የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w09 12/1 ገጽ 8
  • ‘የተወሰነው ጊዜ’ ቀርቧል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘የተወሰነው ጊዜ’ ቀርቧል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ የሚሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሰምተህ እርምጃ ት ወ ስ ዳ ለ ህ ን ?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • የምንኖረው “በመጨረሻው ዘመን” ውስጥ ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • የአምላክን መንግሥት በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • በእርግጥ የምንኖረው “በመጨረሻው ዘመን” ውስጥ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
w09 12/1 ገጽ 8

‘የተወሰነው ጊዜ’ ቀርቧል

የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ልክ እንደ ነቢዩ ዕንባቆም መከራና ሥቃይ የሚጠፋበትን ጊዜ ለማየት ይናፍቁ ነበር። የአምላክ መንግሥት በምድር ላይ ያሉትን ችግሮች እንደሚያስተካክል ሲማሩ ኢየሱስን “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የመገኘትህና የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክትስ ምንድን ነው?” በማለት ጠይቀውት ነበር። (ማቴዎስ 24:3) በዚህ ጊዜ ኢየሱስ መንግሥቱ ምድርን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው መቼ እንደሆነ በትክክል የሚያውቀው ይሖዋ አምላክ ብቻ እንደሆነ ገለጸላቸው። (ማቴዎስ 24:36፤ ማርቆስ 13:32) ይሁን እንጂ ኢየሱስም ሆነ ሌሎች ሰዎች ጊዜው መቅረቡን የሚጠቁሙ ክስተቶች እንደሚፈጸሙ ትንቢት ተናግረዋል።—በስተቀኝ ያለውን ሣጥን ተመልከት።

በዛሬው ጊዜ እነዚህ ነገሮች በስፋት እየተፈጸሙ ነው ቢባል አትስማማም? በተጨማሪም ኢየሱስ በምድር ዙሪያ የማስተማር ሥራ እንደሚካሄድ ትንቢት ተናግሮ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለሕዝቦች ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።”—ማቴዎስ 24:14

በዛሬው ጊዜ ይህ ሥራ ልክ ኢየሱስ እንዳለው በመከናወን ላይ ይገኛል። ሥራውን የሚያከናውኑት የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው። ከሰባት ሚሊዮን የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች 236 በሚያህሉ አገሮች ይህ መንግሥት ወደፊት የሚያከናውነውን ነገር ለሰዎች እየተናገሩ ነው፤ እንዲሁም መከራንና ሥቃይን የሚያስወግደው አምላክ ካወጣቸው የጽድቅ መሥፈርቶች ጋር የሚስማማ ሕይወት መምራት እንዲችሉ ሰዎችን እየረዱ ነው። አንተም ስለ አምላክ መንግሥት መማርህን ከቀጠልክ መከራ በማይኖርበት ዓለም ውስጥ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ይኖርሃል።

[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

ስለ መጨረሻዎቹ ቀኖች የሚናገሩ ጥቅሶች

ማቴዎስ 24:6, 7፤ ራእይ 6:4

• ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ጦርነት

ማቴዎስ 24:7፤ ማርቆስ 13:8

• ታላላቅ የምድር ነውጦች

• የምግብ እጥረት

ሉቃስ 21:11፤ ራእይ 6:8

• ቸነፈር

ማቴዎስ 24:12

• እየበዛ የሚሄድ ክፋት

• የፍቅር መቀዝቀዝ

ራእይ 11:18

• ሰዎች ምድርን ማበላሸታቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:2

• ፍቅረ ንዋይ

• ልጆች ለወላጆች አለመታዘዛቸው

• ሰዎች ከመጠን በላይ ራሳቸውን መውደዳቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:3

• ተፈጥሯዊ ፍቅር መጥፋቱ

• ሰዎች ለመስማማት ፈቃደኞች አለመሆናቸው

• በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ራሳቸውን መግዛት አለመቻላቸው

• ሰዎች ጥሩ የሆነውን ነገር አለመውደዳቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:4

• ሰዎች ከአምላክ ይልቅ ደስታን መውደዳቸው

2 ጢሞቴዎስ 3:5

• ግብዝ የሆኑ ብዙ ሰዎች ክርስቲያን እንደሆኑ መናገራቸው

ማቴዎስ 24:5, 11፤ ማርቆስ 13:6

• ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት መነሳታቸው

ማቴዎስ 24:9፤ ሉቃስ 21:12

• እውነተኛ ክርስቲያኖች መሰደዳቸው

ማቴዎስ 24:39

• ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ማስጠንቀቂያዎች ችላ ማለታቸው

[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በምድር ዙሪያ የይሖዋ ምሥክሮች ለሰዎች ስለ አምላክ መንግሥት ያስተምራሉ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ