ለታዳጊ ወጣቶች
ፈተናዎችን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?
ዮሴፍ—ክፍል 1
መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።
ዋነኞቹ ባለ ታሪኮች፦ ዮሴፍና የጲጢፋራ ሚስት
ታሪኩ በአጭሩ፦ ዮሴፍ የጲጢፋራ ሚስት ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት እንዲፈጽም ያቀረበችለትን ፈተና ተቋቋመ።
1 ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፍጥረት 39:1-12ን አንብብ።
የጲጢፋራን ቤት በአእምሮህ ለማሰብ ሞክርና ምን ያህል ትልቅና የሚያምር እንደሆነ ግለጽ።
․․․․․
የዮሴፍ ቁመና ምን ሊመስል እንደሚችል ግለጽ። (ፍንጭ፦ ቁጥር 6ን በድጋሚ አንብብ።)
․․․․․
ዮሴፍ በቁጥር 8 እና 9 ላይ የጲጢፋራን ሚስት ሲያናግራት ምን ዓይነት የድምፅ ቃና የነበረው ይመስልሃል?
․․․․․
2 ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ዮሴፍ የሥነ ምግባር አቋሙን ለማላላት በቀላሉ ሊፈተን ይችል ነበር የምንለው ለምንድን ነው? (ፍንጭ፦ ፊልጵስዩስ 2:12ን አንብብ፤ ከዚያም ዮሴፍ ስለነበረበት ሁኔታ አስብ። ለምሳሌ ያህል፣ ቤተሰቦቹና እንደ እሱ ይሖዋን የሚያመልኩ ሰዎች በወቅቱ የሚኖሩት የት ነበር?)
․․․․․
በዚያ ጊዜ አምላክ ዝሙትን የሚከለክል ሕግ ባይሰጥም ዮሴፍ ዝሙት መፈጸም በአምላክ ላይ ኃጢአት መሥራት እንደሆነ አድርጎ የቆጠረው ለምን ይመስልሃል? (ፍንጭ፦ የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብና አሰላስልባቸው፦ ዘፍጥረት 2:24፤ 12:17, 18፤ ሮም 2:14, 15፤ ዕብራውያን 5:14)
․․․․․
3 ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦
ራስን የመግዛት ባሕርይ ማሳየት ለራሳችን አክብሮት እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ስላለው አስተዋጽኦ።
․․․․․
አምላክ ያወጣቸውን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች በጥብቅ መከተል ስለሚያስገኘው ጥቅም።
․․․․․
‘የማስተዋል ችሎታህን’ ማሠልጠን አስፈላጊ ስለመሆኑ። (ዕብራውያን 5:14)
․․․․․
ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር።
የፆታ ፈተናን ከመቋቋም ጋር በተያያዘ ይበልጥ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ የሚኖርብህ መቼ ነው? (ፍንጭ፦ ኢዮብ 31:1ን፤ መዝሙር 119:37ን እና ኤፌሶን 5:3, 4ን አንብብና አሰላስልባቸው።)
․․․․․
4 ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?
․․․․․
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎች ለማግኘት የይሖዋ ምሥክሮችን ጠይቅ ወይም www.watchtower.org ተመልከት።