የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 1/1 ገጽ 31
  • አንድ ወጣት ያሳየው ድፍረት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አንድ ወጣት ያሳየው ድፍረት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዶምና የገሞራ ጥፋት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ኢየሱስ አድማጮቹን አስደነቀ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 1/1 ገጽ 31

ለወጣት አንባቢያን

አንድ ወጣት ያሳየው ድፍረት

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—1 ሳሙኤል 17:1-11, 26, 32-51⁠ን አንብብ።

የጎልያድ ቁመና እንዲሁም ድምፁ ምን ዓይነት ሊሆን እንደሚችል ግለጽ።

․․․․․

ዳዊት በእስራኤላውያን ጦር ሠራዊት ውስጥ የነበረ ባይሆንም እንኳ ከጎልያድ ጋር በሚደረገው ጦርነት ውስጥ እንዲገባ ያነሳሳው ምን ነበር? (ቁጥር 26⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ዳዊት፣ ይሖዋ እንደሚረዳው እርግጠኛ እንዲሆን ያደረጉት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? (ከ34-37 ያሉትን ቁጥሮች በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ለምርምር የሚረዱ ሌሎች ጽሑፎችን በመጠቀም የሚከተሉትን ለመመለስ ሞክር፦

(1) የጎልያድ ቁመት። (1 ሳሙኤል 17:4)

ከዘጠኝ ጫማ በላይ = ․․․․․

(2) ጎልያድ የለበሰው ጥሩር ክብደት። (1 ሳሙኤል 17:5)

5,000 ሰቅል ናስ = ․․․․․

(3) የጎልያድ የጦሩ ብረት ክብደት። (1 ሳሙኤል 17:7)

600 ሰቅል ብረት = ․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ስለ ድፍረት።

․․․․․

በራስህ ጥንካሬ ከመመካት ይልቅ በይሖዋ ስለ መታመን።

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር።

እንደ ጎልያድ ያለ ምን አስቸጋሪ እንቅፋት ገጥሞሃል?

․․․․․

ይሖዋ አይተወኝም ብለህ እንድታምን ያደረጉህ (የአንተም ሆነ የሌሎች ሰዎች) ተሞክሮዎች አሉ?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ