የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 7/1 ገጽ 31
  • የቃየን ቁጣ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የቃየን ቁጣ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዶምና የገሞራ ጥፋት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ አድማጮቹን አስደነቀ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 7/1 ገጽ 31

ለወጣት አንባቢያን

የቃየን ቁጣ

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለማስተዋል ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፍጥረት 4:1-12⁠ን አንብብ።

ቃየን ምን ዓይነት ቁመና የነበረው ይመስልሃል? በፊቱ ላይ ምን ይነበባል? ምን ዓይነት ባሕርይስ ነበረው? ስለ አቤልስ ምን ማለት ትችላለህ?

․․․․․

ቃየን “የሥጋ ሥራ” ተብለው ከተገለጹት መካከል የትኞቹን አንጸባርቋል? ይህንንስ እንዴት እናውቃለን? (ገላትያ 5:19-21)

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።—ቁጥር 4-7⁠ን በድጋሚ አንብብ።

ይሖዋ ከቀረበለት መሥዋዕት ይልቅ ይበልጥ ትኩረት ያደረገው በምን ላይ ነበር? (ምሳሌ 21:2)

․․․․․

መቆጣት ተገቢ የሚሆነው መቼ ነው? ይሁንና ቃየን ‘እጅግ መቆጣቱ’ ፈጽሞ ትክክል አልነበረም የምንለው ለምንድን ነው?

․․․․․

ቅናት ተገቢ የሚሆነው መቼ ነው? ያም ሆኖ ቃየን ያሳየው ቅናት ተገቢ አልነበረም የምንለው ለምንድን ነው? (1 ነገሥት 19:10)

․․․․․

ቃየን ቁጣውን ‘ለመቆጣጠር’ ምን እርምጃዎችን መውሰድ ይችል ነበር?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ:-

ስለ ቁጣ።

․․․․․

ስለ ቅናት።

․․․․․

መጥፎ ዝንባሌዎችን ስለ ‘መቆጣጠር።’

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው የትኛው ሁኔታ ነው? ለምንስ?

․․․․․

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ