የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 1/15 ገጽ 3
  • መላእክት እነማን ናቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መላእክት እነማን ናቸው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • መላእክት—“የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • መላእክት በሕይወታችን ውስጥ ምን ሚና ይጫወታሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • መላእክት ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 1/15 ገጽ 3

መላእክት እነማን ናቸው?

የአንድ ኃያል መንግሥት ንጉሥ የሚያየውን ነገር ለማመን አልቻለም። በእሳት ተቃጥለው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው ሦስት ሰዎች ከሞት ተረፉ! ያዳናቸው ማን ነበር? ከዚህ ዓይነት ሁኔታ ለዳኑት ሦስት ሰዎች ንጉሡ “መልአኩን ልኮ አገልጋዮቹን ያዳነ፣ [የእናንተ] አምላክ ይባረክ” አላቸው። (ዳንኤል 3:​28) ይህ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የነበረ የባቢሎን ንጉሥ መላእክት የአምላክን አገልጋዮች ሲያድኑ ተመልክቷል። ባለፉት ዘመናት የኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በመላእክት ያምኑ ነበር። ብዙ ሰዎች በዛሬው ጊዜ መላእክት እንዳሉ ብቻ ሳይሆን በእነርሱ ሕይወት ውስጥ የሚጫወቱት ሚና እንዳለም ያምናሉ። መላእክት እነማን ናቸው? የመጡትስ ከየት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ መላእክት ልክ እንደ አምላክ መንፈስ እንደሆኑ ይናገራል። (መዝሙር 104:​4፤ ዮሐንስ 4:​24) በሚሊዮን የሚቆጠሩ መላእክት አሉ። (ራእይ 5:​11) ሁሉም መላእክት “ኀያላን” ናቸው። (መዝሙር 103:​20) መላእክት ልክ እንደ ሰው የራሳቸው የሆነ ባሕርይና የመምረጥ ነጻነት ያላቸው ፍጡራን ቢሆኑም ሕልውናቸውን ያገኙት ግን ከሰው ልጆች በተለየ መልኩ ነው። እንዲያውም መላእክት የተፈጠሩት አምላክ ሰውንና ፕላኔቷን ምድር እንኳ ከመፍጠሩ ከረዥም ጊዜ በፊት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ‘ምድርን በመሠረተ ጊዜ የንጋት ከዋክብት [መላእክት] እንደዘመሩና . . . መላእክትም [“የእግዚአብሔርም ልጆች፣” የ1954 ትርጉም ] እልል’ እንዳሉ ይናገራል። (ኢዮብ 38:​4, 7) መላእክት የአምላክ ፍጥረታት በመሆናቸው ምክንያት የአምላክ ልጆች ተብለው ተጠርተዋል።

አምላክ መላእክትን የፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው? መላእክት በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ የተጫወቱት ሚና ይኖር ይሆን? በዛሬው ጊዜስ በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድሩ ይሆን? የራሳቸውን ምርጫ ማድረግ የሚችሉ እንደመሆናቸው መጠን ከመላእክት መካከል የሰይጣን ዲያብሎስን ፈለግ በመከተል የአምላክ ጠላቶች የሆኑ አሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ይሰጣል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ