የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 3/1 ገጽ 14-15
  • ጴጥሮስና ሐናንያ ዋሹ—ከዚህ ምን እንማራለን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጴጥሮስና ሐናንያ ዋሹ—ከዚህ ምን እንማራለን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መዋሸት የሌለብን ለምንድን ነው?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ያለብንን ፍርሃት ለማሸነፍ የሚያስችል እርዳታ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ይቅር ባይነትን ከጌታው ተምሯል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ይቅር ባይነትን ከጌታው ተምሯል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 3/1 ገጽ 14-15

ልጆቻችሁን አስተምሩ

ጴጥሮስና ሐናንያ ዋሹ ከዚህ ምን እንማራለን?

እንደምታውቀው መዋሸት ማለት እውነት ያልሆነ ነገር መናገር ማለት ነው። ውሸት ተናግረህ ታውቃለህ?—a አምላክን የሚወዱ አንዳንድ ትላልቅ ሰዎች እንኳ ውሸት ተናግረው ያውቃሉ። ምናልባት አንተም ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ውስጥ አምላክን የሚወዱ ሆኖም ውሸት የተናገሩ ሰዎችን ታውቅ ይሆናል። ከእነዚህ አንዱ ጴጥሮስ ሲሆን ይህ ሰው ከ12ቱ የኢየሱስ ሐዋርያት አንዱ ነበር። ውሸት የተናገረው ለምን እንደነበረ ታሪኩን እንመርምር።

[በገጽ 14 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኢየሱስ ከተያዘ በኋላ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት ተወሰደ። በዚህ ጊዜ እኩለ ሌሊት አልፏል። ጴጥሮስም ሳይታወቅ ወደ ካህኑ ግቢ ሹልክ ብሎ ገባ። ለጴጥሮስ በር የከፈተችለት የሊቀ ካህናቱ አገልጋይ በእሳቱ ብርሃን ስታየው አወቀችው። እሷም “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርክ” አለችው። ጴጥሮስ ግን ፈርቶ ከኢየሱስ ጋር እንዳልነበረ ተናገረ።

ቆየት ብሎም ‘ሌላ ሴት እንዳየችው’ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። እሷም “ይህ ሰው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበር” አለች። ጴጥሮስ አሁንም ካደ። ጥቂት ቆይቶ ሌሎች ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀርበው “በእርግጥ አንተም ከእነሱ አንዱ ነህ!” አሉት።

ጴጥሮስ በጣም ፈራ። ስለዚህ ለሦስተኛ ጊዜ “ሰውየውን አላውቀውም!” ብሎ ዋሸ። በዚህ ጊዜ ዶሮ ጮኸ። ኢየሱስ ጴጥሮስን ተመለከተው፤ ይሄን ጊዜ ጴጥሮስ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ኢየሱስ “ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው ትዝ አለው። ጴጥሮስ በጣም ስላዘነ ምርር ብሎ አለቀሰ!

[በገጽ 15 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ታዲያ በአንተ ላይ እንዲህ ዓይነት ነገር ሊደርስ ይችላል?— ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ሲያወሩ ሰማህ እንበል። አንዱ ልጅ “ለባንዲራ ሰላምታ አይሰጡም” ይላል። ሌላው ደግሞ “ለአገራቸው አይዋጉም” ይላል። ሦስተኛው ልጅ ደግሞ “ገናን ስለማያከብሩ ክርስቲያኖች አይደሉም” ብሎ ይናገራል። ከዚያም አንዱ ልጅ ወደ አንተ ዞር ብሎ “የይሖዋ ምሥክር ነህ አይደል?” ብሎ ይጠይቅሃል። በዚህ ጊዜ ምን ትለዋለህ?—

እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥምህ ጥሩ መልስ መስጠት እንድትችል አስቀድመህ መዘጋጀት ያስፈልግሃል። ጴጥሮስ አልተዘጋጀም ነበር። በመሆኑም ድንገት ከባድ ተጽዕኖ ሲያጋጥመው ዋሸ! ሆኖም ባደረገው ነገር በጣም ስለተጸጸተ አምላክ ይቅር ብሎታል።

በጥንት ጊዜ ይኖር የነበረ ሐናንያ የተባለ አንድ የኢየሱስ ተከታይም ዋሽቷል። ይሁን እንጂ አምላክ ለእሱም ሆነ ለሚስቱ ለሰጲራ ይቅርታ አላደረገላቸውም። ሰጲራ ውሸት ለመናገር ከባሏ ጋር ተስማምታ ነበር። አምላክ ለሐናንያም ሆነ ለሰጲራ ይቅርታ ያላደረገላቸው ለምን እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

ኢየሱስ ሐዋርያቱን ተሰናብቶ ወደ ሰማይ ከሄደ ከአሥር ቀን በኋላ 3,000 የሚያህሉ ሰዎች በኢየሩሳሌም ተጠምቀው ደቀ መዛሙርት ሆኑ። አብዛኞቹ የጴንጤቆስጤን በዓል ለማክበር ከሩቅ አገሮች የመጡ ሲሆኑ የኢየሱስ ተከታዮች ከሆኑ በኋላ ደግሞ ስለ አዲሱ እምነታቸው ተጨማሪ ነገር ለማወቅ ለጥቂት ቀናት እዚያው ኢየሩሳሌም መቆየት ፈለጉ። ስለዚህ አንዳንዶቹ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ገንዘባቸውን እነዚህን ክርስቲያኖች ለማስተናገድ ተጠቀሙበት።

ሐናንያና ሚስቱ አዲስ የተጠመቁትን ደቀ መዛሙርት ለመርዳት ሲሉ መሬታቸውን ሸጡ። ሐናንያ ገንዘቡን ወደ ሐዋርያት በወሰደ ጊዜ ከሽያጩ ያገኘውን ገንዘብ በሙሉ እንዳመጣ ተናገረ። ይህ ግን እውነት አይደለም! የተወሰነውን ገንዘብ ለራሱ አስቀርቷል! አምላክ ይህን ጉዳይ ለጴጥሮስ ስላሳወቀው ሐናንያን “ያታለልከው ሰውን ሳይሆን አምላክን ነው” አለው። ወዲያውኑ ሐናንያ ወድቆ ሞተ! ከሦስት ሰዓት በኋላ ሚስቱ መጣች። ሰጲራም በባሏ ላይ የደረሰውን ነገር ስላላወቀች ዋሸች፤ በዚህ ጊዜ እሷም ወድቃ ሞተች።

እውነቱን መናገር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ የሚያስገነዝብ እንዴት ያለ ጠቃሚ ትምህርት ነው! አዎን፣ ሁላችንም ከእነዚህ ታሪኮች ትምህርት ማግኘት ይኖርብናል! ሆኖም ሁላችንም በተለይ ትናንሽ ልጆች ሳለን ስህተት መሥራታችን አይቀርም። ይሖዋ እንደሚወድህና እንደ ጴጥሮስ ሁሉ አንተንም ይቅር እንደሚልህ ማወቅህ አያስደስትህም?— ቢሆንም እውነት መናገር እንደሚያስፈልገን አትዘንጋ። እንዲሁም በመዋሸት ትልቅ ስህተት ከሠራን ይቅርታ እንዲያደርግልን አምላክን መለመን ያስፈልገናል። ጴጥሮስ ያደረገው ይህንኑ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ይቅርታ ተደርጎለታል። ከእንግዲህ ላለመዋሸት ከልብ ጥረት ካደረግን አምላክ ለእኛም ይቅርታ ያደርግልናል!

ከመጽሐፍ ቅዱስህ ላይ

  • ማቴዎስ 26:69-75⁠ን

  • የሐዋርያት ሥራ 2:38-42⁠ን፣ 4:32-37⁠ን እና 5:1-11⁠ን አንብብ።

a ይህን ርዕስ የምታነበው ከትንሽ ልጅ ጋር ከሆነ፣ ይህ ሰረዝ ቆም ብለህ ልጁ ሐሳቡን እንዲገልጽ እንድታበረታታው ለማስታወስ ተብሎ የተደረገ ነው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ