የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 4/15 ገጽ 27
  • ታስታውሳለህን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታስታውሳለህን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አቂላና ጵርስቅላ ምሳሌ የሚሆኑ ባልና ሚስት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ደቀ መዛሙርት የማድረግ ዓላማ ይዛችሁ ስበኩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ሙዚቃ በዘመናዊ አምልኮ ውስጥ ያለው ቦታ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 4/15 ገጽ 27

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ በወጡት የመጠበቂያ ግንብ እትሞች ላይ ያሉትን ሐሳቦች በጥንቃቄ አስበህባቸዋልን? እንግዲያውስ የሚከተሉትን ሐሳቦች ማስታወስህ ትኩረት የሚስብ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ:-

◻ በዛሬው ጊዜ ብዙ ባልና ሚስት አቂላና ጵርስቅላ ያሳዩትን ግሩም ምሳሌ የተከተሉት እንዴት ነው?

አቂላና ጵርስቅላ በተለያዩ ጉባኤዎች አገልግለዋል። በአሁኑ ጊዜም ብዙ ክርስቲያኖች ልክ እንደነርሱ ይበልጥ እርዳታ ወደሚያስፈልግበት ቦታ ተዛውረው ያገለግላሉ። የመንግሥቱ ሥራ እያደገ ሲሄድ ሲመለከቱና ውድ የሆነ ክርስቲያናዊ ወዳጅነት ሲያዳብሩ እነርሱም ደስታና እርካታ ያገኛሉ።​— 12/15፣ ገጽ 24

◻ መጽሐፍ ቅዱስ ለአልኮል መጠጦች ያለው አመለካከት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ለአልኮል መጠጦች ያለው አመለካከት ሚዛኑን የጠበቀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የወይን ጠጅ የአምላክ ስጦታ እንደሆነ ይናገራል። (መዝሙር 104:​1, 15) በሌላ በኩል ደግሞ ከመጠን በላይ መጠጣትን ያወግዛል። (ሉቃስ 21:​34፤ 1 ጢሞቴዎስ 3:​8፤ ቲቶ 2:​3፤ 1 ጴጥሮስ 4:​3)​— 12/15፣ ገጽ 27

◻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የሐጌ መጽሐፍ ትልቅ ትርጉም ያለው ገጽታ ምንድን ነው?

የሐጌ መጽሐፍ 38 ቁጥሮች ብቻ ያሉት ቢሆንም በውስጡ የአምላክ ስም 35 ጊዜ ተጠቅሷል። ይሖዋ የሚለውን ስም “ጌታ” በሚለው የማዕረግ ስም መተካት እንደዚህ ያሉት ትንቢቶች ለዛቸውን እንዲያጡ ማድረግ ነው።​— 1/1፣ ገጽ 6

◻ ዳዊትና ምናሴ ከሠሯቸው ኃጢአቶች ምን ትምህርት ልናገኝ እንችላለን?

ይሖዋ ዳዊትንና ምናሴን ይቅር ቢላቸውም እንኳ እነዚህ ሰዎችና እስራኤላውያን ኃጢአታቸው ካስከተለባቸው መጥፎ ውጤት የትም ሊያመልጡ አልቻሉም። (2 ሳሙኤል 12:​11, 12፤ ኤርምያስ 15:​3-5) በተመሳሳይም ምንም እንኳ ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር የሚላቸው ቢሆንም የፈጸሟቸው ድርጊቶች የሚያስከትሉባቸው የማይቀሩ ውጤቶች ሊኖሩ ይችላሉ።​— 1/1፣ ገጽ 27

◻ የአምላክን መንግሥት ‘ምሥራች የሚያውጁ ሰዎች’ እግሮቻቸው ‘ያማሩ’ የሆኑት በምን መንገድ ነው? (ኢሳይያስ 52:​7)

አንድ ሰው ለሌሎች ሰዎች ሲሰብክ የሚንቀሳቀሰው በእግሮቹ እንደሆነ የታወቀ ነው። እንደነዚህ ያሉት እግሮች ሰውዬውን ይወክላሉ። የመልእክተኞቹ እግሮች ምሥራቹን ሰምተው ለሚቀበሉ ብዙ ሰዎች ደስ የሚል እይታ እንደሆኑ እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን።​— 1/15፣ ገጽ 13

◻ ‘ምሥራቹን ማወጅ’ የሚጠይቀው ሁለት ገጽታ ያለው ሥራ ምንድን ነው? (1 ቆሮንቶስ 9:​16)

አንደኛ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብን። የዚህ ሥራ ሁለተኛው ገጽታ ለመንግሥቱ መልእክት አዎንታዊ ምላሽ ያሳዩትን ሰዎች ማስተማርን ይጨምራል።​— 1/15፣ ገጽ 23

◻ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር ምን ጥቅሞችን ያስገኛል?

መዝሙር ለፈጣሪያችን ያለንን ስሜት መግለጽ የምንችልበት አጋጣሚ ይሰጠናል። (መዝሙር 149:​1, 3) በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ከልባችን መዘመራችን አእምሯችንና ልባችን ለቀጣዩ ፕሮግራም ዝግጁ እንዲሆን ያደርጋል። በይሖዋ አምልኮም ይበልጥ እንድንካፈል ሊያነሳሳን ይችላል።​— 2/1፣ ገጽ 28

◻ ከመወለድ ቀን የሞት ቀን ይሻላል ሊባል የሚቻለው እንዴት ነው? (መክብብ 7:​1)

አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ በሞት ያንቀላፉትን የታመኑ ሰዎች ሊያስነሣ በሚችለው በይሖዋ ዘንድ ጥሩ ስም አትርፎ ከሆነ ከተወለደበት ቀን የሞተበት ቀን የተሻለ ሊሆን ይችላል። (ዮሐንስ 11:​25)​— 2/15፣ ገጽ 12

◻ የመክብብ መጽሐፍ በግለሰብ ደረጃ ሊጠቅመን የሚገባው ለምንድን ነው?

እያንዳንዳችን ስለ ሕይወት ያለንን አመለካከትና የትኩረት አቅጣጫችንን እንድናስተካክል ሊረዳን ይችላል። (መክብብ 7:​2፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:​16, 17)​— 2/15፣ ገጽ 16

◻ የይሖዋ ምሥክሮች ፋንዳሜንታሊስቶች ናቸውን?

አይደሉም። ጠንካራ ሃይማኖታዊ እምነቶች ቢኖራቸውም ዛሬ ካለው የቃሉ አጠቃቀም አንፃር ፋንዳሜንታሊስቶች ሊባሉ አይገባም። ከእነሱ ጋር የማይስማሙትን ወገኖች በመቃወም ትዕይንተ ሕዝብና ዓመፅ አያካሂዱም። መሪያቸው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይከተላሉ።​— 3/1፣ ገጽ 6

◻ ኢየሱስ የአምላክን የበቀል እርምጃ ለማስፈጸም የሚመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ አለማወቃቸው በክርስቲያኖች ላይ ምን ውጤት ያስከትላል?

ይህ ሁልጊዜ ንቁዎች እንድንሆንና ይሖዋን የምናገለግለው ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ስሜት እንደሆነ በየዕለቱ እንድናሳይ አጋጣሚ ይከፍትልናል።​— 3/1፣ ገጽ 13

◻ አንድ ወንድም እንዳጭበረበረን ከተሰማን ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ምን ማሰብ ይኖርብናል?

እርምጃችን በራሳችን፣ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሌሎች ሰዎች፣ በጉባኤውና በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ የሚያስከትለውን ውጤት ማጤን ይኖርብናል። (1 ቆሮንቶስ 6:​7)​— 3/15፣ ገጽ 22

◻ እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

እውነተኛ ደስታ የልብ ሁኔታ ነው፤ በእውነተኛ እምነትና ከይሖዋ ጋር ባለን ጥሩ ዝምድና የተመሠረተ ነው። (ማቴዎስ 5:​3)​— 3/15፣ ገጽ 23

◻ አንድ ክርስቲያን በእማኝ ዳኝነት እንዲያገለግል ጥሪ ቢቀርብለት ምን ማድረግ ይገባዋል?

በእማኝ ዳኝነት እንዲያገለግል የተጠራ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ ባገኘው ግንዛቤና በገዛ ሕሊናው በመመራት ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን ይኖርበታል። (ገላትያ 6:​5)​— 4/1፣ ገጽ 29

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ