የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w00 3/1 ገጽ 19
  • እምነታቸው ወሮታ አስገኘ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እምነታቸው ወሮታ አስገኘ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘እምነትን ጠብቄአለሁ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • መልስ የሚያገኙት የእነማን ጸሎቶች ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ይሖዋ ጸሎታችንን የሚመልስልን እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • “ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን [ደስተኛ አዓት] ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—1993
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
w00 3/1 ገጽ 19

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

እምነታቸው ወሮታ አስገኘ

ሐዋርያው ጳውሎስ የላቀ እምነት ያሳየ ሰው ሲሆን የእምነት ባልደረቦቹንም እምነታቸውን እንዲያጎለብቱ አበረታቷቸዋል። እንዲህ ብሏል:- “ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።” (ዕብራውያን 11:​6) ከሞዛምቢክ የተገኙት የሚከተሉት ተሞክሮዎች ይሖዋ ጠንካራ እምነት ላሳዩ እንዴት ወሮታ እንደሚከፍልና ከልብ ለቀረቡ ጸሎቶች መልስ እንደሚሰጥ ያሳያሉ።

• በሰሜናዊ የኒያሳ ክልል የምትኖር ባሏ የሞተባት አንዲት እህት እሷና ስድስት ልጆችዋ “የአምላክ የሕይወት መንገድ” በተባለው የአውራጃ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እንዴት መሄድ እንደሚችሉ አሳስቧት ነበር። ብቸኛው የገቢ ምንጯ በአካባቢው በሚገኘው ገበያ ሸቀጣ ሸቀጥ በመነገድ የምታገኘው ገንዘብ ነበር። ሆኖም የስብሰባው ቀን እየተቃረበ ሲመጣ እጅዋ ላይ የነበረው ገንዘብ ሊገዛ የሚችለው ለእሷና ለቤተሰቧ የሚሆን የአንድ ጉዞ የባቡር ቲኬት ብቻ ነበር። ይሁን እንጂ በይሖዋ ዝግጅት ላይ ትምክህት በመጣል ስብሰባው ላይ ለመገኘት ያወጣችውን ዕቅድ ገፋችበት።

ስድስት ልጆችዋን ይዛ ባቡር ተሳፈረች። በጉዞ ላይ ተቆጣጣሪው ትኬቷን እንድታሳይ ጠየቃት። ደረቷ ላይ የለጠፈችውን ካርድ ተመልክቶ ምን ዓይነት መታወቂያ እንደሆነ ጠየቃት። እህት የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ተሳታፊ መሆኗን የሚያሳውቅ ካርድ መሆኑን ነገረችው። ተቆጣጣሪው “ይህ ስብሰባ የሚደረገው የት ነው?” ሲል ጠየቃት። ስብሰባው የሚካሄደው ወደ 300 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቆ በሚገኘው አጎራባች በሆነው የናምፑላ ክልል መሆኑን ከተረዳ በኋላ የመደበኛውን ቲኬት ዋጋ ግማሽ ብቻ በማስከፈል ፈጽሞ ያልተጠበቀ ነገር አደረገ! ከዚያም በግማሹ የትኬት ዋጋ ለእሷና ለቤተሰቧ የሚሆን መመለሻ ትኬቶች ሰጣት። በይሖዋ ላይ ትምክህት በመጣልዋ ምንኛ ተደሰተች!​—⁠መዝሙር 121:​1, 2

• በጣም ሃይማኖተኛ የነበረች አንዲት ሴት እርሱን የምታመልክበትን ትክክለኛውን መንገድ እንዲያሳያት ወደ አምላክ ለ25 ዓመታት ገደማ ጸልያ ነበር። አባል የነበረችበት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ በዓሎችንና ባሕላዊ የአምልኮ ሥርዓቶችን ይቀላቅል ስለነበር እንዲህ ዓይነቱ አምልኮ አምላክን የሚያስደስት ስለመሆኑ ጥርጣሬ ነበራት።

እንዲህ ትላለች:- “‘ለምኑ፣ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፣ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፣ ይከፈትላችሁማል’ የሚለው በማቴዎስ 7:​7 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የኢየሱስ ቃል ሁልጊዜ ትዝ ይለኝ ነበር። ይህን ጥቅስ በማስታወስ አምላክ ወደ እውነት እንዲመራኝ አዘውትሬ እጸልይ ነበር። አንድ ቀን የቤተ ክርስቲያኑ ቄስ በአካባቢው በሚገኘው ገበያ የሚነግዱ ሁሉ እሱ እንዲመርቃቸው ከፈለጉ የተወሰነ ገንዘብና ከሚነግዷቸው ዕቃዎች ውስጥ አንዳንድ ነገሮች ይዘውለት እንዲመጡ ጠየቃቸው። ይህ ጥያቄ ቅዱስ ጽሑፋዊ መስሎ ስላልታየኝ ምንም ነገር አላመጣሁም። ቄሱ ‘መባ’ ይዤ አለመምጣቴን ሲመለከት በሁሉም የቤተ ክርስቲያን አባላት ፊት ይሰድበኝ ጀመር። የዚያን ዕለት አምላክ መመለክ የሚፈልገው በዚህ መንገድ እንዳልሆነ ስለተገነዘብኩ ቤተ ክርስቲያኑን ለቅቄ ወጣሁ። በመሀሉ እውነትን ለማግኘት ያለ ማቋረጥ መጸለዬን ቀጠልኩ።

“በመጨረሻ እንደምንም ደፍሬ ዘመዴ ወደሆነ አንድ የይሖዋ ምሥክር ሄድኩ። ትራክት አበረከተልኝና እያነበብኩ እያለሁ አምላክ ለጸሎቴ መልስ እንደሰጠኝ ወዲያውኑ ተገነዘብኩ። ከጊዜ በኋላ ጓደኛዬም ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት አድናቆት አሳደረና ጋብቻችንን ሕጋዊ አደረግን። በኋላ ላይ ግን ባለቤቴ በጠና ታመመ። ሆኖም እንደገና በገነት ውስጥ መገናኘት እንድንችል እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በእውነት መንገድ በጽናት እንድቀጥል አበረታቶኛል።

“ይሖዋ ለጸሎቴ መልስ ስለሰጠኝና እርሱን የማመልክበትን ትክክለኛውን መንገድ ስላሳየኝ ምንጊዜም አመስጋኝ ነኝ። በተጨማሪም ስምንቱም ልጆቼ ራሳቸውን ለይሖዋ የወሰኑ አገልጋዮች ሲሆኑ በማየት ጸሎቴ መልስ አግኝቷል።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ