ለታዳጊ ወጣቶች
አምላክ አያዳላም
መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።
ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ቆርኔሌዎስና ጴጥሮስ
ታሪኩ በአጭሩ፦ ጴጥሮስ ከአሕዛብ ወገን ለነበረው ለቆርኔሌዎስ በመስበክ የማያዳላውን አምላክ ምሳሌ ተከትሏል።
1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—የሐዋርያት ሥራ 10:1-35, 44-48ን አንብብ።
ቆርኔሌዎስ ምን ዓይነት መልክና ቁመና ያለው ይመስልሃል?
․․․․․
ከቁጥር 3 እስከ 6 ላይ በተገለጸው መሠረት ቆርኔሌዎስ መልአኩ ሲያነጋግረው ምን ዓይነት ስሜት የተሰማው ይመስልሃል?
․․․․․
በቁጥር 7 እና 8 ላይ በተጠቀሰው መሠረት በቆርኔሌዎስና በአገልጋዮቹ መካከል ምን ዓይነት ውይይት የተካሄደ ይመስልሃል?
․․․․․
2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ከቁጥር 10 እስከ 16 ላይ የሚገኘው ለጴጥሮስ የቀረበው ምሳሌ ውጤታማ የነበረው ለምንድን ነው? (ፍንጭ፦ ቁጥር 14 እንደሚጠቁመው ጴጥሮስ አይሁዳዊ መሆኑን ግምት ውስጥ አስገባ።)
․․․․․
ከቁጥር 25 መመልከት እንደሚቻለው ቆርኔሌዎስ ምን ዓይነት ባሕርይ ነበረው? የእሱ ዓይነት ሥልጣን ያለው ሰው እንዲህ ዓይነት ባሕርይ ማሳየቱ ያልተለመደ የሆነው ለምንድን ነው? (ፍንጭ፦ ቁጥር 1ን ተመልከት።)
․․․․․
ምርምር ማድረግ የምትችልባቸው መሣሪያዎችን በመጠቀም በቆርኔሌዎስ ሥልጣን ሥር ባለው የጣሊያን ጦር ሠራዊት ውስጥ ምን ያህል ሰዎች እንዳሉ ለማወቅ ሞክር።
․․․․․
ቆርኔሌዎስ ሃይማኖቱን መለወጡ በጣም አስገራሚ የሆነው ለምንድን ነው?
․․․․․
3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦
ምሳሌዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ስለ መጠቀም።
․․․․․
አምላክ የማያዳላ ስለ መሆኑ።
․․․․․
አንተ ራስህ የማታዳላ መሆንህን ማሳየት ስለምትችልበት መንገድ።
․․․․․
4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ይበልጥ ትምህርት ያገኘህበት ሐሳብ የትኛው ነው? ለምን እንዲህ አልክ?
․․․․․
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።