የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 10/1 ገጽ 4-6
  • አምላክን በእውነት ማምለክ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክን በእውነት ማምለክ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እውነትን ማወቅ ፍርሃትን ያስወግዳል
  • በጣም የተለየ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ‘በይሖዋ የሚታመኑ’ ወጣቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • የይሖዋ ምሥክሮች
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • ክርስቲያኖች አምላክን በመንፈስና በእውነት ያመልካሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 10/1 ገጽ 4-6

አምላክን በእውነት ማምለክ

አምልኮታችን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በእውነት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። (ዮሐንስ 4:​23) መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ አምላኪዎች “የእውነት ዓምድና መሠረት፣ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን [“ጉባኤ፣” NW]” አባላት እንደሆኑ ይገልጻል። (1 ጢሞቴዎስ 3:​15) የአምላክ ጉባኤ አባላት በአምላክ ቃል እውነት በማመን ብቻ አይወሰኑም፤ ከዚህ ይልቅ ከቃሉ ጋር በሚስማማ መንገድ ይኖራሉ እንዲሁም በምድር ዙሪያ እንዲዳረስ በማድረግ ለአምላክ ቃል ጥብቅና መቆማቸውን ያሳያሉ።​—⁠ማቴዎስ 24:​14፤ ሮሜ 10:​9–15

የይሖዋ ምሥክሮች በአሁኑ ጊዜ ከ200 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ እያከናወኑ ባሉት መጽሐፍ ቅዱስን የማስተማር ሥራ በይፋ የታወቁ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናሉ፤ እንዲሁም እውነት መሆኑን ስላመኑበት በሰብዓዊ ፍልስፍናዎች ሳይበርዙ ሳይከልሱ ለሌሎች ያስተምራሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተመሠረቱት ትምህርቶቻቸው ጋር ትውውቅ አለህ? ስለ ይሖዋ ምሥክሮች በሚነዛው አፍራሽ ወሬ የተነሳ ብዙዎች እነሱን ለማዳመጥ ያመነታሉ። ይሁን እንጂ ምሥክሮቹ የሚሰብኩት እውነትን መሆኑንና አለመሆኑን ለማረጋገጥ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች መርምረው የራሳቸውን ፍርድ እንዲሰጡ ግብዣ ቀርቦላቸዋል። እንዲህ ዓይነቱ ወሳኝ ፍርድ በአሉባልታ ላይ የተመሠረተ መሆን የለበትም። የይሖዋ ምሥክሮች የሚያስተምሯቸውን ትምህርቶች በግላቸው የመረመሩ ብዙ ሰዎች ከፍተኛ ጥቅም አግኝተውበታል።

እውነትን ማወቅ ፍርሃትን ያስወግዳል

ለምሳሌ ያህል የኤዩቼንያን ሁኔታ ተመልከት። ያደገችው አጥባቂ የካቶሊክ እምነት ተከታይ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ ነው። አባቷ በ1979 ሊቀ ጳጳሱ ሜክሲኮን እንዲጎበኙ ያደራጁ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ኤዩቼንያ ጓደኞቿን ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ተገናኘች። በእነሱ ድጋፍ አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ይበልጥ በጥንቃቄ መመርመር ጀመረች። እንዲህ በማለት ታስታውሳለች:- “መጀመሪያ ላይ በውስጤ ፍርሃት አደረብኝ። እውነትን አግኝቻለሁ! ይህ ማለት ግን በፊት የማምንባቸው አብዛኞቹ ነገሮች ስህተት ነበሩ ማለት ነው። የቤተሰቦቼ፣ የጓደኞቼና የምወዳቸው ሰዎች ሁሉ እምነት ስህተት ነው። ምን እንደማደርግ ጨነቀኝ። ቤተሰቦቼ ስለያዝኩት አዲስ እምነት ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን እያልኩ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ። የይሖዋ እርዳታ ታክሎበት ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ይህ የሚረብሸኝ ስሜት እየተስተካከለ መጣ። አንድ ቀን የቤተሰባችን ወዳጅ ለሆኑ አንድ የቲኦሎጂ ፕሮፌሰር ስለ ጉዳዩ በምሥጢር ልነግራቸው ወሰንኩ። እውነትን ለማግኘት ስላለኝ ፍላጎት አንድ በአንድ አጫወትኳቸው። ከዚያም ‘እውነትን ማወቅ ከፈለግሽ ወደ ይሖዋ ምሥክሮች ሂጂ’ አሉኝ።”

ኤዩቼንያ የፈራችው አልቀረም ቤተሰቦቿ ከቤት አባረሯት። ይሁን እንጂ ምሥክሮቹ መንፈሳዊ ድጋፍ መስጠታቸውን ቀጠሉ። እንዲህ ስትል ትገልጻለች:- “ለእውነት የጸና አቋም እንድወስድ ጥንካሬ አገኘሁ። ሊጋደሉለት የሚገባ ነገር እንደሆነ ተገነዘብኩ። የይሖዋ ምሥክሮች ያደረጉልኝ እንክብካቤ እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ተፈላጊ እንደሆንኩ ተሰማኝ። ወደ አምላክ ድርጅት ተጠግቼ መኖሬ ያለ ቤተሰቦቼ ድጋፍ በእውነት ውስጥ ጸንቼ እንድቆም አስችሎኛል።”

ሌላም ምሳሌ ተመልከት። ሳብሪና ያደገችው በቤተሰብ መልክ ዘወትር የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይቶች የማድረግ ልማድ አዳብራ ነው። እንዲያውም ‘የቤተሰብ ሃይማኖት’ የሚባል ነገር አቋቁመው ነበር። ስህተቶቻቸውን ለማጋለጥ ስትል የተለያየ ሃይማኖት አባል ከሆኑ ሰዎች ጋር መቀራረብ ሥራዬ ብላ ተያይዛው ነበር። አንድ የይሖዋ ምሥክር መጽሐፍ ቅዱስ እንድታጠና ሐሳብ ሲያቀርብላት እምነታቸው ስህተት መሆኑን ለማጋለጥ በማሰብ ግብዣውን ምንም ሳታቅማማ ተስማማች። እንዲህ በማለት ታስታውሳለች:- “ከአንድ ዓመት በላይ ካጠናሁ በኋላ ‘የራሴን እውነት’ እንዳልለቅቅ ስጋት አደረብኝ። ከዚህ ቀደም በሄድኩባቸው አብዛኞቹ ሃይማኖቶች ማታለያዎቻቸው ምን እንደሆኑ መለየት ምንም አልቸገረኝም ነበር። ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ሳጠና ግን ሁኔታው እንደዚያ አልነበረም።”

ሳብሪና ያደረባት ስጋት ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ታደርግ የነበረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንድታቋርጥ አደረጋት። ሆኖም እንዲህ ካደረገች በኋላ በመንፈሳዊ ባዶ እንደሆነች ተሰማት። ጥናቷን ለመቀጠል ወሰነችና ከጊዜ በኋላ ይህን አዲስ ያገኘችውን እውነት ተቀበለች። እንዲያውም ሳብሪና የተማረችውን ነገር ለሌሎች ለማካፈል እስከመፈለግ ደረሰች። አልፎ ተርፎም ምሥክሮቹ ከቤት ወደ ቤት በሚያደርጉት አገልግሎት አብራቸው ለመሄድ ጠየቀች። ሳብሪና እንዲህ በማለት ትገልጻለች:- “ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር እንድሰብክ መብት ከማግኘቴ በፊት ‘በእርግጥ ከይሖዋ ምሥክሮች እንደ አንዷ ለመሆን ትፈልጊያለሽ?’ የሚል ጥያቄ ቀረበልኝ። ‘አልፈልግም!’ ስል መለስኩ። እንደገና በውስጤ ስጋት አደረብኝ።” በመጨረሻም ሳብሪና በሁሉም ስብሰባዎች ላይ መገኘቷን ከቀጠለችና የአምላክ ሕዝቦች የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች እንዴት በሥራ ላይ እንደሚያውሉ በጥሞና ካጤነች በኋላ በእርግጥም ይህ እውነት መሆኑን ወደ መደምደም ደረጃ ደረሰች። ከጊዜ በኋላ የተጠመቀች ሲሆን አሁን የሙሉ ጊዜ ወንጌላዊ ነች።

በጣም የተለየ የሆነው ለምንድን ነው?

አንዳንዶች ‘የይሖዋ ምሥክሮች የሚያስተምሩት ትምህርት ከሌሎች ሃይማኖቶች በጣም የተለየ የሆነው ለምንድን ነው?’ ብለው ይጠይቁ ይሆናል። ምሥክሮቹ ምን ብለው እንደሚያምኑ በአጭሩ መመልከቱ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ የሚያጠኑ ሐቀኛ ክርስቲያኖች መሆናቸውን እንድትገነዘብ ይረዳሃል። ከላይ ጠቅለል ባለ መልኩ የቀረቡትን መሠረታዊ እምነቶቻቸውን የያዙትን ጥቅሶች ከራስህ መጽሐፍ ቅዱስ አውጥተህ እንድታነብ እናበረታታሃለን።

የይሖዋ ምሥክሮች ምን ብለው እንደሚያምኑና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ሁሉ እንዴት በጥብቅ እንደሚከተሉ ቀረብ ብለህ በመመልከት እውነት በሚያስገኘው ነፃነት መደሰት ትችላለህ። (ዮሐንስ 17:​17) እውነትን የምትፈራበት አንዳችም ምክንያት የለም። ኢየሱስ “እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል” ሲል የገባውን ቃል አስታውስ።​—⁠ዮሐንስ 8:​32 የ1980 ትርጉም

[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

የይሖዋ ምሥክሮች የሚያምኑባቸው መሠረታዊ ነገሮች

◯ ይሖዋ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው። የግል ስሙ በእጅ በተጻፉ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ ከ7,000 ጊዜ በላይ ይገኛል።​—⁠መዝሙር 83:​18 NW

◯ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ለሰው ልጆች ለመስጠት ሲል ወደ ምድር የመጣ የአምላክ ልጅ ነው። (ዮሐንስ 3:​16, 17) የይሖዋ ምሥክሮች በወንጌሎች ውስጥ የሚገኙትን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶች ይከተላሉ።

◯ የይሖዋ ምሥክሮች የሚለው ስም በኢሳይያስ 43:​10 [NW] ላይ የተመሠረተ ሲሆን ጥቅሱ “እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል ይሖዋ” በማለት ይገልጻል።

◯ ሰዎች “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ላይ እንዲመጣ የሚጸልዩለት መንግሥት በሰማይ ያለ መስተዳድር ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ በዓለም ላይ ያለውን ችግርና ሰቆቃ በሙሉ በማስወገድ መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ ለሚሰጠው ገነት መንገድ ይከፍታል።​—⁠ኢሳይያስ 9:​6, 7፤ ዳንኤል 2:​44፤ ማቴዎስ 6:​9, 10፤ ራእይ 21:​3, 4

◯ የአምላክን ፈቃድ የሚያደርግ ማንኛውም ሰው የአምላክ መንግሥት በሚያመጣቸው በረከቶች ለዘላለም የመደሰት አጋጣሚ አለው።​—⁠ዮሐንስ 17:​3፤ 1 ዮሐንስ 2:​17

◯ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው መሠረት ባሕርያቸውን መቅረጽ አለባቸው። ሐቀኛ ለመሆን፣ በሥነ ምግባር ንጹሕ የሆነ ሕይወት ለመምራትና ባልንጀሮቻቸውን ለመውደድ ጥረት ማድረግ አለባቸው።​—⁠ማቴዎስ 22:​39፤ ዮሐንስ 13:​35፤ 1 ቆሮንቶስ 6:​9, 10

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የይሖዋ ምሥክሮች ከ200 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ያሳውቃሉ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ