የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/04 ገጽ 10
  • የአቅኚነት መንፈስ አሳዩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአቅኚነት መንፈስ አሳዩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፊልጶስ ቀናተኛ ወንጌላዊ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • “ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች” ማወጅ
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • የአቅኚነት አገልግሎት የሚያስገኛቸው በረከቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ተፈጥሯዊ አነጋገር
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2004
km 8/04 ገጽ 10

የአቅኚነት መንፈስ አሳዩ

1 ሁሉም የመንግሥቱ አስፋፊዎች አሁን አቅኚዎች ሆነው ለማገልገል ሁኔታቸው ቢፈቅድላቸውም ባይፈቅድላቸውም የአቅኚነት መንፈስ ማሳየት ይችላሉ። እንድንሰብክና ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ የተሰጠንን ትእዛዝ ለመፈጸም ልባዊ ፍላጎት አላቸው። (ማቴ. 28:​19, 20፤ ሥራ 18:​5) ስለ ሰዎች ደኅንነት ስለሚያስቡ አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ሲሉ መሥዋዕትነት ይከፍላሉ። (ማቴ. 9:​36፤ ሥራ 20:​24) የይሖዋ አገልጋዮች ሌሎች እውነትን እንዲማሩ ለመርዳት አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኞች ናቸው። (1 ቆ⁠ሮ. 9:​19-23) እንደዚህ ዓይነት መንፈስ ካሳዩ የአምላክ አገልጋዮች አንዱ የሆነውን የወንጌላዊውን ፊልጶስን ምሳሌ እንመልከት።

2 መስበክና ማስተማር፦ ፊልጶስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን በነበረው የክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ከበድ ያሉ ኃላፊነቶች ነበሩት። (ሥራ 6:​1-6) ያም ሆኖ ዋነኛ ተግባሩ ምሥራቹን በቅንዓት መስበክ ነበር። (ሥራ 8:​40) ዛሬም ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች በጉባኤ ውስጥ የተሰጣቸውን ኃላፊነት መወጣት ቢኖርባቸውም በአገልግሎቱ ግንባር ቀደም ሆነው በቅንዓት በመካፈል የአቅኚነት መንፈስ ሊያሳዩ ይችላሉ። እንዲህ ማድረጋቸው ጉባኤውን በጣም ያበረታታል!​—⁠ሮሜ 12:​11

3 እስጢፋኖስ ከሞተ በኋላ የተነሳው የስደት ማዕበል የደቀ መዛሙርቱን ሕይወት አመሰው። ይሁን እንጂ ፊልጶስ መስበኩን አላቋረጠም። ለሳምራውያን በመስበክ ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል። (ሥራ 8:1, 4-6, 12, 14-17) ችግሮች ሲያጋጥሙንም እንኳ ምሥራቹን መስበካችንን ባለማቋረጥ እንዲሁም ለምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ ሳናዳላ በመስበክ የእርሱን ምሳሌ መከተል እንችላለን።​—⁠ዮሐ. 4:​9

4 ፊልጶስ የአምላክን ቃል በማስተማር ረገድ ጥሩ ችሎታ እንደነበረው ከኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ጋር ስላደረገው ውይይት ከሚገልጸው ዘገባ መረዳት ይቻላል። (ሥራ 8:​26-38) የአቅኚነት መንፈስ ማሳየት የምንችልበት ሌላው መንገድ በመጽሐፍ ቅዱስ የመጠቀምና ‘ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሱ’ የማስረዳት ችሎታችንን በማዳበር ነው። (ሥራ 17:2, 3) እንደ ፊልጶስ እኛም ሰዎች በሚገኙበት በማንኛውም ቦታና ምቹ በሆነ አጋጣሚ ሁሉ ምሥራቹን ልንነግራቸው እንጥራለን።

5 ቤተሰብና ጉባኤ፦ የፊልጶስ አመለካከትና ምሳሌነቱ በሴቶች ልጆቹ ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ምንም ጥርጥር የለውም። (ሥራ 21:​9) በተመሳሳይም ወላጆች ሕይወታቸው በመንግሥቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንዲሆን ጥረት የሚያደርጉ ከሆነ ልጆቻቸውም እንዲሁ እንዲያደርጉ ያበረታቷቸዋል። ወላጆች ሳምንቱን በሥራ ተወጥረው ስለሚያሳልፉ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ሊደክማቸው ቢችልም በቅንዓት የሚሰብኩ ከሆነ የስብከቱን ሥራ አስፈላጊነት በልጆቻቸው ልብ ውስጥ በማይጠፋ መንገድ መቅረጽ ይችላሉ።​—⁠ምሳሌ 22:​6

6 ፊልጶስ በይሖዋ አገልግሎት ተግተው ይካፈሉ የነበሩትን ቀናተኛ ክርስቲያኖች ይኸውም ጳውሎስንና ሉቃስን በእንግድነት ተቀብሎ ነበር። (ሥራ 21:​8, 10) በዛሬው ጊዜ ምሥራቹን በቅንዓት ለሚሰብኩት ወንድሞች ያለንን አድናቆት ማሳየትና እነርሱን መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው? አገልግሎት የሚወጡ ብዙ አስፋፊዎች በማይኖሩበት ቀን ጠዋት ላይ ወይም ከሰዓት በኋላ ከአቅኚዎች ጋር አብረን ልናገለግል እንችላለን። (ፊልጵ. 2:​4) ከዚህም በላይ ቤታችን ጋብዘናቸው የሚያንጽ ጭውውት ማድረግ እንችላለን። ሁላችንም ሁኔታችን ምንም ይሁን ምን የአቅኚነት መንፈስ ለማሳየት ጥረት እናድርግ።

[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]

1. የአቅኚነት መንፈስ በምን መንገዶች ይገለጻል?

2. ሽማግሌዎችና የጉባኤ አገልጋዮች በአገልግሎት ረገድ የፊልጶስን የቅንዓት ምሳሌ መኮረጅ የሚችሉት እንዴት ነው?

3. ችግሮች ሲያጋጥሙን የአቅኚነት መንፈስ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

4. ፊልጶስ በአስተማሪነት ረገድ ምን አርዓያ ትቶልናል?

5. ክርስቲያን ወላጆች በልጆቻቸው ልብ ውስጥ የአቅኚነትን መንፈስ ለመቅረጽ ምን ማድረግ ይችላሉ?

6. በጉባኤያችን ያሉትን አቅኚዎች እንደምናደንቃቸው እንዴት ማሳየት እንችላለን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ