የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 5/1 ገጽ 3-4
  • ሁሉም ሰው ነፃ መሆንን ይሻል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሁሉም ሰው ነፃ መሆንን ይሻል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አሁንም “በባርነት ቀንበር” ሥር ይገኛል
  • ነፃ፣ ግን ተጠያቂነት ያለበት ሕዝብ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ይሖዋ ወደ እውነተኛው ነፃነት ይምራችሁ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • የነፃነት አምላክ የሆነውን ይሖዋን አገልግሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018
  • ከአምላክ የሚሰጠውን ነፃነት ዓላማ አትሳቱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 5/1 ገጽ 3-4

ሁሉም ሰው ነፃ መሆንን ይሻል

“የሰው ልጅ ነፃ ሆኖ ይወለድ እንጂ በየትኛውም ሥፍራ በባርነት ቀንበር ሥር ይገኛል” ሲል ፈረንሳዊው ፈላስፋ ዣን-ዣክ ሩሶ በ1762 ጽፏል። ነፃ ሆኖ መወለድ። እንዴት ደስ ይላል! ዳሩ ምን ያደርጋል ሩሶ እንደተናገረው በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በታሪክ ዘመናት በሙሉ ነፃነት የሚባል አግኝተው አያውቁም። ከዚህ ይልቅ ዘላቂ ደስታና እርካታ በሚነፍግ ሥርዓት ውስጥ “በባርነት ቀንበር ሥር” ኑሯቸውን ይገፋሉ።

በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዛሬም እንኳ ቢሆን ‘ሰው ሰውን የገዛው ለጉዳቱ መሆኑን’ እየተመለከቱ ነው። (መክብብ 8:​9) የሥልጣን ጥማቸውን ለማርካት የሚሯሯጡ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የሌሎችን ነፃነት ስለ መጋፋት ቅንጣት ታክል ደንታ የላቸውም። አንድ ዓይነተኛ ዘገባ “ፈጥኖ ደራሽ ረሻኝ ጓዶች 21 ሰዎችን ገደሉ” ይላል። ሌላው ደግሞ ‘ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሴቶችን፣ ሕፃናትንና አረጋውያንን የሚገድሉ፣ የሰዎችን አንገት የሚቀሉ፣ የሲቪል እስረኞችን ጭንቅላት በጥይት የሚመቱ እንዲሁም መንደሮችን የሚያወድሙና በመድፍ የሚደበድቡ’ የጸጥታ አስከባሪዎች ስለሚያካሂዱት “የጅምላ ጭፍጨፋ” ይናገራል።

ሰዎች ከጭቆና ለመላቀቅ ቢናፍቁና ለነፃነት ቢታገሉ ምንም አያስደንቅም! የሚያሳዝነው ሐቅ ግን ሰዎች ለነፃነት የሚያደርጉት ትግል አብዛኛውን ጊዜ የሌሎች ሰዎችን መብትና ነፃነት የሚጋፋ መሆኑ ነው። በዚህ መሃል ብዙ ንጹሐን ወንዶች፣ ሴቶችና ሕፃናት መሠዋታቸው የማይቀር ነው። ትግሉ ትክክለኛና ፍትሃዊ እስከሆነ ድረስ ንጹሐን ዜጎች ማለቃቸው የግድ ትግሉ “የሚጠይቀው” ነገር እንደሆነ ተደርጎ ይታያል። ለምሳሌ ያህል ባለፈው ዓመት በአየርላንድ በምትገኘው በትንሿ የኦማ መንደር “የነፃነት ታጋዮች” በመኪና ላይ ያጠመዱት ቦምብ ፈንድቶ በአካባቢው የነበሩ 29 ሰዎችን የገደለ ሲሆን በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን አቁስሏል።

አሁንም “በባርነት ቀንበር” ሥር ይገኛል

ውጊያው ሲጠናቀቅ የሚገኘው ትርፍ ምንድን ነው? “የነፃነት ታጋዮች” በውጊ​ያው ሲያሸንፉ የተወሰነ መጠን ያለው ነፃነት ይገኝ ይሆናል። ይሁንና በእርግጥ ነፃ ናቸውን? ሌላው ቀርቶ ነፃ በሚባለው ዓለም ውስጥ በሚገኙ ኅብረተሰቦች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች አሁ​ንም እንኳ ቢሆን ድህነትን፣ አለፍጽምናን፣ በሽታንና ሞትን በመሳሰሉ ጨካኝ ጌቶች “የባርነት ቀን​በር” ሥር አይደሉምን? አንድ ሰው እነዚህን ለመሳሰሉ ነገሮች ባሪያ ሆኖ ሳለ እንዴት ነፃ ነኝ ሊል ይችላል?

የጥንቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ሙሴ ባለፉት የታሪክ ዘመናትም ሆነ ዛሬ የብዙ ሰዎች ሕይወት ምን እንደሚመስል በትክክል ገል​ጿል። ግፋ ቢል ለ70 ወይም ለ80 ዓመታት እንኖር ይሆናል፤ ከዚያ “ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው” ብሏል። (መዝሙር 90:​10) ይህ ሁኔታ ይለወጥ ይሆን? ሁላችንም በዛሬው ጊዜ ብዙዎች ካለባቸው ሥቃይና ፍርሃት ነፃ የሆነ አርኪ ሕይወት እናገኝ ይሆን?

መጽሐፍ ቅዱስ አዎን የሚል መልስ ይሰጣል! መጽሐፍ ቅዱስ ‘ስለ አምላክ ልጆች ክብራማ ነፃነት’ ይናገራል። (ሮሜ 8:​21) ሐዋርያው ጳውሎስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በሮማ ለሚገኙ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ የተናገረለትን ነፃነት እስቲ በጥልቀት እንመርምር። ጳውሎስ በዚህ ደብዳቤ ላይ እያንዳንዳችን እውነተኛና ዘላቂ የሆነ “ክብራማ ነፃነት” እንዴት ልናገኝ እንደምንችል ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ሰጥቷል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

From the book Beacon Lights of History, Vol. XIII

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ