የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 8/15 ገጽ 3
  • ብዙ ወጣቶች ትኩረት የነፈጉት መጽሐፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ብዙ ወጣቶች ትኩረት የነፈጉት መጽሐፍ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንዳንዶች የተለየ አመለካከት አላቸው
  • መጽሐፍ ቅዱስን የምታውቀው ምን ያህል ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • የወጣትነት ሕይወትህን የተሳካ አድርገው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቤን ይበልጥ አስደሳች ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2001
  • በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ መጠቀም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 8/15 ገጽ 3

ብዙ ወጣቶች ትኩረት የነፈጉት መጽሐፍ

“መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል መሆኑን እንዴት አውቃለሁ? መጽሐፉን የማንበብ ፍላጎቱም የለኝም” በማለት ቤቲ የተባለች ወጣት ተናግራለች።

ቤቲ በምትኖርበት በጀርመን ብዙ ወጣቶች የእርሷ ዓይነት አመለካከት አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ያን ያህል አስፈላጊ ሆኖ አይታያቸውም። በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው በጀርመን ከሚኖሩ ወጣቶች ውስጥ አንድ በመቶ የሚሆኑት አዘውትረው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነብቡ ሲሆን ሁለት በመቶዎቹ ደግሞ በየጊዜው ያነብባሉ። አሥራ ዘጠኝ በመቶዎቹ አልፎ አልፎ የሚያነብቡ ሲሆን ወደ 80 በመቶ የሚጠጉት ግን ከነጭራሹ አያነብቡም። በሌሎች አገሮች ምናልባትም አንተ በምትኖርበት አገርም ያለው ሁኔታ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ወጣቶች ትኩረት የነፈጉት መጽሐፍ ነው።

ወጣቱ ትውልድ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምንም ዓይነት እውቀት የሌለው መሆኑ ምንም አያስደንቅም! ላውዚትስ ሩንትሻው የተባለው ጋዜጣ በ2000 ዓመት መግቢያ ላይ አሥርቱን ትእዛዛት የሚያውቁና ሕይወታቸውንም በዚያው መሠረት የሚመሩት ምን ያህል ሰዎች እንደሆኑ የሚገልጥ ጥናት አውጥቶ ነበር። ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ከሆኑት ሰዎች ውስጥ 67 በመቶ የሚሆኑት እነዚህን ትእዛዞች የሚያውቁና ሕይወታቸውንም በዚያው መሠረት የሚመሩ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች ከሆኑት መካከል ግን ይህንን የሚያደርጉት 28 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው። አዎን፣ አብዛኞቹ ወጣቶች ከአምላክ ቃል ጋር ምንም ትውውቅ የላቸውም።

አንዳንዶች የተለየ አመለካከት አላቸው

በሌላው በኩል ደግሞ በዓለም ዙሪያ የአምላክ ቃል ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የተገነዘቡ በሚልዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች አሉ። ለምሳሌ ያህል አሌክሳንደር የ19 ዓመት ልጅ ሲሆን ጠዋት ሥራ ከመጀመሩ በፊት ሁልጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ያነብባል። “ቀኑን ለመጀመር ከዚህ የተሻለ ምን ነገር ማድረግ እችላለሁ?” በማለት ተናግሯል። ሳንድራ ሁልጊዜ ማታ ማታ መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብ ልማድ አላት። “ይህ ልማድ የሕይወቴ ክፍል ሆኗል” በማለት ተናግራለች። የ13 ዓመቷ ጁሊያም ማታ ከመተኛቷ በፊት ቢያንስ አንድ ምዕራፍ የማንበብ ልማድ አዳብራለች። “መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ያስደስተኛል። ወደፊትም በዚሁ መቀጠል እፈልጋለሁ።”

ትክክልና ጥበብ ያለበት አመለካከት የትኛው ነው? መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው? ለወጣቱ ትውልድስ ጠቃሚና አስፈላጊ ነው? አንተ ምን ይመስልሃል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ