የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 9/1 ገጽ 3
  • የሰማዩ አባትህን ታውቀዋለህ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሰማዩ አባትህን ታውቀዋለህ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አባታችን ይሖዋ በጣም ይወደናል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • ይሖዋን እንደ አባትህ አድርገህ ትመለከተዋለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • አምላክ ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ‘ወልድ አብን ለመግለጥ ፈቃደኛ ነው’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 9/1 ገጽ 3

የሰማዩ አባትህን ታውቀዋለህ?

አባትህን ምን ያህል ታውቀዋለህ? አፍቃሪ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ ያደግክ ከሆንክ ይህ ጥያቄ ሳያስገርምህ አይቀርም። በመሆኑም ‘ይህ ምን ጥያቄ አለው፤ በደንብ አውቀዋለሁ!’ ብለህ ትመልስ ይሆናል። አዎን፣ ብዙ ሰዎች አባታቸው ምን እንደሚወድና እንደሚጠላ፣ አንዳንድ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ምን እንደሚያደርግ እንዲሁም ለቤተሰቡ ምን ያህል እንደሚያስብ ያውቃሉ።

ያም ሆኖ አባትህ በፍጹም ያልጠበቅከው ባሕርይ በማሳየቱ የተገረምክባቸው ጊዜያት ይኖሩ ይሆናል። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ልጅ አባቱን የሚያውቀው በዝምተኛነቱ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ድንገተኛ ሁኔታ ሲፈጠር አባቱ ቤተሰቡን ከአደጋ ለመጠበቅ ሲል ቆራጥ እርምጃ ሲወስድ ይመለከት ይሆናል።

ስለ ፈጣሪያችንስ ምን ማለት ይቻላል? መጽሐፍ ቅዱስ “የምንኖረውና የምንንቀሳቀሰው፣ ያለነውም በእርሱ” እንደሆነ ይናገራል። (የሐዋርያት ሥራ 17:28) ሕይወት ያገኘነው ከእሱ በመሆኑ አምላክ የሁላችንም አባት ነው። (ኢሳይያስ 64:8) አንተም፣ አምላክን እንደ አባትህ አድርገህ ትመለከተው ይሆናል፤ ይህም ትክክልና ተገቢ ነው። ይሁን እንጂ ስለ እሱ ልናውቃቸውና ልንማራቸው የሚገቡ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ይህ ደግሞ ደስታና ጥቅም ያስገኝልናል።

ሰብዓዊ አባትህን በደንብ እያወቅከው በሄድክ መጠን ለእሱ ያለህ አክብሮት የዚያኑ ያህል ይጨምራል። በተመሳሳይም አምላክን ይበልጥ እያወቅከው ስትሄድ ከእሱ ጋር ያለህ ዝምድና ይጠናከራል። አምላክን በደንብ የምታውቀውና የእሱን ፈቃድ የምትፈጽም ከሆነ በሕይወትህ ውስጥ የሚያጋጥሙህን ችግሮች እንድትቋቋም ይረዳሃል።

የሰማዩ አባታችን ምን ዓይነት አምላክ ነው? የአምላክን ባሕርያት ማወቅህ በአመለካከትህ ላይ ምን በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል? እሱን ማወቅህ ምን ኃላፊነቶችን ያስከትልብሃል? በሚቀጥለው ርዕስ ላይ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ታገኛለህ።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

አንድን ሰው ይበልጥ ባወቅከው መጠን ለእሱ ያለህ አመለካከትም የዚያኑ ያህል ይለወጣል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ