የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 3/15 ገጽ 31
  • የበሽተኞች መብት ተከበረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የበሽተኞች መብት ተከበረ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሐኪም ሙያ
    ንቁ!—1993
  • የይሖዋ ምሥክሮችና የሕክምና ባለሙያዎች ተባብረው ይሠራሉ
    ንቁ!—1994
  • አምላክ ስለ ደም ያለውን አመለካከት ተቀበልኩ
    ንቁ!—2004
  • የመምረጥ መብት አለህ
    ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 3/15 ገጽ 31

የበሽተኞች መብት ተከበረ

‘ይህን ቀዶ ሕክምና በምንም ዓይነት ያለ ደም ማድረግ አልችልም። ቀዶ ሕክምናው እንዲደረግልሽ የምትፈልጊ ከሆነ እኔ የማክምበትን መንገድ መቀበል አለብሽ። አለበለዚያ ሌላ ዶክተር መፈለግ ይኖርብሻል።’

ዶክተሩ የተናገረው ነገር ጄንግ ሴ ጁ የተባለችውን በታይላድ የምትኖር የይሖዋ ምሥክር እምነት አላናወጠውም። ሜኒንጂኦማ የተባለ የአንጎል ዕጢ የሚያሠቃያት ጄንግ በፍጥነት ቀዶ ሕክምና ማድረግ ያስፈልጋት ነበረ። ነገር ግን ‘ከደም ራቁ’ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ ለመከተል ወስና ነበር።—ሥራ 15:28, 29

በተቻለ መጠን አገሯ ውስጥ ለመታከም ስለፈለገች ወደ ሌሎች ሁለት ሆስፒታሎች ሄደች። እዚያም ያሉት ዶክተሮች ያለ ደም ቀዶ ሕክምና አናደርግም አሉ። በመጨረሻ ታይላንድ በሚገኘው የሆስፒታል መረጃ አገልግሎት (ኤች አይ ኤስ) አማካኝነት ከቶኪዮ የሴቶች ሕክምና ኮሌጅ ኒውሮሎጂካል ተቋም ጋር ተገናኘች። ይህ ሆስፒታል በጨረር ሕክምና አዲስ ግኝት በሆነው በጋማ ጨረር በመጠቀም የአንጎል ዕጢ ላለባቸው ከ200 ለሚበልጡ ሰዎች ሕክምና አድርጎ ነበር።

ጄንግ በሆስፒታሉ አቅራቢያ በሚኖሩ ጃፓናውያን የይሖዋ ምሥክሮች ቤት እንድታርፍ ዝግጅት ተደረገ። ሁለት የታይላንድ ቋንቋ መናገር የሚችሉ የኤች አይ ኤስ ወኪሎችን ጨምሮ ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች ተሰባስበው በአውሮፕላን ማረፊያው በመገኘት ተቀበሏት። ጄንግ አንድ ሳምንት ያህል ከተመረመረች በኋላ የጋማ ጨረር ሕክምና ወደምትወስድበት ሆስፒታል ገባች። ሕክምናው የወሰደው አንድ ሰዓት ብቻ ነበር። በማግሥቱ ከሆስፒታል ወጣችና በሦስተኛው ቀን ወደ ታይላንድ ተመለሰች።

ጄንግ እንዲህ አለች፦ “በዚህ ዝግጅት አማካኝነት ይህን ያክል እርዳታ አገኛለሁ ብዬ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም። ያሳዩኝ ፍቅርና እርስ በርስ ያለው ቅንጅት ነክቶኛል።”

ማዪኔቼ ሺምቡን የተባለ አንድ የጃፓን ጋዜጣ ይህን ዜና ሪፖርት ሲያደርግ እንዲህ ብሏል፦ “እስካሁን ድረስ ደም አለመውሰድ ጎላ ብሎ የሚታየው በሃይማኖታዊ ምክንያቶች ነበር። ሆኖም ደም መውሰድ ኤድስን፣ ሄፓታይተስ ሲ የመሳሰሉ በቫይረስ የሚመጡ በሽታዎችንና የተለያዩ አለርጂዎችን ያስከትላል። በዚህ የተነሳ ሃይማኖታዊ እምነታቸው ምንም ዓይነት ቢሆን ደም ለመውሰድ የማይፈልጉ በሽተኞች አሉ።”

ጋዜጣው በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ደም አንወስድም ያሉ ብዙ ሰዎች ሆስፒታል ለመቀየር ተገደዋል፤ ሆኖም የበሽተኞችን ምርጫ በማክበር ረገድ የሕክምና ተቋሞች ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። በሽተኞች ምን ዓይነት ሕክምና እንደሚሰጣቸው አስቀድሞ ማወቅና በሚሰጣቸው ሕክምና መስማማት ያለባቸው ሲሆን ደም የመውሰዱም ጉዳይ ከዚህ የተለየ መሆን የለበትም። ይህ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል።”

እንደ ጄንግ ሴ ጁ ያሉ ሌሎች ያለ ደም የሚደረግ ሕክምና የሚፈልጉ ሰዎች ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች መዛወር አስፈልጓቸዋል። ሆኖም የበሽተኞቻቸውን መብት ለማክበር ፈቃደኛ የሆኑ ዶክተሮች የሚያደርጉትን ጥረት ያደንቃሉ።

የሆስፒታል መረጃ አገልግሎት የይሖዋ ምሥክሮችን እምነት የሚያከብሩ ሐኪሞችን ትብብር ለመጠየቅ በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ቅርንጫፍ ቢሮዎች የተደረገ ዝግጅት ነው። የሆስፒታል መረጃ አገልግሎት በዓለም ዙሪያ ከሆስፒታሎች፣ ከሕክምና ባለሙያዎች፣ ከጤና ጥበቃ ሠራተኞች፣ ከጠበቆችና ከዳኞች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ