የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w96 12/15 ገጽ 22-24
  • አቂላና ጵርስቅላ ምሳሌ የሚሆኑ ባልና ሚስት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አቂላና ጵርስቅላ ምሳሌ የሚሆኑ ባልና ሚስት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ድንኳን ሰፊዎች
  • እንግዳ ተቀባይ የመሆን ምሳሌ
  • ለጳውሎስ ሲሉ ‘ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ’
  • የሚቀራረቡ ባልና ሚስት
  • ደቀ መዛሙርት የማድረግ ዓላማ ይዛችሁ ስበኩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • “መናገርህን ቀጥል እንጂ ዝም አትበል”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • ክርስቲያኖች እርስ በርስ መደጋገፍ አለባቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • ታስታውሳለህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
w96 12/15 ገጽ 22-24

አቂላና ጵርስቅላ ምሳሌ የሚሆኑ ባልና ሚስት

“በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ [“የሥራ ባልደረቦቼ ለሆኑት፣” አዓት] ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን [“አንገታቸውን፣” አዓት] ለሞት አቀረቡ፣ የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑአቸው ናቸው እንጂ እኔ ብቻ አይደለሁም።”—ሮሜ 16:3, 4

ሐዋርያው ጳውሎስ ሮም ለሚገኘው ጉባኤ የጻፋቸው እነዚህ ቃላት ለእነዚህ ባልና ሚስት ከፍተኛ የሆነ አድናቆትና አክብሮት እንዳለው የሚያመለክቱ ናቸው። ለጉባኤያቸው በሚጽፍበት ጊዜ እነርሱን ላለመዘንጋት ተጠንቅቋል። ይሁን እንጂ የጳውሎስ ‘የሥራ ባልደረቦች የነበሩት’ እነዚህ ሁለት ሰዎች እነማን ናቸው? በእርሱም ሆነ በጉባኤው ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያተረፉት ለምን ነበር?—2 ጢሞቴዎስ 4:19

አቂላ ከእስራኤል ግዛት ውጪ ከሚኖሩት አይሁዳውያን (ተፈናቃይ አይሁዳውያን) አንዱ ሲሆን የትውልድ አገሩ በትንሿ እስያ በስተ ሰሜን በሚገኘው ጳንጦስ በሚባለው ክፍለ ሃገር ነው። እርሱና ሚስቱ ጵርስቅላ (ጵርስቃ) ወደ ሮም ሄደው እዚያ መኖር ጀመሩ። ፖምፔ በ63 ከዘአበ ኢየሩሳሌምን ወርሮ ብዙ ቁጥር ያላቸው እስረኞች ባሪያ ሆነው ወደ ሮም እንዲጋዙ ባደረገ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአይሁዳውያን ማኅበረሰብ ቀደም ሲል በእዚህ ከተማ ይኖሩ ነበር። እንዲያውም በሮም የተገኙ በድንጋይ ላይ የተቀረጹ ጽሑፎች አሥራ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ምኩራቦች በጥንቷ ከተማ እንደነበሩ አረጋግጠዋል። በ33 እዘአ በጰንጠቆስጤ ዕለት ምሥራቹን ያዳመጡ ከሮም የመጡ ብዙ አይሁዳውያን በኢየሩሳሌም ተገኝተው ነበር። የክርስትናን መልእክት ወደ ሮማ ግዛት ዋና ከተማ በመጀመሪያ ያደረሱት ምናልባት እነዚህ ሰዎች ሳይሆኑ አይቀርም።—ሥራ 2:10

ይሁን እንጂ በንጉሠ ነገሥት ቀላውዴዎስ ትእዛዝ አይሁዳውያን በ49 ወይም በ50 እዘአ መጀመሪያ ላይ ከሮም ተባረሩ። በዚህም ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ የግሪክ ዋና ከተማ በሆነችው በቆሮንቶስ ከአቂላና ከጵርስቅላ ጋር ተገናኘ። ጳውሎስ ቆሮንቶስ በደረሰ ጊዜ አቂላና ጵርስቅላ እንግድነት ተቀብለው አስተናገዱት። ድንኳን የመስፋት ተመሳሳይ የእጅ ሙያ ስለነበራቸው ሥራም ጭምር ሰጡት።—ሥራ 18:2, 3

ድንኳን ሰፊዎች

ሥራው ቀላል አልነበረም። ድንኳን መሥራት ጠንካራ፣ ሸካራ ሸራዎችን ወይም ቆዳዎችን መቁረጥና አንድ ላይ መስፋትን የሚጠይቅ ነበር። ታሪክ ጸሐፊው ፈርናንዶ ቤያ “በጉዞ ጊዜ ለመጠለያ፣ ከፀሐይና ከዝናብ ለመከላከያ ወይም በመርከብ ውስጥ ለዕቃ ማሠሪያ የሚያገለግሉ ሸራዎችን ለማዘጋጀት ሸካራና ከርዳዳ ሸራዎችን” ለሥራው የሚጠቀም ድንኳን ሰፊ “ሥራው ልዩ ሙያና ጥንቃቄ ይጠይቅበት ነበር” በማለት ተናግረዋል።

ይህ አንድ ጥያቄ ያስነሳል። ጳውሎስ ከፍተኛ የሥራ ዓይነት የሚያስገኝለትን ትምህርት ‘በገማልያል እግር አጠገብ’ የተማረ እንደሆነ ተናግሮ አልነበረምን? (ሥራ 22:3) ይህ እውነት ቢሆንም አንድ ልጅ ከፍተኛ ትምህርት እንዲቀስም ቤተሰቡ አቅዶ እያለ እርሱን የእጅ ሙያ ማስተማር በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይኖሩ በነበሩ አይሁዶች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ይሰጠው ነበር። ስለዚህም ሁለቱም አቂላና ጳውሎስ ድንኳን የመስፋት ሙያ የተማሩት ገና ወጣት በነበሩበት ጊዜ ሳይሆን አይቀርም። ይህ ሙያ ከጊዜ በኋላ ጠቃሚ ሆኖ ተገኝቷል። ይሁን እንጂ ክርስቲያን እንደመሆናቸው መጠን ዋነኛው ግባቸው እንዲህ ዓይነቱን ሥጋዊ ሥራ ማሳደድ አልነበረም። ጳውሎስ ከአቂላና ከጵርስቅላ ጋር ሆኖ በቆሮንቶስ ይሠራ የነበረው እንቅስቃሴውን ማለትም ምሥራቹን ለማወጅ የሚያስችለውን ድጋፍ ‘በሌሎች ላይ ሳይከብድ’ ለማግኘት ብቻ እንደሆነ አብራርቷል።—2 ተሰሎንቄ 3:8፤ 1 ቆሮንቶስ 9:18፤ 2 ቆሮንቶስ 11:7

አቂላና ጵርስቅላ ጳውሎስ ሚስዮናዊ አገልግሎቱ ቀላል እንዲሆንለት ለማገዝ አቅማቸው የሚፈቅድላቸውን ያህል ለማድረግ ደስተኞች እንደነበሩ ግልጽ ነው። ሦስቱ ጓደኛሞች ሊገዙ ለሚመጡና ለመንገደኞች መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት ለመስጠት ምን ያህል ጊዜ ሥራቸውን ያቋርጡ እንደነበር ማን ያውቃል! በተጨማሪም በዘመናችን ያሉት ክርስቲያኖች ሰፋ ያለ ጊዜያቸውን ሰዎች ምሥራቹን እንዲሰሙ በሚደረገው ሥራ ላይ ለማዋል ሲሉ የትርፍ ጊዜ ሥራና በዓመት ውስጥ የተወሰኑ ወራት ብቻ እንደሚሠሩ ሁሉ እነርሱም ምንም እንኳ ድንኳን የመስፋት ሥራቸው አድካሚና ዝቅተኛ ሥራ ቢሆንም የአምላክን መንግሥት ጥቅሞች ለማስፋፋት ሲሉ “ቀንና ሌሊት” ለመሥራት ደስተኞች ነበሩ። —1 ተሰሎንቄ 2:9፤ ማቴዎስ 24:14፤ 1 ጢሞቴዎስ 6:6

እንግዳ ተቀባይ የመሆን ምሳሌ

ጳውሎስ 18 ወራት በቆሮንቶስ በቆየባቸው ጊዜያት የአቂላን ቤት ሚስዮናዊ እንቅስቃሴዎችን የሚያከናውንበት ማዕከል ሳያደርግ አልቀረም። (ሥራ 18:3, 11) በተጨማሪም ሲላስ (ሲልቫነስ) እና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ በእንግድነት በመጡ ጊዜ አቂላና ጵርስቅላ እነርሱን በእንግድነት ለመቀበል ደስተኞች ኖረው መሆን አለበት። (ሥራ 18:5) ከጊዜ በኋላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆኑት ጳውሎስ ወደ ተሰሎንቄ የጻፋቸው ሁለቱ ደብዳቤዎች የተጻፉት ሐዋርያው ከአቂላና ከጵርስቅላ ጋር አብሮ በሚኖርበት ጊዜ ሊሆን ይችላል።

በዚህ ጊዜ የጵርስቅላና የአቂላ ቤት ለብዙ ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ማዕከላዊ ቦታ እንደነበረ ለመገመት አያስቸግርም። ተወዳጅ ወዳጆቻቸው የነበሩት በአካያ አውራጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትናን ተቀብለው ራሱ ጳውሎስ ያጠመቃቸው እስጢፋኖስና ቤተሰቡ፣ ቤቱን ጳውሎስ ንግግር እንዲያቀርብበት የፈቀደለት ቲቶ ኢዮስጦስ፣ ከመላው ቤተሰቡ ጋር እውነትን የተቀበለው ቀርስጶስ የተባለው የምኩራብ አለቃ አዘውትረው እዚህ ቤት ሳይመላለሱ አልቀረም። (ሥራ 18:7, 8፤ 1 ቆሮንቶስ 1:16) በተጨማሪም ፈርዶናጥስና አካይቆስ፤ እቤቱ የጉባኤ ስብሰባዎች እንዲደረጉ የፈቀደው ጋይዮስ፤ የከተማ መጋቢ የነበረው ኤርስጦስ፤ ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች ደብዳቤ ሲልክ ጸሐፊው የነበረው ጤርጥዮስ፤ የክንክራኦስ ጉባኤ ታማኝ እህት የነበረችውና ምናልባትም ደብዳቤውን ከቆሮንቶስ ተቀብላ ወደ ሮሜ የወሰደችው ፌቤን ይገኙበታል።—ሮሜ 16:1, 22, 23፤ 1 ቆሮንቶስ 16:17

ተጓዥ አገልጋዮችን በእንግድነት ለመቀበል አጋጣሚው ያላቸው በአሁኑ ዘመን የሚኖሩ የይሖዋ አገልጋዮች ይህ ወቅት ምን ያህል የሚያበረታታና አስደሳች ትዝታ ጥሎ እንደሚያልፍ ያውቃሉ። በእነዚህ ጊዜያት የሚነገሩት የሚያንጹ ተሞክሮዎች ለሁሉም መንፈሳዊ የማበረታቻ ምንጭ ሊሆኑላቸው ይችላሉ። (ሮሜ 1:11, 12) በተጨማሪም አቂላና ጵርስቅላ እንዳደረጉት እንደ ጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት ለመሰሉት ስብሰባዎች ቤታቸውን ክፍት ያደረጉ ለእውነተኛው አምልኮ መስፋፋት በዚህ መንገድ አስተዋጽኦ ለማድረግ በመቻላቸው ደስታና እርካታ ያገኛሉ።

አቂላና ጵርስቅላ ከጳውሎስ ጋር በጣም የጠበቀ ወዳጅነት ስለነበራቸው በ52 እዘአ በጸደይ ወራት ቆሮንቶስን ለቆ በሄደ ጊዜ እስከ ኤፌሶን ድረስ አብረውት በመሄድ ሸኝተውታል። (ሥራ 18:18-21) በዚህ ከተማ ከቆዩ በኋላ ሐዋርያው ለሚያደርገው ቀጣይ ጉብኝት መሠረት ጣሉ። እነዚህ ጥሩ ተሰጥኦ የነበራቸው የምሥራቹ አስተማሪዎች አንደበተ ርቱዕ የነበረውን አጵሎስን ያገኙትና ‘የእግዚአብሔርን መንገድ ከፊት ይልቅ በትክክል’ የገለጡለት በዚህ ከተማ ነበር። (ሥራ 18:24-26) ጳውሎስ በ52/53 እዘአ በክረምት አካባቢ በሦስተኛው ሚስዮናዊ ጉዞው ኤፌሶንን ድጋሚ በጎበኘ ጊዜ እነዚህ ታታሪ ባልና ሚስት የዘሩት ዘር ለአጨዳ ደርሶ ነበር። የኤፌሶን ጉባኤ በአቂላ ቤት ስብሰባዎችን በሚያደርግበት ወቅት ጳውሎስ ሦስት ዓመት ለሚያህል ጊዜ “መንገዱን” እየሰበከ አስተምሯል።—ሥራ 19:1-20, 26፤ 20:31፤ 1 ቆሮንቶስ 16:8, 19

ከዚያም ወደ ሮም በተመለሱ ጊዜ እነዚህ የጳውሎስ ጓደኞች ቤታቸውን ለክርስቲያን ስብሰባዎች ክፍት አድርገው ‘እንግዶችን የመቀበል ጎዳና መከተላቸውን’ ቀጥለዋል።—ሮሜ 12:13፤ 16:3-5

ለጳውሎስ ሲሉ ‘ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ’

ጳውሎስ ኤፌሶን በነበረበት ጊዜ ከአቂላና ከጵርስቅላ ጋር በአንድ ቤት ሳይኖር አልቀረም። አንጥረኞች ሁካታ ባስነሱበት ወቅት ከእነርሱ ጋር ይኖር ነበር? በሥራ 19:23-31 ላይ እንደተመዘገበው ምስሎችን ይሠሩ የነበሩት ብር ሠሪዎች የመንግሥቱ ምሥክርነት እንዳይሰጥ ዓመፅ ባስነሱ ጊዜ ጳውሎስ ወደ ረብሸኞቹ ዘልቆ በመግባት ሕይወቱን አደጋ ላይ እንዳይጥል ወንድሞች አገዱት። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ጳውሎስ ‘በሕይወቱ ተስፋ የቆረጠው’ እንዲሁም አቂላና ጵርስቅላ በአንድ መንገድ ጣልቃ ገብተው ለእርሱ ሲሉ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉት በዚህ ቀውጢ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አላቸው።—2 ቆሮንቶስ 1:8፤ ሮሜ 16:3, 4

“ሁከቱም ከቀረ በኋላ” ጳውሎስ ቀስ ብሎ ከተማውን ለቆ ሄደ። (ሥራ 20:1) አቂላና ጵርስቅላም ተቃውሞና ፌዝ እንደገጠማቸው ምንም አያጠራጥርም። ይህ ሁኔታ ተስፋ አስቆርጧቸው ይሆን? ከዚህ በተቃራኒ አቂላና ጵርስቅላ ክርስቲያናዊ እንቅስቃሴያቸውን ሳያቋርጡ በድፍረት ወደፊት ገፍተዋል።

የሚቀራረቡ ባልና ሚስት

የቀላውዴዎስ የግዛት ዘመን ሲያከትም አቂላና ጵርስቅላ ወደ ሮም ተመለሱ። (ሮሜ 16:3-15) ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ ተጠቅሰው የምናገኛቸው ወደ ኤፌሶን ከተመሰሉ በኋላ ነው። (2 ጢሞቴዎስ 4:19) በሌሎች ጥቅሶች ላይ እንደተገለጸው ሁሉ እዚህም ላይ ቢሆን እነዚህ ባልና ሚስት የተጠቀሱት በአንድነት ነው። እንዴት ያሉ የተቀራረቡና አንድነት ያላቸው ባልና ሚስት ነበሩ! ጳውሎስ ውድ ወንድም የሆነውን አቂላን ሲያስታውስ የሚስቱን የታማኝነት ድጋፍ ሳያነሳ ማለፍ አልቻለም። አንዱ የትዳር ጓደኛ የሚሰጠው የታማኝነት እገዛ ሌላኛው የትዳር ጓደኛ አንዳንድ ጊዜ ነጠላ የሆነ ግለሰብ ሊያከናውን ከሚችለው በላይ “በጌታ ሥራ” ከፍተኛ የሆነ ተግባር እንዲፈጽም ስለሚያስችለው በአሁኑ ጊዜ ለሚገኙት ክርስቲያን ባልና ሚስቶች እንዴት ያሉ ጥሩ ምሳሌ ይሆናሉ።—1 ቆሮንቶስ 15:58

አቂላና ጵርስቅላ በተለያዩ ጉባኤዎች አገልግለዋል። በአሁኑ ጊዜም ቀናተኛ ክርስቲያኖች እርዳታ የበለጠ ወደሚያስፈልግበት ቦታ ልክ እንደነርሱ ተዛውረው ያገለግላሉ። የመንግሥቱ ሥራ እያደገ ሲሄድ ሲመለከቱና ሞቅ ያለና ውድ የሆነ ክርስቲያናዊ ወዳጅነት ሲያዳብሩ እነርሱም ደስታና እርካታ ያገኛሉ።

አቂላና ጵርስቅላ ከፍተኛ የክርስቲያናዊ ፍቅር ምሳሌ በማሳየታቸው ምክንያት የጳውሎስና የሌሎች ሰዎች አድናቆት አትርፈዋል። ከሁሉም የሚበልጠው ግን በይሖዋ ዘንድ ጥሩ ስም ማትረፋቸው ነው። ቅዱሳን ጽሑፎች “እግዚአብሔር፣ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፣ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና” በማለት ያረጋግጡልናል።—ዕብራውያን 6:10

አቂላና ጵርስቅላ እንዳደረጉት ራሳችንን ለማቅረብ የሚያስችለን አጋጣሚ ላይፈጠር ቢችልም የእነርሱን ግሩም ምሳሌ ልንከተል እንችላለን። ጉልበታችንንና ሕይወታችንን ለቅዱስ አገልግሎት ስናውል ጥልቅ የሆነ እርካታ እናገኛለን። “መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።”—ዕብራውያን 13:15, 16

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ