን ያልሆኑትን ሰዎች ዕድል አስቀድሞ ባይወስነውም እንኳ ለኃጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ። የአውጉስቲን ማብራሪያ ለነፃ ምርጫ ትንሽ ቀዳዳ በመተዉ ለብዙ እሰጥ አገባ መንገድ ከፍቷል።

የአውጉስቲን ወራሾች

ዕድል ተወስኗል የሚለው እምነትና ነፃ ምርጫ ያስከተለው ንትርክ በመካከለኛው ዘመን በየጊዜው ሳያሰልስ ይቀሰቀስ የነበረ ሲሆን በዘመነ ተሃድሶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። እንደ ሉተር አመለካከት የእያንዳንዱ ሰው ዕድል ተወስኗል የሚለው እምነት አምላክ የተመረጡትን ሰዎች የወደፊት መልካም ሥራ ወይም ተግባር አስቀድሞ ሳይመለከት የሚያደርገው ነፃ ምርጫ ነው። ዕድል ተወስኗል የሚለው እምነት ለአንዳንዶች ዘላለማዊ መዳን ሲሆን ለሌሎች ደግሞ ዘላለማዊ ፍርድ ነው በማለት ካልቪን ሁለት ገጽታዎች ያሉት ሐሳብ በማቅረብ ይበልጥ መሠረታዊ ወደ ሆነ መደምደሚያ ደርሷል። ካልቪንም ቢሆን የአምላክ ምርጫ በፍርደ ገምድልነት የሚደረግ እንዲያውም ግራ የሚያጋባ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል።

ዕድል ተወስኗል ስለሚለው እምነትና ከዚህ ጋር የሚዛመደው አምላክ ሰዎችን ለማዳንና ጻድቅነታቸውን ለመግለጽ የሚጠቀምበትን መንገድ ለማመልከት አብያተ ክርስቲያናት የሚጠቀሙበት “ጸጋ” ስለሚለው ቃል የተነሳው ክርክር ካቴድራሉ ካልተስማማበት በቀር ምንም ነገር ማሰራጨት እንደማይቻል በ1611 ሲወሰን ጉዳዩ ይበልጥ እየገነነ መጣ። የአውጉስቲን ትምህርቶች በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በ17ኛውና በ18ኛዎቹ መቶ ዘመናት ከነበሩት የፈረንሳይ ጃንሰኒስቶች ጠንካራ ድጋፍ አግኝቶ ነበር። ጃንሰኒስቶች በግልጽ የሚደግፉት በጣም ጥብቅና የበላይ የሆነውን የክርስትና ዓይነት ሲሆን ሌላው ቀርቶ ከመሳፍንት ወገን የሆኑ ተከታዮች ነበሯቸው። ቢሆንም በጉዳዩ ላይ የተነሳው ንትርክ ገና አልበረደም ነበር። ንጉሥ ሉዊስ 14ኛ የጃንሰኒስት ፅንሰ ሐሳብ መፍለቂያ የሆነው የፖርት ሮያል ገዳም እንዲጠፋ አዘዙ።

ተሃድሶ በተደረገባቸው የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የተነሳው ክርክር ገና መቋጫ አላገኘም ነበር። ከሌሎች ጋር በመሆን ያኮበስ አርሚኒየስን የሚከተሉ ሪሞንስትራንቶች አንድ ሰው ለራሱ መዳን የሚጫወተው ሚና አለ ብለው ያምኑ ነበር። የፕሮቴስታንቱ የዶርድሬክት ሲኖዶስ (1618–19) በጊዜው የተስፋፋውን ጥብቅ ካልቪናዊ አስተሳሰብ በተቀበለ ጊዜ ለጥያቄው ጊዜያዊ እልባት ሰጠ። ላቫንቸር ደ ላ ሬፎርም ለ ሞንድ ደ ዣን ካሊቫን የተባለው መጽሐፍ እንደሚገልጸው ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል በሚለው እምነትና በነፃ ምርጫ ላይ በጀርመን የተነሳው አለመግባባት ረዥም ጊዜ የወሰዱ “ያልተሳኩ የዕርቅ ሙከራዎችን እንዲሁም ተገቢ ያልሆኑ አድራጎቶችን፣ እስርንና የሃይማኖት ምሁራን መጋዝን የመሳሰሉ ድርጊቶች” እንዲወለዱ አድርጓል።

ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል ወይስ ነፃ ምርጫ?

ሆድና ጀርባ የሆኑት እነዚህ ሁለት ሐሳቦች ማለትም ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል የሚለው እምነትና ነፃ ምርጫ ገና ከመነሻቸው የተፋፋሙ አያሌ ቅራኔዎችን ቀስቅሰዋል። አውጉስቲን በበኩሉ እነዚህን እርስ በርስ የማይጣጣሙ ሐሳቦች ማብራራት አልቻለም ነበር። ካልቪንም የአምላክ ሉዓላዊ ፈቃድ መግለጫና የማይጨበጥ ነገር እንደሆነ አድርጎ ተመልክቶታል።

ነገር ግን ስለ አምላክ ባሕርያትና ማንነት መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው መግለጫ እነዚህ ጥያቄዎች ይበልጥ ግልጽ ሆነው እንዲገቡን ይረዳናልን? የሚቀጥለው ርዕስ ይህንን ነጥብ በጥልቀት ይመረምራል።

[በገጽ 4 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

ካልቪን

ሉተር

ጃንሰን

[ምንጭ]

ሥዕሎቹ፦ Bibliothèque Nationale, Paris

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ