የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 12/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ኢየሱስ ወደፊት ምን ያደርጋል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • አምላክ መላውን ምድር የሚያስተዳድር አንድ መንግሥት ያቋቁማል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ስለ አምላክ መንግሥት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 12/1 ገጽ 16
[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ክርስቶስ ተመልሶ የሚመጣበት ዓላማ ምንድን ነው?

ኢየሱስ በ33 ዓ.ም. ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት፣ ተመልሶ እንደሚመጣ ቃል ገብቷል። ኢየሱስ፣ ለረጅም ጊዜ ወደ ሩቅ አገር ከሄደ በኋላ ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተረክቦ ከሚመለስ አንድ መስፍን ጋር ራሱን አመሳስሏል። ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣበት ዓላማ ለሰው ልጆች መልካም አስተዳደር ለማስፈን ነው።—ሉቃስ 19:11, 12⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ ለሰው ዘሮች መልካም አስተዳደር ያመጣላቸዋል

ክርስቶስ የሚመለሰው በምን ዓይነት አካል ነው? ከሙታን የተነሳው የማይታይ መንፈሳዊ አካል ሆኖ ነው። (1 ጴጥሮስ 3:18) ከዚያም ወደ ሰማይ ሄዶ በአምላክ ቀኝ ተቀመጠ። (መዝሙር 110:1) በጣም ቆይቶ ደግሞ “ጥንታዌ ጥንቱ” በሆነው በይሖዋ አምላክ ፊት የቀረበ ሲሆን እሱም በሰው ልጆች ላይ የመግዛት ሥልጣን ሰጠው። ስለዚህ ኢየሱስ የሚመለሰው ሰው ሆኖ ሳይሆን በዓይን የማይታይ ንጉሥ ሆኖ ነው።—ዳንኤል 7:13, 14⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ ምን ያደርጋል?

[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኢየሱስ በዓይን በማይታይ ሁኔታ ከመላእክቱ ጋር ተመልሶ ሲመጣ በሰው ዘሮች ላይ ይፈርዳል። ክፉ ሰዎችን የሚያጠፋ ሲሆን እሱን እንደ ንጉሣቸው አድርገው ለተቀበሉት ግን ዘላለማዊ ሕይወት ይሰጣቸዋል።—ማቴዎስ 25:31-33, 46⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ሲገዛ ምድርን ወደ ገነትነት ይለውጣታል። እንዲሁም ሙታንን በማስነሳት ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ተደስተው እንዲኖሩ ያደርጋል።—ሉቃስ 23:42, 43⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 73-85 ተመልከት

www.jw.org/am ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማውረድ ይቻላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ