የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w99 10/1 ገጽ 3-4
  • ጊዜ እንዲህ አጭር የሆነው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጊዜ እንዲህ አጭር የሆነው ለምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የተትረፈረፈ ጊዜ
  • እያጠረ የሚሄድ ጊዜ
  • ጊዜ አጭር የሆነብን እኛ ብቻ አይደለንም
  • አሁን ያለንን ጊዜ በጥበብ መጠቀም
  • ይሖዋ ዕድሜያችንን እንዴት እንደምንቆጥር ያስተምረናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ስለ ጊዜና ስለ ዘላለማዊነት የምናውቀው ምን ያህል ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ዘላለማዊነትን በማሰብ አካሄድን ከአምላክ ጋር ማድረግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • የዘላለሙን ንጉሥ አወድሱ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
w99 10/1 ገጽ 3-4

ጊዜ እንዲህ አጭር የሆነው ለምንድን ነው?

ጊዜ ለሚለው ቃል ትክክለኛ ፍቺ ለመስጠት እንቸገር ይሆናል። ሆኖም ዘወትር ጊዜ እንደሚያጥረን ሆኖ ይሰማናል። እንዲሁም በፍጥነት እንደሚያልፍ እናውቃለን። እንዲያውም ብዙውን ጊዜ “እንዲያው ጊዜው ይከንፋል” ብለን እናዝናለን።

ያም ሆኖ ግን በ1877 እንግሊዛዊው ገጣሚ አውስቲን ዶብሶን እንደሚከተለው በማለት በመጠኑም ቢሆን ወደ ሐቁ የሚጠጋ ነገር ተናግሮ ነበር:- “አዬ፣ ጊዜ ያልፋል አላችሁ? የለም! ጊዜስ እንዳለ ነው፣ የምናልፈው እኛ ነን።” ዶብሶን በ1921 ከሞተ በኋላ ወደ 80 የሚጠጉ ዓመታት አልፈዋል፤ ጊዜ ግን እንዳለ ነው።

የተትረፈረፈ ጊዜ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው ዘር ፈጣሪ እንዲህ ይለናል:- “ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።” (መዝሙር 90:​2) ስለዚህ ጊዜም እንደ አምላክ ለዘላለም ይኖራል!

ወሰን የሌለው ጊዜ ባለቤት ከሆነው አምላክ በተቃራኒ ስለ ሰዎች እንዲህ እናነባለን:- “ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፣ እኛም በመዓትህ አልቀናልና፤ ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይሆናሉ። የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፣ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው። ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፣ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፣ እኛም እንገሠጻለንና [“እናልፋለን፣” የ1980 ትርጉም]።”​—⁠መዝሙር 90:​9, 10

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያስተምረው ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም እንዲኖሩ የአምላክ ዓላማ ሆኖ ሳለ በዛሬው ጊዜ ሕይወት እንዲህ አጭር የሆነው ለምንድን ነው? (ዘፍጥረት 1:​27, 28፤ መዝሙር 37:​29) የሰው ልጅ እንደ አምላክ ዓላማ ገደብ ለሌለው ጊዜ በሕይወት መኖሩ ቀርቶ ግፋ ቢል በአማካይ ከ30,000 ለሚያንሱ ቀናት ብቻ የሚኖረው ለምንድን ነው? የሰው ዘር ያለው ጊዜ እንዲህ አጭር የሆነው ለምንድን ነው? ለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ተጠያቂው ማን ወይም ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽና አርኪ መልስ ይሰጣል።a

እያጠረ የሚሄድ ጊዜ

በዕድሜ የገፉ ሰዎች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኑሮ ውክቢያ የበዛበት እየሆነ እንደመጣ ይናገራሉ። ዶክተር ዚቢል ፍሪክ የተባሉ ጋዜጠኛ ባለፉት 200 ዓመታት ውስጥ የአንድ ሳምንት የሥራ ቀናት ከ80 ወደ 38 ሰዓታት ዝቅ ማለታቸውን ከገለጹ በኋላ “ይሁንና ይህ ማማረራችንን እንድናቆም አላደረገም” ብለዋል። ይህንንም ሲያብራሩ “ጊዜ የለም፤ ጊዜ ገንዘብ ነው፤ ጊዜ እንደ እስትንፋስ አጥሮናል፤ ሕይወታችን በሩጫና በጥድፊያ የተሞላ ነው” እንደምንል ገልጸዋል።

አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶች ቀደም ሲል የነበሩ ትውልዶች ሊያገኟቸው ቀርቶ ሊያልሟቸው የማይችሏቸውን አጋጣሚዎችና አመቺ ሁኔታዎች ፈጥረዋል። ይሁን እንጂ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች የመካፈል አጋጣሚው በጨመረ ቁጥር እነዚህን ነገሮች ለማከናወን የሚያስችል በቂ ጊዜ አለመኖሩ ለከፍተኛ ብስጭት ይዳርጋል። በአሁኑ ጊዜ በብዙ የዓለም ክፍሎች ሰዎች የሚንቀሳቀሱት በማያፈናፍን ፕሮግራም ነው። አባባ ጠዋት በ1:​00 ሰዓት ሥራ መሄድ አለበት፤ እማማ በ2:​30 ልጆቹን ትምህርት ቤት ማድረስ አለባት፤ አያታችን ደግሞ በ3:​40 ላይ የሐኪም ቀጠሮ አለው፤ ከዚያ ደግሞ ከምሽቱ 1:​30 ላይ በሚደረግ አንድ አስፈላጊ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሁላችንም መዘጋጀት አለብን። ከአንደኛው ቀጠሮ ወደ ሌላኛው ቀጠሮ በሚደረገው ሩጫ ለመዝናናት የሚተርፍ ጊዜ አይኖርም። እንዲሁም አሰልቺ ስለሆነው ስለዚህ በሩጫ የተሞላ ሕይወት ዘወትር እናማርራለን።

ጊዜ አጭር የሆነብን እኛ ብቻ አይደለንም

የአምላክ ጠላት የሆነው ሰይጣን ዲያብሎስ በአሁኑ ጊዜ የራሱ ክፋት ሰለባ ሆኗል። የሰው ልጆች የሕይወት ዘመን ሊያጥር የበቃው እሱ በሸረበው ተንኮል መሆኑ ይታወቃል። (ከገላትያ 6:​7, 8 ጋር አወዳድር።) ራእይ 12:​12 የሰማያዊውን መሲሐዊ መንግሥት መወለድ አስመልክቶ የሚናገረው ነገር ብሩህ ተስፋ እንዲኖረን ያደርጋል። እንዲህ ይላል:- “ስለዚህ፣ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፣ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፣ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቊጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።” በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።

አስተማማኝ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አቆጣጠርና የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ መሠረት በአሁኑ ጊዜ የምንኖረው በዚያ “ጥቂት ዘመን” ማብቂያ ላይ ነው። የሰይጣን ዘመን በቅርቡ እንደሚያከትም ማወቁ እንዴት የሚያስደስት ነው! ወደ ጥልቁ ከተጣለ በኋላ ታዛዥ የሰው ልጆች ፍጽምናን ይላበሳሉ፤ እንዲሁም ይሖዋ መጀመሪያ ላይ አስቦት የነበረውን የዘላለም ሕይወት ይወርሳሉ። (ራእይ 21:​1-4) ከዚያ በኋላ የጊዜ ችግር አይኖርም።

የዘላለም ሕይወት አግኝቶ ማብቂያ ለሌለው ጊዜ መኖር ምን እንደሚመስል ልትገምት ትችላለህ? በጊዜ እጦት ምክንያት ሳታከናውን የምትተዋቸው ነገሮች በፍጹም አይኖሩም። ተጨማሪ ጊዜ ካስፈለገህ ነገ ወይም የሚቀጥለው ሳምንት ወይም የሚቀጥለው ዓመት አለልህ፤ እንዲያውም ከፊትህ ወሰን የሌለው ጊዜ ተዘርግቷል!

አሁን ያለንን ጊዜ በጥበብ መጠቀም

ሰይጣን በሰዎች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድርበት ጊዜ የተገደበ መሆኑን ስለ ተገነዘበ ሰዎችን በሥራ በማስጠመድ ስለ ተቋቋመው የአምላክ መንግሥት ምሥራች የሚሰሙበት ጊዜ ለማሳጣት ይሞክራል። ስለዚህ የሚከተለውን መለኮታዊ ምክር ልብ ማለታችን ተገቢ ነው:- “እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።”​—⁠ኤፌሶን 5:​15-17

ጊዜያችንን ዘላቂ ጥቅም የሌላቸው ነገሮችን በማሳደድ ከማባከን ይልቅ ጥበበኞች በመሆን ጊዜያችንን እጅግ አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ማዋል አለብን! “ጥበበኛ ልብ እንዲኖረን ዕድሜያችንን መቁጠር አስተምረን” በሚሉት ከልብ የመነጩ ቃላት ይሖዋን የተማጸነውን የሙሴን የመሰለ አመለካከት ማዳበር አለብን።​—⁠መዝሙር 90:​12 NW

እርግጥ በዛሬው ዓለም በሥራ ያልተጠመደ ሰው የለም። ያም ሆኖ ግን የይሖዋ ምሥክሮች ውድ ከሆነው ጊዜህ ውስጥ የተወሰነውን በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር የዘላለም ሕይወት ለማግኘት የሚያስፈልጉትን መሥፈርቶች ለመማር እንድታውል አጥብቀው ያሳስቡሃል። ‘የይሖዋ ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማስተዋል’ በሳምንት ለአንድ ሰዓት ያክል የሚደረግ በደንብ የታሰበበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚከተሉት ቃላት በራስህ ላይ ሲፈጸሙ ለመመልከት ያስችልሃል:- “ከክፉ ሽሽ፣ መልካምንም አድርግ ለዘላለምም ትኖራለህ። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፣ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ።”​—⁠መዝሙር 37:​27, 29

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ኒው ዮርክ በሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር የታተ​መውን ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ 6ኛ ምዕራፍ ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ