የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 1/1 ገጽ 19
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጳንጥዮስ ጲላጦስ ማን ነበረ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ኢየሱስ አልፎ ተሰጠ፤ ከዚያም ሊገደል ተወሰደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 1/1 ገጽ 19

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ጳንጥዮስ ጲላጦስ ቄሳርን የሚፈራበት ምክንያት ነበረው?

የአይሁድ መሪዎች፣ ሮማዊው ገዥ ጳንጥዮስ ጲላጦስ ኢየሱስን እንዲገድለው ለማስገደድ ሲሉ “ይህን ሰው ከፈታኸው አንተ የቄሳር ወዳጅ አይደለህም” ብለውት ነበር። (ዮሐንስ 19:12) እዚህ ላይ የተጠቀሰው “ቄሳር” የሮም ንጉሠ ነገሥት የነበረው ጢባርዮስ ነው። ታዲያ ጲላጦስ ይህን ንጉሠ ነገሥት የሚፈራበት ምክንያት ነበረው?

ጢባርዮስ ቄሳር ምን ዓይነት ሰው ነበር? ኢየሱስ ለፍርድ ከመቅረቡ ከዓመታት በፊት ጢባርዮስ “የራሱን ፍላጎት ብቻ ለማርካት የሚጥርና ያሰበውን ነገር ዳር ለማድረስ ሲል ማንኛውንም መጥፎ ድርጊት ከመፈጸም ወደኋላ የማይል ሰው” እንደነበር ዘ ኒው ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ ገልጿል። ከልክ በላይ ተጠራጣሪ ከመሆኑ የተነሳ ከሃዲ ነው ብሎ የጠረጠረውን ማንኛውንም ሰው እንኳ ሳይቀር ያሠቃይ ብሎም ይገድል ነበር። ይኸው የማመሳከሪያ ጽሑፍ አክሎ እንዲህ ብሏል፦ “ጢባርዮስ በኖረበት ዘመን የነበሩ ታሪክ ጸሐፊዎች እንዳሉት ከሆነ በጣም የሚወዳቸው መዝናኛዎች ጭካኔና አስጸያፊ ድርጊቶች የሚንጸባረቅባቸው ነበሩ። ሌላው ሁሉ ቢቀር እንኳ ባሻው ጊዜ የፈለገውን ሰው ይገድል ነበር።”

በመሆኑም ጢባርዮስ ያተረፈው ስም፣ ጲላጦስ በአይሁድ መሪዎች ሐሳብ ተስማምቶ ኢየሱስ እንዲገደል ትእዛዝ እንዲያስተላልፍ ተጽዕኖ አሳድሮበት ሊሆን ይችላል።—ዮሐንስ 19:13-16

ኢየሱስ የሐዋርያቱን እግር ያጠበው ለምንድን ነው?

በጥንት ዘመን ይኖሩ የነበሩት አብዛኞቹ እስራኤላውያን የሚሄዱት በባዶ እግራቸው ነበር። አንዳንዶቹ ጫማ የሚያደርጉ ቢሆኑም እንኳ ጫማዎቹ ቀጭን ማሠሪያ ያላቸው ነጠላ ጫማዎች ነበሩ። መንገዶቹም ሆኑ መስኮቹ አቧራማ ወይም ጭቃማ በመሆናቸው እግራቸው መቆሸሹ አይቀርም ነበር።

ስለሆነም አንድ ሰው ወደ ቤት ሲገባ ጫማውን ማውለቁ የተለመደ ነገር ነበር። አንድን እንግዳ ማስተናገድ እግሩን ማጠብን ይጨምር የነበረ ሲሆን ይህን የሚያደርገው የቤቱ ባለቤት አሊያም አገልጋዩ ነው። ይህ ልማድ በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ላይ ተጠቅሶ ይገኛል። ለምሳሌ ያህል፣ አብርሃም ወደ ድንኳኑ የመጡትን እንግዶች እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ “ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ እዚህም ከዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ። . . . እህል ቀምሳችሁ ትበረቱ ዘንድ ምግብ ላቅርብላችሁ።”—ዘፍጥረት 18:4, 5፤ 24:32፤ 1 ሳሙኤል 25:41፤ ሉቃስ 7:37, 38, 44

እነዚህ ዘገባዎች ኢየሱስ የፋሲካን በዓል ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ ባከበረበት ወቅት እግራቸውን ያጠበው ለምን እንደሆነ እንድንረዳ ያስችሉናል። በዚያን ወቅት የቤቱ ባለቤት ወይም አገልጋይ በስፍራው አልነበረም፤ በተጨማሪም ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ይህን ለማድረግ የተነሳሳ ሰው አልነበረም። በመሆኑም ኢየሱስ በመታጠቢያ ዕቃ ውስጥ ውኃ ጨምሮ የሐዋርያቱን እግር ማጠብና በፎጣ ማድረቅ ጀመረ፤ ይህን በማድረግ ሐዋርያቱ እርስ በርስ እንዲዋደዱና ትሕትና እንዲያሳዩ ግሩም ትምህርት ሰጥቷቸዋል።—ዮሐንስ 13:5-17

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ