የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp19 ቁጥር 1 ገጽ 3
  • አምላክ ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ማን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የሰማዩ አባትህን ታውቀዋለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • አምላክ ማን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
wp19 ቁጥር 1 ገጽ 3
በጣም የሚያምር መልክዓ ምድርን በአድናቆት የሚመለከት ሰው

አምላክ ማን ነው?

ብዙ ሰዎች በአምላክ እንደሚያምኑ ይናገራሉ። “አምላክ ማን ነው?” ተብለው ቢጠየቁ የሚሰጡት መልስ ግን የተለያየ ነው። አንዳንዶች አምላክ ሰዎችን በሆነ ባልሆነው የሚቀጣ ጨካኝ ዳኛ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ ምንም ዓይነት ጥፋት ቢሠሩ አምላክ ይቅር እንደሚላቸውና ምንጊዜም እንደሚወዳቸው ያምናሉ። አምላክ ሊቀረብ እንደማይችልና ለእኛ ምንም ደንታ እንደሌለው የሚያስቡ ሰዎችም አሉ። አምላክን በተመለከተ እንዲህ ያሉ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ አመለካከቶች መኖራቸው በርካታ ሰዎች ‘አምላክ ማን እንደሆነ ማወቅ አይቻልም’ ብለው እንዲያስቡ አድርጓል።

የአምላክን ማንነት ማወቅ ያን ያህል አስፈላጊ ነው? አዎ። ስለ አምላክ እውነቱን ማወቅህ ሕይወትህ ዓላማና ትርጉም ያለው እንዲሆን ያደርጋል። (የሐዋርያት ሥራ 17:26-28) ወደ አምላክ ይበልጥ በቀረብክ መጠን እሱም ይበልጥ ይወድሃል፤ እንዲሁም ይረዳሃል። (ያዕቆብ 4:8) በተጨማሪም ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት መቅሰምህ ወደፊት የዘላለም ሕይወት እንድታገኝ ያስችልሃል።—ዮሐንስ 17:3

አምላክን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው? እስቲ በደንብ ስለምታውቀው ሰው፣ ለምሳሌ ስለ ቅርብ ወዳጅህ ለማሰብ ሞክር። በመካከላችሁ እንዲህ ያለ ወዳጅነት ሊመሠረት የቻለው እንዴት ነው? ስሙን፣ ባሕርይውን፣ የሚወደውንና የሚጠላውን፣ ከዚህ በፊት ያደረገውንና ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን ጨምሮ ስለ እሱ የተለያዩ ነገሮችን ስላወቅክ እንደሆነ ግልጽ ነው። ከዚህ ሰው ጋር እንድትቀራረብ ያደረገህ ስለ እሱ ማወቅህ ነው።

በተመሳሳይም ስለ አምላክ ማወቅ የምትችለው ስለ እሱ በመማር ነው፤ በመሆኑም የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ማወቅህ አስፈላጊ ነው፦

  • የአምላክ ስም ማን ነው?

  • አምላክ ምን ባሕርያት አሉት?

  • አምላክ ከዚህ በፊት ምን አድርጓል?

  • አምላክ ወደፊት ምን ያደርጋል?

  • አምላክን ማወቅህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

ይህ መጽሔት መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠውን መልስ ይዟል። በዚህ መጽሔት ውስጥ ያሉት ርዕሶች አምላክ ማን እንደሆነ እንድታውቅ ብቻ ሳይሆን ከእሱ ጋር የቀረበ ዝምድና መመሥረትህ ምን ጥቅም እንዳለው እንድትገነዘብ ይረዱሃል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ