የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 7/1 ገጽ 31
  • እምነቷ ሌሎችን ያበረታታል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እምነቷ ሌሎችን ያበረታታል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የረጅም ዓመታት ፍለጋ በረከት አስገኘ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • “እንዲህ ያለ ፍቅር አግኝቼ አላውቅም”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ‘እምነትን ጠብቄአለሁ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 7/1 ገጽ 31

እምነቷ ሌሎችን ያበረታታል

ሲልቪያ በታኅሣሥ ወር 1992 ስትወለድ የተሟላ ጤንነት ያላት ትመስል ነበር። ይሁን እንጂ ሁለት ዓመት ሲሞላት ሲስቲክ ፋይብሮሲስ በተባለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በሚሄድ እንዲሁም የመተንፈስና ምግብ የመፍጨት ችግር በሚያስከትል የማይድን በሽታ እንደተያዘች ታወቀ። ሕመሟን ለማስታገስ ሲባል በየቀኑ 36 ክኒን የምትውጥ ሲሆን በመተንፈሻ አካላት የሚሳቡ መድኃኒቶችንና እንደ እሽት ያሉ ሕክምናዎችን ትወስዳለች። ከጤናማ ሰው ጋር ሲነጻጸር የሳንባዋ የመሥራት አቅም 25 በመቶ ብቻ በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ ሌላው ቀርቶ ከቤት ስትወጣ እንኳ ለመተንፈስ የሚረዳትን ኦክስጅን የያዘ ሲሊንደር ይዛ መንቀሳቀስ ይኖርባታል።

እናቷ ቴሬዛ እንዲህ ስትል ተናግራለች:- “ሲልቪያ ያለባትን ሕመም የተቋቋመችበት መንገድ በጣም ይገርማል። ከቅዱሳን መጻሕፍት ያገኘችው እውቀት ጠንካራ እምነት እንዲኖራት አስችሏታል። ይህ እምነቷ ደግሞ ሐዘኗንም ሆነ ችግሯን እንድትቋቋም ረድቷታል። የታመሙ ሁሉ ፈውስ የሚያገኙበት አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ይሖዋ የሰጠውን ተስፋ ሁልጊዜ ታስታውሳለች።” (ራእይ 21:4) ቤተሰቦቿ አንዳንድ ጊዜ ተስፋ ሲቆርጡ በልበ ሙሉነት የምታሳያቸው ፈገግታ ብርታት ይሰጣቸዋል። እንዲያውም ወላጆቿንና ወንድሟን “በአዲሱ ዓለም የምናገኘው ሕይወት አሁን የሚደርስብንን ሥቃይ ሁሉ ያስረሳናል” ትላቸዋለች።

ሲልቪያ በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ምሥራች ዘወትር ለሌሎች ሰዎች ታካፍላለች፤ የምታነጋግራቸው ሰዎችም በፊቷ ላይ የሚነበበውን የደስታ ስሜት ያስተውላሉ። ከዚህም በላይ በካናሪ ደሴቶች የሚገኘው እርሷ የምትሰበሰብበት የክርስቲያን ጉባኤ አባላት፣ በጉባኤ ላይ የምትሰጠውን ሐሳብ መስማትና የምታደርገውን ተሳትፎ መመልከት በጣም ያስደስታቸዋል። እንዲሁም ሲልቪያ እያንዳንዱ ስብሰባ ካለቀ በኋላ ከክርስቲያን ወንድሞቿና እህቶቿ ጋር እየተጫወተች መቆየት ያስደስታታል። ተግባቢና ተጫዋች ልጅ መሆኗ ጉባኤ ውስጥ ባሉት ሁሉ እንድትወደድ አድርጓታል።

“ሲልቪያ በጣም ወሳኝ የሆነ አንድ ትምህርት አስጨብጣናለች” ሲል አባቷ አንቶኒዮ ተናግሯል። “ችግሮች ቢኖሩብንም እንኳ ሕይወት ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ በመሆኑ ልናደንቀው ይገባል” ብሏል። ልክ እንደ ሲልቪያ ወጣቶችም ሆኑ አረጋውያን የሆኑ የአምላክ አገልጋዮች በሙሉ “‘ታምሜአለሁ’ የሚል አይኖርም” የተባለለትን ጊዜ በናፍቆት ይጠባበቃሉ።—ኢሳይያስ 33:24

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሲልቪያ፣ እናቷ የኦክስጅኑን ሲሊንደር ይዛላት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ስታነብ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ