የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 4/1 ገጽ 15
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ በምድር ላይ እንደኖረ የሚያሳይ ማስረጃ
    ንቁ!—2016
  • አስደናቂዎቹ የጆሴፈስ የታሪክ ጽሑፎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • እምነት ልትጥልበት የምትችል መጽሐፍ​—ክፍል 6
    ንቁ!—2011
  • ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እንደኖረ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 4/1 ገጽ 15

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ኢየሱስ በታሪክ ውስጥ የነበረ ሰው መሆኑን የሚያረጋግጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነ ማስረጃ አለ?

▪ ኢየሱስ በኖረበት ዘመን አካባቢ የነበሩ በርካታ የዓለም ታሪክ ጸሐፊዎች ስለ ኢየሱስ ጠቅሰው ጽፈዋል። ከእነዚህ ጸሐፊዎች አንዱ ቆርኔሌዎስ ታሲተስ ሲሆን ሮም በንጉሥ ነገሥቶች በምትተዳደርበት ወቅት የነበረውን ታሪክ ጽፏል። ታሲተስ በ64 ዓ.ም. በሮም ስለተከሰተው ቃጠሎ ሲጽፍ ለደረሰው ውድመት ተጠያቂው ንጉሠ ነገሥት ኔሮ እንደሆነ የሚገልጽ ወሬ ይናፈስ እንደነበር ገልጿል። ኔሮ አደጋውን በብዙኃኑ ዘንድ ክርስቲያን ተብለው ይጠሩ በነበሩት ሰዎች ላይ ለማሳበብ እንደሞከረ ታሲተስ ዘግቧል። ታሲተስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ክርስቲያን ለሚለው ስም መገኛ የሆነው ክራይስቱስ [ክርስቶስ] በጢባርዮስ የንግሥና ዘመን ጳንጥዮስ ጲላጦስ በተባለው አስተዳዳሪ ተገድሏል።”—አናልስ፣ XV, 44

ፍላቭየስ ጆሴፈስ የተባለው አይሁዳዊ ታሪክ ጸሐፊም ስለ ኢየሱስ ጠቅሷል። ሮማዊው የይሁዳ ገዢ ፊስጦስ በ62 ዓ.ም. ገደማ ከሞተ በኋላና እሱን የተካው አልባይነስ ሥልጣን ከመጨበጡ በፊት ባለው ጊዜ ውስጥ ስለተከናወኑት ነገሮች ጆሴፈስ ሲጽፍ ሊቀ ካህናቱ ሐና (ሐናንያ) “የሳንሄድሪንን ዳኞች ሰብስቦ አንዳንድ ሰዎችንና ያዕቆብ የሚባለውን ሰው በፊታቸው አቀረበ፤ ይህ ሰው ክርስቶስ እየተባለ የሚጠራው የኢየሱስ ወንድም ነው” ብሏል።—ጁዊሽ አንቲኩዊቲስ፣ XX, 200 (ix, 1)

ኢየሱስ፣ ክርስቶስ ተብሎ የተጠራው ለምንድን ነው?

▪ የወንጌል ዘገባዎች መልአኩ ገብርኤል ማርያም እንደምትፀንስ ለመንገር በተገለጠላት ጊዜ ልጇን ኢየሱስ ብላ ልትጠራው እንደሚገባ እንደነገራት ይገልጻሉ። (ሉቃስ 1:31) በጥንት ዘመን የነበሩት አይሁዳውያን በዚህ ስም በብዛት ይጠቀሙ ነበር። ጆሴፈስ የተባለው አይሁዳዊ ታሪክ ጸሐፊ፣ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ከተጠቀሱት ሌላ ‘ኢየሱስ’ በሚለው ስም ስለሚጠሩ ሌሎች 12 ሰዎች ጠቅሷል። የማርያም ልጅ “የናዝሬቱ ኢየሱስ” ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ይህም የናዝሬት ነዋሪ መሆኑን ስለሚጠቁም የትኛው ኢየሱስ መሆኑን ለመለየት ይረዳ ነበር። (ማርቆስ 10:47) የማርያም ልጅ፣ “ክርስቶስ” ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ በመባልም ይታወቃል። (ማቴዎስ 16:16 አ.መ.ት) ይህ መጠሪያ ምን ትርጉም አለው?

“ክርስቶስ” የሚለው የአማርኛ ቃል የመጣው ክሪስቶስ ከሚለው የግሪክኛ ቃል ሲሆን ማሺያክ (መሲሕ) ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው። ሁለቱም ቃላት በቀጥታ ሲተረጎሙ “የተቀባ” የሚል ፍቺ አላቸው። ይህ መጠሪያ ከኢየሱስ በፊት ለሌሎች ሰዎችም ተሠርቶበታል። ለምሳሌ ሙሴ፣ አሮንና ንጉሥ ዳዊት የተቀቡ እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም አምላክ ኃላፊነትና ሥልጣን በመስጠት እንደሾማቸው የሚያሳይ ነው። (ዘሌዋውያን 4:3፤ 8:12፤ 2 ሳሙኤል 22:51፤ ዕብራውያን 11:24-26) እንደሚመጣ አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ ይኸውም ኢየሱስ የይሖዋ ዋነኛ ወኪል ነበር። በመሆኑም ኢየሱስ፣ “ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ” ተብሎ መጠራቱ የተገባ ነው።—ማቴዎስ 16:16 አ.መ.ት፤ ዳንኤል 9:25

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የፍላቭየስ ጆሴፈስን ምስል የሚያሳይ ሥዕል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ