የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 7/15 ገጽ 24-25
  • ፊልጶስ ቀናተኛ ወንጌላዊ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፊልጶስ ቀናተኛ ወንጌላዊ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዳዲስ የአገልግሎት ክልሎች መክፈት
  • የፊልጶስ ተጨማሪ መብቶች
  • “ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች” ማወጅ
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • የአቅኚነት መንፈስ አሳዩ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ፊልጶስ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለ ሥልጣን አጠመቀ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • ተፈጥሯዊ አነጋገር
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 7/15 ገጽ 24-25

ፊልጶስ ቀናተኛ ወንጌላዊ

ቅዱሳን ጽሑፎች ሊኮረጅ የሚገባው እምነት ያላቸው የብዙ ወንዶችንና ሴቶችን ታሪኮች ይዘዋል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያን ሚስዮናዊ የነበረውን ፊልጶስን እንውሰድ። ሐዋርያ የነበረ ባይሆንም የመንግሥቱን መልእክት በማሰራጨት በኩል ግን ብዙ ሠርቷል። እንዲያውም ፊልጶስ የሚታወቀው “ወንጌላዊው” በመባል ነበር። (ሥራ 21:​8) ፊልጶስ ይህንን ስያሜ ያገኘው ለምን ነበር? ከእሱስ ምን ልንማር እንችላለን?

ፊልጶስ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ብቅ ያለው በ33 እዘአ ከዋለው የጰንጤቆስጤ ዕለት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ነው። በዚያን ጊዜ ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑት አይሁዶች በዕለት የምግብ ክፍፍል በኩል መበለቶቻቸው ችላ እንደተባሉ በመግለጽ ዕብራይስጥ ተናጋሪ በሆኑት አይሁዶች ላይ ማጉረምረም ጀምረው ነበር። ይህን ጉዳይ እንዲይዙት ሐዋርያት “የተመሰከረላቸውን . . . ሰባት ሰዎች” ሾሙ። ከተመረጡት መሀል አንዱ ፊልጶስ ነበር።​—⁠ሥራ 6:​1-6

እነዚህ ሰባት ሰዎች “የተመሰከረላቸው” ነበሩ። የጄምስ ሞፋት ትርጉም “መልካም ስም የነበራቸው” ብሎታል። አዎን፣ በተሾሙበት ጊዜም ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ ያላቸው መንፈሳዊ ሰዎች መሆናቸው የተመሰከረላቸው ነበሩ። ዛሬ ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች ሆነው የሚያገለግሉት ሁኔታም ተመሳሳይ ነው። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እንዲሁ በችኮላ አይሾሙም። (1 ጢሞቴዎስ 5:​22) “በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር” ሊኖራቸውና መሰል ክርስቲያኖችም እነሱ ምክንያታዊና ራሳቸውን የሚገዙ መሆናቸውን ሊያውቁ ይገባል።​—⁠1 ጢሞቴዎስ 3:​2, 3, 7፤ ፊልጵስዩስ 4:​5

ፊልጶስ በኢየሩሳሌም የተሰጠውን ሥራ በሚገባ እንደተወጣ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። ቢሆንም ግን ወዲያውኑ ከባድ ስደት ተነሳና የክርስቶስ ተከታዮች ተበታተኑ። እንደ ሌሎቹ ሁሉ ፊልጶስም ከተማይቱን ለቆ ሄደ፤ ሆኖም አገልግሎቱ በዚያ አላበቃም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአዲስ ክልል ውስጥ ማለትም በሰማርያ በስብከቱ ሥራ ተጠምዶ ነበር።​—⁠ሥራ 8:​1-5

አዳዲስ የአገልግሎት ክልሎች መክፈት

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ “በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ” እንደሚሰብኩ አስቀድሞ ተናግሯል። (ሥራ 1:​8) ፊልጶስ በሰማርያ በመስበኩ እነዚህ የኢየሱስ ቃላት ፍጻሜያቸውን እንዲያገኙ አስተዋፅኦ አድርጓል። አይሁዶች ባጠቃላይ የሰማርያን ሰዎች ዝቅ አድርገው ይመለከቷቸው ነበር። ፊልጶስ ግን በእነዚህ ሰዎች ላይ አስቀድሞ አልፈረደም፤ ሳያዳላ በመስበኩም በረከት አግኝቷል። ጠንቋይ የነበረውን ሲሞንን ጨምሮ ብዙ የሰማርያ ሰዎች ተጠምቀዋል።​—⁠ሥራ 8:​6-​13

ከጊዜ በኋላ የይሖዋ መልአክ ፊልጶስን ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያመራው የምድረ በዳ መንገድ እንዲሄድ አዘዘው። በዚያም ፊልጶስ በሰረገላ ላይ ተቀምጦ የኢሳይያስን ትንቢት ጮክ ብሎ ያነብ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሥልጣን ተመለከተ። ፊልጶስም ከሰረገላው ጎን እየሮጠ ውይይት ጀመረ። ምንም እንኳን ይህ ኢትዮጵያዊ ወደ ይሁዲነት የተለወጠና ስለ አምላክም ሆነ ስለ ቅዱሳን ጽሑፎች የተወሰነ እውቀት ያለው ቢሆንም የሚያነበውን ነገር ለመረዳት እርዳታ እንደሚያስፈልገው በትህትና አመነ። በመሆኑም ፊልጶስን ሰረገላው ላይ ወጥቶ ከሱ ጋር እንዲቀመጥ ጋበዘው። ከተመሰከረለትም በኋላ ውኃ ያለበት ቦታ ደረሱ። ኢትዮጵያዊውም “እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነው?” በማለት ጠየቀ። ፊልጶስም ወዲያውኑ አጠመቀው፣ ኢትዮጵያዊውም ደስ እያለው መንገዱን ቀጠለ። ይህ አዲስ ደቀ መዝሙር ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶ ምሥራቹን እንዳስፋፋ ምንም አያጠራጥርም።​—⁠ሥራ 8:​26-​39

የሰማርያን ሰዎችና ኢትዮጵያዊውን ባለሥልጣን በተመለከተ ፊልጶስ ካከናወነው አገልግሎት ምን እንማራለን? ሰዎችን በዜግነታቸው፣ በዘራቸው፣ ወይም በማኅበረሰቡ ውስጥ ባላቸው ቦታ የተነሳ ለምሥራቹ ፍላጎት አይኖራቸውም ብለን መገመት አይኖርብንም። ከዚህ ይልቅ የመንግሥቱን መልእክት “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች” ማወጅ ይኖርብናል። (1 ቆሮንቶስ 9:​19-​23 NW) ለሁሉም ሰዎች ለመስበክ ራሳችንን ካዘጋጀን የዚህ ክፉ ሥርዓት መጨረሻ ከመምጣቱ በፊት ይሖዋ ‘አሕዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት በማድረጉ’ ሥራ ሊጠቀምብን ይችላል።​—⁠ማቴዎስ 28:​19, 20

የፊልጶስ ተጨማሪ መብቶች

ለኢትዮጵያዊው ባለሥልጣን ከሰበከ በኋላ ፊልጶስ በአዛጦን ውስጥ ምሥክርነት ሰጥቷል። ከዚያ “ወደ ቂሣርያም እስኪመጣ ድረስ እየዞረ በከተማዎች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።” (ሥራ 8:​40) በመጀመሪያው መቶ ዘመን እነዚህ ሁለት ከተማዎች ብዙ አሕዛብ የሚኖርባቸው ነበሩ። በስተ ሰሜን ወደ ቂሣርያ ሲሄድ ፊልጶስ ልዳን እና ኢዮጴን በመሳሰሉት የአይሁድ ዋነኛ ማዕከሎች ሳይሰብክ አልቀረም። ምናልባትም ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ቆየት ብሎ በእነዚህ አካባቢዎች ደቀ መዛሙርት ሊገኙ የቻሉት።​—⁠ሥራ 9:​32-​43

ፊልጶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተጠቀሰው ከ20 ዓመታት በኋላ ነው። በሦስተኛው ሚስዮናዊ ጉዞው መጨረሻ ላይ ጳውሎስ በጴጤሌማይስ አርፎ ነበር። የጳውሎስ የጉዞ ጓደኛ ሉቃስ “በነገውም ወጥተን ወደ ቂሣርያ መጣን . . . በወንጌላዊው ፊልጶስ ቤት ገብተን በእርሱ ዘንድ ተቀመጥን” ይላል። በዚህ ጊዜ ፊልጶስ “ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።”​—⁠ሥራ 21:​8, 9

በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ፊልጶስ በቂሣርያ ቋሚ ኑሮ መሥርቶ ነበር። ቢሆንም ግን ሉቃስ “ወንጌላዊው” ብሎ ስለጠራው የሚስዮናዊነት መንፈሱ አልጠፋም ነበር። ይህ አገላለጽ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው ምሥራቹን ለመስበክ ሲል ቤቱን ትቶ ወዳልተሠራባቸው የአገልግሎት ክልሎች የሚሄድን ሰው ነው። ፊልጶስ ትንቢት የሚናገሩ አራት ሴቶች ልጆች ያሉት መሆኑ እነሱም የቀናተኛውን አባታቸውን ፈለግ እንደተከተሉ ያሳያል።

በዘመናችን ያሉ ክርስቲያን ወላጆችም ልጆቻቸው የእነሱ ዋነኛ ደቀ መዛሙርት መሆናቸውን ማስታወስ ይኖርባቸዋል። ምንም እንኳን እንደዚህ ያሉ ወላጆች በቤተሰብ ኃላፊነት የተነሳ አንዳንድ ቲኦክራሲያዊ መብቶችን መተው ቢኖርባቸውም ልክ እንደ ፊልጶስ እነሱም አምላክን በሙሉ ልብ የሚያገለግሉና ምሳሌ የሚሆኑ ወላጆች ሊሆኑ ይችላሉ።​—⁠ኤፌሶን 6:​4

የጳውሎስና የጓደኞቹ ጉብኝት እንግዳ ተቀባይነትን እንዲያሳዩ ለፊልጶስ ቤተሰቦች ጥሩ አጋጣሚ ሰጥቷቸዋል። ምን ያህል እርስ በርስ ተበረታተው እንደነበር ልትገምት ትችላለህ! ምናልባትም ሉቃስ በኋላ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 6 እና 8 የተጨመሩትን ፊልጶስ የሠራቸውን ሥራዎች ዝርዝር የሰበሰበው በዚህ አጋጣሚ ሳይሆን አይቀርም።

ይሖዋ አምላክ የመንግሥቱን ጥቅም ለማራመድ ፊልጶስን በሰፊው ተጠቅሞበታል። የፊልጶስ ቅንዓት ምሥራቹን ወደ አዳዲስ የአገልግሎት ክልሎች ለማሰራጨትና በቤተሰቡም ውስጥ ጤናማ የሆነ መንፈሳዊ ሁኔታ ለማዳበር ረድቶታል። አንተም ተመሳሳይ የሆኑ መብቶችና በረከቶች አግኝተህ ለመደሰት ትፈልጋለህ? ከሆነ የወንጌላዊው ፊልጶስን ባሕርያት ለመኮረጅ ጣር።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ