የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 9/1 ገጽ 18
  • ‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማስተዋወቂያ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ‘ከመጽናናት ሁሉ አምላክ’ የሚገኝ መጽናኛ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • አምላክ የሚያጽናናን እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ‘ያዘኑትን አጽናኑ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 9/1 ገጽ 18

ወደ አምላክ ቅረብ

‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’

2 ቆሮንቶስ 1:3, 4

በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን እንደ መከራ፣ ችግርና ብቸኝነት ያሉ ሁኔታዎች እንድናዝን አልፎ ተርፎም ተስፋ እንድንቆርጥ ሊያደርጉን ይችላሉ። በእነዚህ ጊዜያት፣ ‘ማን ሊረዳኝ ይችላል?’ በማለት ትጠይቅ ይሆናል። ሐዋርያው ጳውሎስ በ2 ቆሮንቶስ 1:3, 4 ላይ ያሰፈረው ሐሳብ ይሖዋ አምላክ የማይነጥፍ የመጽናናት ምንጭ መሆኑን ይጠቁማል።

በቁጥር 3 ላይ አምላክ “የርኅራኄ አባት” ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ምን ማለት ነው? “ርኅራኄ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪከኛ ቃል መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች መራራትን ያመለክታል።a አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ማመሳከሪያ ይህን ቃል አስመልክቶ “ሐዘኔታ ማሳየት” ወይም “ከልብ ማሰብ” ተብሎ ሊተረጎም እንደሚችል ገልጿል። አምላክ ‘ርኅሩኅ’ መሆኑ እርምጃ እንዲወስድ ያነሳሳዋል። አምላክ እንዲህ ያለ ባሕርይ እንዳለው ማወቃችን ወደ እሱ እንድንቀርብ አይገፋፋንም?

በተጨማሪም ጳውሎስ፣ ይሖዋን ‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’ በማለት ጠርቶታል። ጳውሎስ እዚህ ላይ የተጠቀመበት ቃል “ችግር ወይም ሐዘን የደረሰበትን ሰው ማጽናናት ብሎም ማበረታቻ ወይም እርዳታ መስጠት” የሚል ሐሳብ ይዟል። ዚ ኢንተርፕሪተርስ ባይብል እንዳለው ከሆነ “መከራ የደረሰበት ሰው ችግሩን መቋቋም እንዲችል ማበረታቻ ስንሰጠው እያጽናናነው ነው።”

‘አምላክ የሚያጽናናን እና ችግራችንን ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት የሚሰጠን እንዴት ነው?’ በማለት ትጠይቅ ይሆናል። አምላክ በዋነኝነት እንዲህ የሚያደርገው በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስና በሰጠን የጸሎት መብት አማካኝነት ነው። ጳውሎስ “ቅዱሳት መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ እንዲኖረን” ሲል አምላክ በፍቅር ተነሳስቶ ቃሉን እንደሰጠን ነግሮናል። በተጨማሪም ከልብ የመነጨ ጸሎት በማቅረብ ‘ከማስተዋል በላይ የሆነውን የአምላክን ሰላም’ ማግኘት እንችላለን።—ሮሜ 15:4፤ ፊልጵስዩስ 4:7

ይሖዋ ሕዝቦቹን የሚያጽናናቸው እስከ ምን ድረስ ነው? ጳውሎስ፣ አምላክ “በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል” በማለት ተናግሯል። (2 ቆሮንቶስ 1:4) ምንም ዓይነት ውጥረት፣ ጭንቀት ወይም መከራ ይድረስብን አምላክ ሁኔታውን ለመቋቋም የሚያስችል ብርታትና ጥንካሬ ይሰጠናል። ይህ ታዲያ የሚያጽናና አይደለም?

አምላክ ከሚሰጠው ማጽናኛ ተጠቃሚ የሚሆነው ተቀባዩ ብቻ አይደለም። ጳውሎስ ቀጥሎ ሲናገር አምላክ የሚያጽናናን “እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል [ነው]” ብሏል። ከደረሰብን መከራ መጽናናታችን የሌሎችን ችግር እንደ ራሳችን አድርገን እንድንመለከትና የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ እንድንሰጣቸው ይገፋፋናል።

“የመጽናናትም ሁሉ አምላክ” የሆነው ይሖዋ ችግሮቻችንንና ሥቃያችንን ያስወግድልናል ማለት ላይሆን ይችላል። ይሁንና አምላክ ማጽናኛ እንዲሰጠን ወደ እሱ ዘወር የምንል ከሆነ በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥመንን ማንኛውንም ሐዘን ወይም መከራ ለመቋቋም የሚያስችል ኃይል እንደሚሰጠን እርግጠኞች መሆን እንችላለን። እንዲህ ያለውን ርኅሩኅ አምላክ በእርግጥም ልናመልከውና ልናወድሰው ይገባል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a አምላክ “የርኅራኄ አባት [ወይም የርኅራኄ ምንጭ]” ተብሎ ተጠርቷል። ምክንያቱም ርኅራኄ ከአምላክ የሚመነጭ ሲሆን ከባሕርያቱም መካከል አንዱ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ