የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 11/1 ገጽ 3
  • ባለን ረክተን መኖር እንችላለን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ባለን ረክተን መኖር እንችላለን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ባለህ ረክተህ የመኖርን “ሚስጥር” ተምረሃል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በመከተል እርካታና ደስታ ማግኘት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ጓደኞችህን በጥበብ ምረጥ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 11/1 ገጽ 3

ባለን ረክተን መኖር እንችላለን?

“ረክቶ መኖር ድሃ የሆኑ ሰዎችን ባለጠጋ ያደርጋል፤ አለመርካት ደግሞ ሀብታም የሆኑ ሰዎችን ድሃ ያደርጋል።” —ቤንጃሚን ፍራንክሊን

ከዚህ አባባል ጋር በሚስማማ ሁኔታ ብዙ ሰዎች ረክቶ መኖርን እንደ ዕቃ በገንዘብ መግዛት እንደማይቻል ተገንዝበዋል። በመሆኑም ተጨማሪ ንብረት ማፍራትን፣ የተሻለ ስኬት ማግኘትን ወይም ሌሎች የደረሱበት የኑሮ ደረጃ ላይ መድረስን በሚያበረታታው በዚህ ዓለም ውስጥ ሰዎች ባላቸው ነገር ረክተው ወይም ደስተኛ ሆነው መኖር አለመቻላቸው ምንም አያስገርምም! ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ተጽዕኖ አድርገውብህ ያውቃሉ?

• ማስታወቂያዎች አንድ ተጨማሪ ነገር ብትገዛ ረክተህ መኖር እንደምትችል የሚገልጹ መልእክቶች ያዥጎደጉዱብሃል።

• በሥራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት ያለው የፉክክር መንፈስ፣ ዋጋማነትህ የሚለካው ሌሎች ያከናወኑትን ነገር ማድረግ በመቻልህ ላይ እንደሆነ እንዲሰማህ ያደርግሃል።

• ሰዎች ለምታደርግላቸው ነገር አድናቆት የላቸውም።

• ጓደኞችህ ባላቸው ነገር ያስቀኑሃል።

• ሕይወትን በተመለከተ ለምታነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ አላገኘህም።

እንደነዚህ ያሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች እያሉም እንኳ ረክተህ መኖር ትችላለህ? ሐዋርያው ጳውሎስ ‘ረክቶ የመኖርን ሚስጥር’ ጠቅሶ ተናግሯል። ብዙ አግኝቶም ሆነ በትንሽ ነገር የኖረባቸው ጊዜያት ነበሩ። ወዳጆቹ ያደንቁት የነበረ ቢሆንም ሌሎች ደግሞ ያፌዙበት ነበር። ሆኖም “በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብሆን ባለኝ ረክቼ መኖርን ተምሬያለሁ” ብሏል።—ፊልጵስዩስ 4:11, 12

ረክቶ ለመኖር የሚያስችሏቸውን እርምጃዎች ወስደው የማያውቁ ሰዎች ረክቶ መኖር የሚለው ሐሳብ ሚስጥር ይሆንባቸዋል፤ ሆኖም ጳውሎስ እንደተናገረው ረክቶ መኖርን መማር ይቻላል። የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትንና ባለን ረክተን ለመኖር የሚረዱንን አምስት ቁልፍ ነገሮች እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ