የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w08 11/1 ገጽ 24-25
  • “ቃል” ሁሉን ቻይ አምላክ ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ቃል” ሁሉን ቻይ አምላክ ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጥሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መምረጥ የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የአምላክ ቃል አፍቃሪዎች ትልቅ ግምት የሚሰጡት ክንውን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • የአፍሪካ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • በዓለም ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆት ያተረፈው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
w08 11/1 ገጽ 24-25

“ቃል” ሁሉን ቻይ አምላክ ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚዎች ዮሐንስ 1:1⁠ን ሲተረጉሙ ለዚህ ጥያቄ መልስ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል። አዲስ ዓለም ትርጉም ይህንን ጥቅስ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከአምላክ ጋር [with God] ነበር፤ ቃልም አምላክ [a god] ነበር” በማለት ተርጉሞታል። (ዮሐንስ 1:1) አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ደግሞ የዚህን ጥቅስ የመጨረሻ ክፍል ሲተረጉሙ “ቃል” “የመለኮትነት ባሕርይ የተላበሰ” እንደነበረ የሚገልጽ ወይም ተመሳሳይ ሐሳብ የሚያስተላልፍ ቃል ተጠቅመዋል። (በጄምስ ሞፋት የተዘጋጀው ኤ ኒው ትራንስሌሽን ኦቭ ዘ ባይብል፤ ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል) ይሁንና በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የዮሐንስ 1:1⁠ን የመጨረሻ ክፍል “ቃልም አምላክ [God (ሁሉን ቻይ አምላክ)] ነበር” በማለት ተርጉመውታል።—ዘ ሆሊ ባይብል—ኒው ኢንተርናሽናል ቨርሽን፤ ዘ ጀሩሳሌም ባይብል

የግሪክኛ ቋንቋ ሰዋስውና በጥቅሱ ዙሪያ ያለው ሐሳብ፣ አዲስ ዓለም ትርጉም ጥቅሱን የተረጎመበት መንገድ ትክክል እንደሆነ የሚያሳዩ ከመሆኑም ሌላ “ቃል” በጥቅሱ መጀመሪያ ላይ የተጠቀሰውን “አምላክ” ሊያመለክት እንደማይችል ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይነገር የነበረው ግሪክኛ ቋንቋ፣ ማንነትን የማያመለክት መስተአምር (በእንግሊዝኛ “a” ወይም “an”) የሚጠቀም አለመሆኑ በአንዳንድ ሰዎች አእምሮ ውስጥ ከላይ ያለውን ጥያቄ ያስነሳል። በዚህም ምክንያት ከክርስቶስ ልደት በኋላ በነበሩት በመጀመሪያዎቹ መቶ ዘመናት ይነገር በነበረ ቋንቋ የተተረጎመ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ትኩረታችንን ይስበዋል።

ቋንቋው የሳሂዲክ ኮፕቲክ በመባል ይታወቃል። ኮፕቲክ፣ ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን ካጠናቀቀ በኋላ ባሉት መቶ ዘመናት ግብጽ ውስጥ ይነገር የነበረ ቋንቋ ሲሆን የሳሂዲክ ቀበሌኛ ደግሞ ጥንታዊ የሆነው የኮፕቲክ የጽሑፍ ቋንቋ ነው። ጥንታዊ የሆኑትን የኮፕቲክ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በተመለከተ ዚ አንከር ባይብል ዲክሽነሪ እንዲህ ብሏል፦ “[የሰብዓ ሊቃናት ትርጉም] እና [የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት] ወደ ኮፕቲክ ቋንቋ የተተረጎሙት በ3ኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ነበር፤ በመሆኑም የኮፕቲኩ ትርጉም በአሁኑ ጊዜ በእጃችን ከሚገኙት ከአብዛኞቹ ትርጉሞች የበለጠ ዕድሜ ያላቸውን [ጥንታዊ የግሪክኛ ቅጂዎች] መሠረት ያደረገ ነው።”

በሳሂዲክ ኮፕቲክ የተተረጎመውን መጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ያደረጉ ሁለት ምክንያቶች አሉ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የሥላሴ መሠረተ ትምህርት በይፋ ተቀባይነት ካገኘበት ከ4ኛው መቶ ዘመን በፊት ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖች ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዴት ይረዱ እንደነበር ይጠቁመናል። በሁለተኛ ደረጃ፣ የኮፕቲክ የሰዋስው ሕግ በጣም አስፈላጊ በሆነ አንድ መንገድ ከእንግሊዝኛ የሰዋስው ሕግ ጋር ይመሳሰላል። ጥንታዊ የሆኑት የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ትርጉሞች የሲሪያክ፣ የላቲንና የኮፕቲክ ትርጉሞች ናቸው። የሲሪያክና የላቲን ቋንቋዎች በዘመኑ እንደነበረው የግሪክኛ ቋንቋ ሁሉ ማንነትን የማያመለክት መስተአምር የሌላቸው ሲሆን የኮፕቲክ ቋንቋ ግን እንዲህ ዓይነቱ መስተአምር አለው። በተጨማሪም ቶማስ ኦዴን ላምብዲን የተባሉ የቋንቋ ምሁር ኢንትሮዳክሽን ቱ ሳሂዲክ ኮፕቲክ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “ኮፕቲክ ቋንቋ መስተአምሮችን የሚጠቀምበት መንገድ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ የሰዋስው ሥርዓት ጋር በጣም ይመሳሰላል።”

በመሆኑም የኮፕቲክ ትርጉም በዚያን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ዮሐንስ 1:1⁠ን እንዴት ይረዱት እንደነበር የሚያሳይ ግሩም ማስረጃ ይሰጣል። ይህ ማስረጃ ምንድን ነው? የሳሂዲክ ኮፕቲክ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በዮሐንስ 1:1 የመጨረሻ ክፍል ላይ “አምላክ” ከሚለው ቃል በፊት ማንነትን የማያመለክት መስተአምር (በእንግሊዝኛ “a”) ይጠቀማል። ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው፣ በጥንት ዘመን የነበሩት ተርጓሚዎች በዮሐንስ 1:1 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ሐሳብ፣ ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው የሚል መልእክት እንደማያስተላልፍ ተገንዝበው ነበር። “ቃል” አምላክ ነበር ቢባልም ሁሉን ቻይ አምላክ ግን አይደለም።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ