የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w12 9/1 ገጽ 3
  • የሴት ልጅ አበሳ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የሴት ልጅ አበሳ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ በእርግጥ ለሴቶች ያስብላቸዋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት—ዓለም አቀፍ ችግር
    ንቁ!—2008
  • ሴቶች በአሁኑ ጊዜ ይከበራሉን?
    ንቁ!—1995
  • ሴቶች፣ በቤታቸው ውስጥ ይከበራሉን?
    ንቁ!—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
w12 9/1 ገጽ 3

የሴት ልጅ አበሳ
ወንዶች በሚበዙበት ከፍል ውስጥ የምትማር አንዲት ልጅ

“በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ግፍ ስመለከት ሴት መሆኔ ያስጠላኛል።”—ዛህራ፣ የ15 ዓመት ወጣት፣ ጂኢኦ መጽሔት፣ የፈረንሳይኛ እትም

ከላይ የተጠቀሰችው ወጣት የተናገረችው ሐሳብ በዓለም ዙሪያ የሚታየውን አሳዛኝ እውነታ ቁልጭ አድርጎ ይገልጻል፤ በማንኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶች ሕይወታቸውን ሙሉ ዓመፅና መድልዎ ይፈጸምባቸዋል። እስቲ ቀጥሎ የቀረቡትን መረጃዎች እንመልከት፦

  • የፆታ መድልዎ፦ በእስያ አብዛኞቹ ወላጆች፣ ወንዶች ልጆችን ቢወልዱ ይመርጣሉ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በ2011 ባወጣው ዘገባ ላይ የቀረበ ግምታዊ አኃዝ እንደሚያሳየው በዚህ የዓለም ክፍል 134 ሚሊዮን የሚያህሉ ሴት ሕፃናት ውርጃ ይፈጸምባቸዋል፤ በጨቅላነታቸው ይገደላሉ፤ እንዲሁም ተገቢው አያያዝ ሳይደረግላቸው በመቅረቱ ይሞታሉ።

  • ትምህርት፦ በመላው ዓለም ጨርሶ የትምህርት ዕድል ከማያገኙት ወይም ከአራት ዓመት የበለጠ ከማይማሩት ሰዎች መካከል ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት ሴቶችና ልጃገረዶች ናቸው።

  • ፆታዊ ትንኮሳ፦ ከ2.6 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶች የሚኖሩት በትዳር ጓደኛ መደፈር እንደ ወንጀል በማይቆጠርባቸው አገሮች ነው።

  • ጤና፦ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ መሠረታዊ የጤና ክትትል ባለመኖሩ፣ ከእርግዝና ወይም ከወሊድ ጋር ተያይዘው በሚመጡ ችግሮች የተነሳ በየሁለት ደቂቃው አንዲት ሴት ትሞታለች።

  • የንብረት ባለቤትነት መብት፦ በዓለም ላይ ካለው ሰብል ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የሚያመርቱት ሴቶች ቢሆኑም በብዙ አገሮች የንብረት ባለቤት የመሆን ወይም መሬት የመውረስ ሕጋዊ መብት የላቸውም።

የተጨነቀች ሴት

ሴቶች እንደነዚህ ያሉት መሠረታዊ መብቶች የተነፈጓቸው ለምንድን ነው? በአንዳንድ ባሕሎች ውስጥ ሴቶችን መበደልንና በእነሱ ላይ ጥቃት መሰንዘርን የሚያበረታቱ ብሎም ትክክል እንደሆነ አድርገው የሚያቀርቡ ሃይማኖታዊ እምነቶች አሉ። አንድ የፈረንሳይ ዕለታዊ ጋዜጣ፣ ቻንድራ ራሚ ቾፕራን የተባሉ ሕንዳዊ የሕግ ባለሙያ እንደሚከተለው በማለት እንደተናገሩ ጠቅሷል፦ “በሁሉም ሃይማኖቶች ውስጥ ያሉትን ሕጎች የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፤ ሁሉም በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን መድልዎ ይደግፋሉ።”

አንተስ በዚህ ትስማማለህ? በርካታ የሃይማኖት መጻሕፍት እንደሚያደርጉት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስም ሴቶች ዝቅ ተደርገው እንዲታዩ የሚያደርግ ይመስልሃል? አንዳንዶች፣ እንዲህ ያለውን አመለካከት የሚያበረታቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንዳሉ ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው አምላክ ለሴቶች ያለው አመለካከት ምንድን ነው? ይህ ጥያቄ ብዙዎች ስሜታዊ እንዲሆኑ የሚያደርግ ጉዳይ ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ሚዛናዊ ሆነን በጥልቀት መመርመራችን መልሱን ለማግኘት ይረዳናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ