የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 10/1 ገጽ 3-4
  • ‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክርስቲያኖች አምላክን በመንፈስና በእውነት ያመልካሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • እውነት ጊዜ ያለፈበት ነገር ሆኗል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • አምላክ ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • እውነትን መፈለግ ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 10/1 ገጽ 3-4

‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’

“እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል።” ኢየሱስ ኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ተሰብስቦ ለነበረው ብዙ ሕዝብ ሲያስተምር ይህን ገልጿል። (ዮሐንስ 8:​32 የ1980 ትርጉም) የኢየሱስ ሐዋርያት የእሱ ትምህርቶች እውነት መሆናቸውን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀባቸውም። መምህራቸው መለኮታዊ ምንጭ እንዳለው የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ተመልክተዋል።

ሆኖም ዛሬ አንዳንዶች ኢየሱስ የተናገረለት እውነት የትኛው እንደሆነ መለየት አዳጋች ሊሆንባቸው ይችላል። በነቢዩ ኢሳይያስ ዘመን እንደነበሩት ሰዎች ሁሉ በዛሬው ጊዜም ‘ክፉውን መልካም መልካሙን ክፉ የሚሉ፣ ጨለማውን ብርሃን ብርሃኑንም ጨለማ የሚያደርጉ፣ ጣፋጩን መራራ መራራውንም ጣፋጭ የሚያደርጉ’ ሰዎች አሉ። (ኢሳይያስ 5:​20) በዛሬው ጊዜ ብዙ ዓይነት አመለካከቶች፣ ፍልስፍናዎችና የአኗኗር ዘይቤዎች እየተስፋፉ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ሁሉም ነገር አንጻራዊ እንደሆነና እውነት የሚባል ነገርም እንደሌለ ይሰማቸዋል።

ኢየሱስ ለአድማጮቹ እውነት ነፃ እንደሚያወጣቸው ሲነግራቸው “የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ከቶ ባሪያዎች አልሆንም፤ አንተ:- አርነት ትወጣላችሁ አንዴት ትላለህ?” ሲሉ መልሰውለታል። (ዮሐንስ 8:​33) ነፃ የሚያወጣቸው ማንም ሰው ወይም ምንም ነገር እንደሚያስፈልጋቸው ሆኖ አልተሰማቸውም። ሆኖም ኢየሱስ በመቀጠል “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው” ሲል አብራራ። (ዮሐንስ 8:​34) ኢየሱስ እየተናገረለት የነበረው እውነት ከኃጢአት ነፃ የሚያወጣውን መንገድ ሊከፍት ይችላል። ኢየሱስ “ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ” ብሏል። (ዮሐንስ 8:​36) ስለዚህ ሰዎችን ነፃ የሚያወጣው እውነት የአምላክ ልጅ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገረው እውነት ነው። ማንኛውም ሰው ከኃጢአትና ከሞት ነፃ ሊሆን የሚችለው በኢየሱስ ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወት መሥዋዕት ላይ በማመን ብቻ ነው።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ኢየሱስ “በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው” ሲል ተናግሯል። (ዮሐንስ 17:​17) ከአጉል እምነትና ከሐሰት አምልኮ ነፃ ሊያወጣ የሚችለው እውነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሠፈረው የአምላክ ቃል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገልጽ እውነት ይዟል። ይህ እውነት ሰዎች በእሱ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ከማስቻሉም በላይ ወደፊት ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው መንገድ ይከፍታል። የአምላክን ቃል እውነት ማወቅ በጣም አስደሳች ነገር ነው!

እውነትን ማወቅ አስፈላጊነቱ ምን ያህል ነው? በዛሬው ጊዜ ያሉ ብዙ ሃይማኖቶች መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚከተሉ ቢናገሩም በአመዛኙ የሚመሩት በሰው ፍልስፍናዎችና ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ ልማድ ነው። አብዛኛውን ጊዜ የሃይማኖት መሪዎችን ይበልጥ የሚያሳስባቸው የሚያስተላልፉት መልእክት ትክክለኛ መሆን አለመሆኑ ሳይሆን በምዕመናኑ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት አለማግኘቱ ነው። አንዳንዶች ደግሞ አምልኮቱ ከልብ ይሁን እንጂ አምላክ ማንኛውንም አምልኮ ይቀበላል ብለው ያስባሉ። ይሁን እንጂ ኢየሱስ እንዲህ በማለት ገልጿል:- “በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና።”​—⁠ዮሐንስ 4:​23

አምላክን ተቀባይነት ባለው መንገድ ለማምለክ ከፈለግን እውነትን ማወቅ ይኖርብናል። ዘላቂ ደስታችን የተመካው እንዲህ በማድረጋችን ላይ ስለሆነ ይህ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ስለሆነም እያንዳንዱ ሰው ራሱን እንዲህ እያለ መጠየቅ ይገባዋል:- ‘አምልኮቴ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አለውን? የአምላክን ቃል እውነት የመማር ልባዊ ፍላጎት አለኝ? ወይስ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርምር ሊያሳውቀኝ የሚችለውን ነገር እፈራለሁ?’

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ