የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 9/1 ገጽ 3-4
  • ነፃነት የሌለበት ሰፊ መንገድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ነፃነት የሌለበት ሰፊ መንገድ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ድሮ የነበረው አኗኗር ተለውጧል
  • በእርግጥም ሰፊ መንገድ
  • ሰፊው መንገድ ወደ ጥፋት ይወስዳል
  • ወደ ነፃነት የሚወስደው ጠባብ መንገድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ‘እሱን መስማታችሁን’ ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የይሖዋ ምሥክሮች፣ እውነተኛው ሃይማኖት የእነሱ ብቻ እንደሆነ ይሰማቸዋል?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 9/1 ገጽ 3-4

ነፃነት የሌለበት ሰፊ መንገድ

ቤቱ በእሳት ሲያያዝ ሦስቱም የቤተሰቡ አባላት ማለትም አባት፣ እናትና ትንሿ ሴት ልጃቸው በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ነበሩ። በመስኮቶቹ ለመዝለል ሞከሩ፤ ነገር ግን መስኮቶቹ በሌባ መከላከያ የብረት ዘንጎች ታጥረው ነበር። በእነዚሁ የብረት ዘንጎች የተነሳ እሳት አደጋ ተከላካዮች ሊያድኗቸው አልቻሉም። እናትየውና አባትየው እዚያው ጭሱና ነበልባሉ ውስጥ ሞቱ። ሴቷ ልጅ ሆስፒታል ከደረሰች በኋላ ሞተች።

ከአደጋ ይጠብቀናል ብለው ባደረጉት መከላከያ የተነሳ የዚህ ቤተሰብ አባላት ማለቃቸው እንዴት ያሳዝናል! የቤቱን ደህንነት ለመጠበቅ በሌባ መከላከያ የብረት ዘንግና በቁልፍ የሚጠቀመው ይህ ቤተሰብ ብቻ ስላልሆነ ታሪኩ ያለንበትን ጊዜ የሚያሳይ ነው። ብዙ ሰዎች ቤታቸውና ንብረታቸው በረዣዥም አጥር ታጥሯል። ይህንን ያደረጉት ለምንድን ነው? ደህንነትና የአእምሮ ሰላም ማግኘት ስለሚፈልጉ ነው። ሰዎች ደህንነት የሚሰማቸው በራሳቸው ቤቶች ውስጥ እስረኞች ሆነው ሲቀመጡ በሆነበት በ“ነፃው ዓለም” ላይ ይህ እንዴት ያለ መቅሰፍት ነው! ልጆች በአካባቢያቸው ባለ መናፈሻ ውስጥ ብቻቸውን ያለ ስጋት መጫወት ወይም ወላጃቸው አለበለዚያ ደግሞ ሌላ ትልቅ ሰው ካላደረሳቸው በስተቀር ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የማይችሉባቸው ሰፈሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱ መጥተዋል። በተለያዩ የኑሮ ዘርፎች ነፃነት እንደ ጠዋት ጤዛ እየተነነ ነው።

ድሮ የነበረው አኗኗር ተለውጧል

አያቶቻችን የኖሩባቸው ጊዜያት ካለንበት ጊዜ የተለዩ ነበሩ። ልጆች ሳሉ አብዛኛውን ጊዜ ያለፍርሃት ያሰኛቸው ቦታ መጫወት ይችሉ ነበር። አዋቂዎች ሳሉ ስለ ቁልፎችና መስኮት ላይ ስለሚገጠሙ የሌባ መከላከያ የብረት ዘንጎች አይጨነቁም ነበር። ነፃ እንደሆኑ ይሰማቸዋል፤ በተወሰነ መጠን ነፃ ነበሩ። ነገር ግን አያቶቻችን በእነርሱ ዕድሜ የኅብረተሰቡ ሁኔታ እየተለወጠ ሲሄድ ተመልክተዋል። ሁኔታው ተለውጦ ወዳጃዊ ስሜት ቀዝቅዟል፤ ሰዎች ይበልጥ ራስ ወዳድ ሆነዋል። በብዙ ቦታዎች የሰው ፍቅር ከላይ ለተጠቀሰው አሳዛኝ ሁኔታዎች አስተዋጽኦ ባደረገው የሰው ፍርሃት ተተክቷል። እያደገ ከመጣው ከዚህ የነፃነት ማጣት ጎን ለጎን የሥነ ምግባር ሕግጋቶች ያለማቋረጥ እያዘቀጡ ነው። ኅብረተሰቡ “አዲሱን ሥነ ምግባር” ወዶታል፤ ሐቁን ስንመለከት ግን ሁኔታው ምንም ዓይነት ሥነ ምግባር ወደማናይበት ደረጃ ደርሷል።

በክዊንዝላንድ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር ሩፔርት ጉድማን እንዲህ በማለት ጽፈዋል፦ “ወጣቶች በአሁኑ ጊዜ ልዩ ለሆነ ማለትም በሕይወት ውስጥ ከሁሉ ይበልጥ የሚያስፈልገው ደስታ ማግኘት ነው ለሚል . . . የአኗኗር ዘይቤ ተጋልጠዋል። ይህ አኗኗር የራስን ደስታ ማሳደድ፣ ከልክ በላይ ስለራስ መጨነቅ፣ ራስን ማርካት፣ የራስ ጥቅም የሚል መርሆ ያለው ሲሆን ‘በራስ’ ላይ ያተኮረ ነው።” በተጨማሪም እንዲህ አሉ፦ “ራስን መግዛት፣ ራስን መሥዋዕት ማድረግ፣ ጠንክሮ መሥራት፣ ጠንቃቃ መሆን፣ ባለሥልጣኖችን ማክበር፣ ወላጆችን ማፍቀርና ማክበር የመሳሰሉት ጥሩ ሥነ ምግባሮች . . . በብዙ ሰዎች ዘንድ እንግዳ የሆኑ ነገሮች እየሆኑ መጥተዋል።”

በእርግጥም ሰፊ መንገድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን የሚያውቁ ሰዎች እየተስፋፋ በመጣው በዚህ የራስ ወዳድነት ባሕርይ አይደነቁም። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ በማለት አድማጮቹን አስጠንቅቋል፦ “ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፣ መንገዱም ትልቅ ነውና፣ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ሕይወት፤ የሚወስደው ደጅ የጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ነውና፣ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።” (ማቴዎስ 7:13, 14) ለብዙ ተጓዦች የሚሆን በቂ ቦታ ያለው የመጀመሪያው መንገድ “ሰፊ” ነው፤ ምክንያቱም ሥነ ምግባርንና የዕለት ተዕለት ሕይወትን በሚቆጣጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ያልተገደበ ነው። ያለምንም ሕግጋትና ያለአንዳች ተጠያቂነት ደስ ያላቸውን ነገር መናገርና ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች በሰፊው መንገድ መጓዝ ያስደስታቸዋል።

እውነት ነው ሰፊውን መንገድ የመረጡ ብዙ ሰዎች ባገኙት ነፃነት እንደሚደሰቱ ይናገሩ ይሆናል። ነገር ግን አብዛኞቻቸው ተስፋፍቶ በሚገኘው የራስ ወዳድነት ጠባይ የሚንቀሳቀሱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ “በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ” እንደሚገዙ ይናገራል። ይህ መንፈስ ብልግና በመፈጸም፣ በአደንዛዥ ዕፆች በመጠቀም ወይም ስግብግብነት በተሞላበት ሁኔታ ሀብትን በማሳደድ፣ ክብርን ወይም ሥልጣንን በመፈለግ ‘የሥጋን ፈቃድ እያደረጉ በሥጋቸው ምኞት እንዲኖሩ’ ይገፋፋቸዋል።—ኤፌሶን 2:2, 3

ሰፊው መንገድ ወደ ጥፋት ይወስዳል

በሰፊው መንገድ ላይ እየተጓዙ ያሉ ሰዎች ‘የሥጋ ምኞትን’ ለመፈጸም እንደሚገፋፉ ልብ በል። ይህም በማንኛውም መንገድ ነፃ እንዳልሆኑ ያሳያል፤ ጌታ አላቸው። የሥጋ ባሪያዎች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ይህንን ጌታ ማገልገል ብዙ ችግር ሊያስከትል ይችላል። በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ወረርሽኝ በሽታዎች፣ የቤተሰብ መፈራረስ፣ በአደንዛዥ ዕፅና በአልኮል የተጎዳ አካልና አእምሮ ጥቂቶቹ ችግሮች ናቸው። እንዲያውም የዓመፅ ተግባራት፣ ዝርፊያና አስገድዶ መድፈር የመነጩት በዚህ ልቅ የሆነ ሰፊ መንገድ ላይ እየዳበረ ከመጣው የራስ ወዳድነት አስተሳሰብ ነው። ‘ወደ ጥፋት የሚወስደው’ መንገድ ሕልውና በቀጠለ መጠን የሚያፈራው ፍሬ ከምንጊዜውም ይበልጥ ጎጂ ይሆናል።—ምሳሌ 1:22, 23፤ ገላትያ 5:19–21፤ 6:7

ለምሳሌ ያክል ከአውስትራሊያ የተገኙ ሁለት እውነተኛ የሕይወት ታሪኮችን ተመልከት። ማሪ በአደንዛዥ ዕፆች እንድትጠቀምና የጾታ ብልግና እንድትፈጽም በሚደርስባት ፈተና ተሸነፈች።a ቢሆንም ትፈልገው የነበረው ደስታ ሸሻት። ሁለት ልጆች ከወለደች በኋላ እንኳ ሕይወቷ ባዶ ይመስል ነበር። ኤድስ እንደያዛት ስታውቅ ሕይወቷ የመጨረሻ አስከፊ ደረጃ ላይ ደረሰ።

ቶም ከዚህ በተለየ መንገድ ተሠቃይቶ ነበር። “ያደግሁት ሰሜን ክዊንዝላንድ ውስጥ በሚገኝ ሚሽን ቤተ ክርስቲያን ነበር” በማለት ጻፈ። “በ16 ዓመቴ በጣም መጠጣት ጀመርኩ። አባቴ፣ አጎቶቼና ጓደኞቼ የወጣላቸው ጠጪዎች ስለነበሩ ማንኛውም ሰው የሚያደርገው የተለመደ ነገር ይመስለኝ ነበር። ከቢራ ጀምሮ ለመጠጥነት የማያገለግሉ የአልኮል ፈሳሾችን እስከ መጠጣት ደርሼ ነበር። በተጨማሪም የፈረስ ውድድር ሲካሄድ ገንዘብ እያስያዝኩ መወራረድ ጀመርኩ፤ አንዳንድ ጊዜ ላቤን አንጠፍጥፌ ካገኘሁት ደሞዝ አብዛኛውን በውርርዱ አጠፋ ነበር። የምሠራው ሸንኮራ አገዳ የመቁረጥ ሥራ ጥሩ ክፍያ ስለሚያስገኝልኝ የማወጣው ገንዘብ ቀላል አልነበረም።

“ከዚያም አገባሁና ልጆች ወለድን። ኃላፊነቶቼን ከመወጣት ይልቅ ጓደኞቼ እንደሚያደርጉት እጠጣ፣ ቁማር እጫወትና እደባደብ ነበር። በምኖርበት አካባቢ በሚገኝ እስር ቤት ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ። ነገር ግን ይህም እንኳ በእኔ ላይ ለውጥ አላመጣም። ሕይወቴ እያዘቀጠ ነበር። በችግር የተሞላ ነበር።”

አዎን፣ ቶምና ማሪ ራሳቸውን ለመጥፎ ምኞት አሳልፈው በመስጠት ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸውንም ጭምር ጎድተዋል። የሚያሳዝነው ሌሎች ብዙ ወጣቶች ልቅ የሆነው ሰፊ መንገድ በሚያቀርበው የተሳሳተ ነፃነት ተታለዋል። ወጣቶች ከዚህ ነፃነት በስተጀርባ ያለውን እውነታ መመልከት ቢችሉ ጥሩ ነው። የሰፊውን መንገድ እውነተኛ ሁኔታዎች ማለትም በዚህ መንገድ ላይ የሚጓዙ ሰዎች መጨረሻ ላይ የማይቀሩላቸውን አስከፊ ውጤቶች መመልከት ቢችሉ ጥሩ ነው። በእርግጥም ሰፊና በላዩ ላይ ለመጓዝ የማያስቸግር ነው። ቢሆንም የሚያስከትለው ችግር የዚያኑ ያህል በጣም ሰፊ ነው። “በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳል” የሚለውን የማይታበል ሐቅ አክብዶ መመልከት የጥበብ መንገድ ነው።—ገላትያ 6:8

ነገር ግን ከዚህ የተሻለ አማራጭ መንገድ አለ። ይህም ጠባቡ መንገድ ነው። ነገር ግን ይህ መንገድ ምን ያህል የማያወላዳ፣ ምን ያህልስ በሰዎች የተጨናነቀና ጠባብ ነው? የሚወስደውስ ወዴት ነው?

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ስሞቹ ተለውጠዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ