የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 4/15 ገጽ 30
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ታማኝነት የሚያስከትለውን ፈተና መቋቋም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ትምህርትን ይሖዋን ለማወደስ ተጠቀሙበት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • “አንተ ብቻ ታማኝ ነህ”
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
  • ታማኝ የሆኑትን ተመልከቱ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 4/15 ገጽ 30

ታስታውሳለህን?

በቅርብ ጊዜ ከወጡት የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ተግባራዊ ጥቅም አግኝተህባቸዋልን? እንግዲያው ምን ያህል እንደምታስታውስ በሚከተሉት ጥያቄዎች ለምን ራስህን አትፈትንም፦

◻ ከአሞናውያን ውድቀት ምን መማር እንችላለን? (ሶፎንያስ 2:9, 10)

ይሖዋ ለሚያሳየው ደግነት ምላሹ ጥላቻ ከሆነ ሁኔታውን አቅልሎ አይመለከተውም፤ በጥንት ጊዜያት እንዳደረገው ሁሉ ወደፊትም የወሰነው ጊዜ ሲደርስ እርምጃ ይወስዳል። (ከመዝሙር 2:6-12 ጋር አወዳድር።)—12/15፣ ገጽ 10

◻ ክርስቲያኖች በየትኞቹ መንገዶች ሰላም አላቸው?

በመጀመሪያ ደረጃ “በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም” አግኝተዋል። (ሮሜ 5:1) በሁለተኛ ደረጃ “በመጀመሪያ ንጽሕት፣ በኋላም ሰላማዊ” የሆነችውን “ላይኛይቱን ጥበብ” ስለሚኮተኩቱ እርስ በርሳቸው ሰላም አላቸው። (ያዕቆብ 3:17 አዓት)—1/1 ገጽ 11

◻ የአምላክ ቃል በምን ነገሮች ተመስሏል? ይህስ ለእኛ ጠቃሚ የሆነው እንዴት ነው?

የአምላክ ቃል በሚያዳብር ወተት፣ በጠንካራ ምግብ፣ በሚያረካና ንጹሕ በሚያደርግ ውኃ፣ በመስተዋት እንዲሁም በስለታም ሰይፍ ተመስሏል። አንድ አገልጋይ እነዚህ አገላለጾች ምን ትርጉም እንዳላቸው ከተረዳ መጽሐፍ ቅዱስን ጥሩ አድርጎ ሊጠቀምበት ይችላል።—1/1፣ ገጽ 29

◻ ሚዛኑን የጠበቀ ዓለማዊ ትምህርት ምን እንድናደርግ ሊረዳን ይገባል?

በጥሩ ሁኔታ እንድናነብ፣ ግልጽ በሆነ ሁኔታ እንድንጽፍ፣ በአእምሮም ሆነ በሥነ ምግባር እንድንጎለምስ እንዲሁም የዕለት ተዕለት ኑሯችንን እንድናሸንፍና ውጤታማ የሆነ ቅዱስ አገልግሎት ለማቅረብ ይረዳናል።—2/1፣ ገጽ 10

◻ ትምህርትን በተመለከተ ከኢየሱስ ምን ጠቃሚ ትምህርት ልናገኝ እንችላለን?

ያገኘነውን ትምህርት ራሳችንን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሳይሆን ታላቁን አስተማሪ ይሖዋን ለማወደስና ለማስከበር መጠቀም እንዳለብን እንማራለን። (ዮሐንስ 7:18)—2/1 ገጽ 10

◻ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ይህ መንግሥት አምላክ ኃጢአትና ሞት ያስከተሏቸውን ችግሮች ለማስወገድና በምድር ላይ የጽድቅ ሁኔታዎች እንዲሰፍኑ ለማድረግ ያለውን ፈቃዱን የሚያስፈጽም በሰማይ የተቋቋመ መለኮታዊ መስተዳድር ነው። (ዳንኤል 2:44፤ ራእይ 11:15፤ 12:10)—2/1፣ ገጽ 16

◻ መጽሐፍ ቅዱስ ዓመፅን ጨርሶ ለማጥፋት የሚያስፈልግ ትምህርት የሚሰጠው እንዴት ነው?

ይሖዋ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ሰዎች ሰላም ወዳድና ጻድቅ እንዲሆኑ እያስተማራቸው ነው። (ኢሳይያስ 48:17, 18) የአምላክ ቃል የሰውን ልብ ለመንካትና አስተሳሰቡንና ባሕርዩን ለመለወጥ የሚያስችል ኃይል አለው። (ዕብራውያን 4:12)—2/15፣ ገጽ 6

◻ የኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ትንቢት ሦስት ፍጻሜዎች አሉት ሊባል የሚቻለው በምን መንገድ ነው?

የኢሳይያስ ትንቢት የመጀመሪያ ፍጻሜውን ያገኘው አይሁዶች በ537 ከዘአበ ከባቢሎን ምርኮ በተመለሱበት ወቅት ነበር። መንፈሳዊ እስራኤላውያን ከታላቂቱ ባቢሎን ቁጥጥር ስለወጡ በዛሬው ጊዜ መንፈሳዊ ፍጻሜ እያገኘ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ምድር ቃል በቃል ገነት ትሆናለች በማለት ከሚሰጠው ተስፋ ጋር በተያያዘ መልኩ ወደፊት ሦስተኛ ፍጻሜ ይኖረዋል። (መዝሙር 37:10, 11፤ ራእይ 21:4, 5)—2/15፣ ገጽ 17

◻ አምላክ ልጁ ኢየሱስ በፈጸማቸው ተአምራት አማካኝነት ለሰዎች በግል እንዲሚያስብ ያሳየው እንዴት ነው?

ኢየሱስ ‘አብ ሲያደርግ ያየውን እንጂ ከራሱ ምንም ሊያደርግ ስለማይችል’ እርሱ ያሳየው ርኅራኄ ይሖዋ ለእያንዳንዱ አገልጋዩ ፍቅራዊ አሳቢነት እንዳለው የሚያሳይ ነው። (ዮሐንስ 5:19)—3/1፣ ገጽ 5

◻ ኢየሱስ በዮሐንስ 5:28, 29 (አዓት) ላይ የተጠቀመበት “የመታሰቢያ መቃብር” የሚለው አባባል ምን ያመለክታል?

እዚህ ላይ የገባው ምኔምዮን (የመታሰቢያ መቃብር) የሚለው የግሪክኛ ቃል አንድ ሰው ከሞተ በኋላም ይሖዋ ታሪኩን እንደሚያስታውሰው ያሳያል። ይህም የእርሱን ወይም የእርሷን የተፈጥሮ ጠባይና በአእምሯቸው ውስጥ ያለውን ነገር ያጠቃልላል። ይህ ሁኔታ አምላክ ለሰዎች በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብላቸው ጠንካራ ማስረጃ ይሆናል!—3/1፣ ገጽ 6

◻ በሶፎንያስ ትንቢት ውስጥ ለእኛ በጣም ጠቃሚ የሆነ ምን የማስጠንቀቂያ መልእክት ሰፍሯል?

ዛሬ በልባችን ውስጥ ጥርጣሬዎች እንዲተከሉ የምንፈቅድበትና በአእምሯችንም ሆነ በልባችን የይሖዋ ቀን ገና ነው ብለን የምናስብበት ጊዜ አይደለም። በተጨማሪም ሰዎች የሚያሳዩን ግዴለሽነት እንዳያዳክመን መጠንቀቅ አለብን። (ሶፎንያስ 1:12, 13፤ 3:8)—3/1፣ ገጽ 17

◻ ለአምላክ ታማኝ መሆን አስቸጋሪ የሆነው ለምንድን ነው?

ምክንያቱም ታማኝነት ከወላጆቻችን ከወረስናቸው የራስ ወዳድነት ዝንባሌዎች ጋር አይስማማም። (ዘፍጥረት 8:21፤ ሮሜ 7:19) ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰይጣንና አጋንንቱ አምላክን እንድንከዳ ለማድረግ ከምንጊዜውም የበለጠ ታጥቀው ተነሥተዋል። (ኤፌሶን 6:12፤ 1 ጴጥሮስ 5:8)—3/15፣ ገጽ 10

◻ ታማኝ በመሆን ረገድ በየትኞቹ አራት መስኮች የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች መቋቋም አለብን? ይህንን ለማድረግ የሚረዳን ምንድን ነው?

እነዚህ አራት መስኮች ለይሖዋ፣ ለድርጅቱ፣ ለጉባኤና ለትዳር ጓደኛ ታማኝ መሆን ናቸው። ለዚህ የሚረዳን አንዱ ነገር ታማኝነት የሚያስከትለውን ፈተና መቋቋማችን የይሖዋን ሉዓላዊነት ከስድብ ነፃ ከማድረግ ጋር የተያያዘ መሆኑን ማወቃችን ነው።—3/15፣ ገጽ 20

◻ ዳዊት ታቦቱን ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ካደረገው ሙከራ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን? (2 ሳሙኤል 6:2-7)

ዳዊት የታቦቱን አያያዝ በተመለከተ ይሖዋ የሰጣቸውን መመሪያዎች ችላ ማለቱ መቅሰፍት አስከትሎበታል። ይህ ሁኔታ ይሖዋ የሰጣቸውን ግልጽ የሆኑ መመሪያዎች ችላ በማለታችን ምክንያት ለሚደርሱብን ችግሮች ፈጽሞ በይሖዋ ላይ ማማረር እንደሌለብን ያስተምረናል። (ምሳሌ 19:3)—4/1፣ ገጽ 28, 29

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ