የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 3/1 ገጽ 24
  • የአልዓዛር ትንሣኤ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአልዓዛር ትንሣኤ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰዶምና የገሞራ ጥፋት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ኢየሱስ አድማጮቹን አስደነቀ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 3/1 ገጽ 24

ለወጣት አንባቢያን

የአልዓዛር ትንሣኤ

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዮሐንስ 11:1-45⁠ን አንብብ።

ቁጥር 21⁠ንና 32⁠ን በምታነብበት ጊዜ በማርታና በማርያም ላይ ይነበብ ስለነበረው ስሜት ምን አስተዋልክ?

․․․․․

በቁጥር 33ና 35 ላይ ኢየሱስ ስሜቱን የገለጸበትን ሁኔታ በዓይነ ሕሊናህ መሳል ትችላለህ?

․․․․․

በቁጥር 43ና 44 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው ታሪክ በተፈጸመበት ወቅት ብትኖር ኖሮ ሁኔታዎቹ ምን ስሜት ሊያሳድሩብህ እንደሚችሉ ለማሰብ ሞክር። አልዓዛርን ብትሆን ኖሮ ምን ይሰማህ ነበር? በቦታው ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ ብትሆን ኖሮስ?

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ኢየሱስ ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ቢታንያ ለመድረስ የሚወስድበት ጊዜ ሁለት ቀን ነበር። ታዲያ ኢየሱስ መዘግየት የፈለገው ለምንድን ነው? (ቁጥር 6⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

መጽሐፍ ቅዱስ ማርያምና ማርታ ለመንፈሳዊ ነገሮች ፍላጎት እንደነበራቸው የሚጠቁመው እንዴት ነው? (ሉቃስ 10:38, 39፤ ዮሐንስ 11:24)

․․․․․

ኢየሱስ እንደገና መሞታቸው ባይቀርም ሰዎችን ከሞት ያስነሳው ለምን ነበር? (ማርቆስ 1:41, 42፤ ዮሐንስ 5:28, 29፤ 11:45)

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ኢየሱስ ሙታንን ለማስነሳት ስላለው ችሎታና ስላሳየው የፈቃደኝነት መንፈስ።

․․․․․

ኢየሱስ ላዘኑ ሰዎች ስላለው ጥልቅ የሆነ የርኅራኄ ስሜት።

․․․․․

በትንሣኤ ማንን ማግኘት ትፈልጋለህ?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ