የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 4/1 ገጽ 16
  • ኢየሱስ ወደፊት ምን ያደርጋል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ወደፊት ምን ያደርጋል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 4/1 ገጽ 16
ኢየሱስ በጨርቅ ምድርን ሲያጸዳ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ኢየሱስ ወደፊት ምን ያደርጋል?

ኢየሱስ በ33 ዓ.ም. ሞቶ ከተነሳ በኋላ ወደ ሰማይ አርጓል። ይህ ከሆነ ከብዙ ጊዜ በኋላ ደግሞ ኢየሱስ ንጉሥ እንዲሆን ሥልጣን ተሰጥቶታል። (ዳንኤል 7:13, 14) ወደፊት ኢየሱስ ይህን ንጉሣዊ ሥልጣኑን ተጠቅሞ ሰላምን በዓለም በሙሉ ያሰፍናል፤ እንዲሁም ድህነትን ያስወግዳል።—መዝሙር 72:7, 8, 13⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ክፋትን ከምድር ላይ ጠራርጎ ያስወግዳል

ኢየሱስ የሰው ልጆችን በሚያስተዳድርበት ወቅት በርካታ አስደናቂ ነገሮችን ያከናውናል። አባቱ የሰጠውን ኃይል ተጠቅሞ የሰው ልጆች ፍጹማን እንዲሆኑ ያደርጋል። በዚያን ጊዜ እርጅናና ሞት ከምድር ላይ ስለሚወገዱ የሰው ልጆች ደስታ የተሞላበት ሕይወት ያጣጥማሉ።—ዮሐንስ 5:26-29⁠ን እና 1 ቆሮንቶስ 15:25, 26⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ ምን እያደረገ ነው?

በአሁኑ ጊዜ ኢየሱስ፣ እውነተኛ ተከታዮቹ በዓለም ዙሪያ የሚያከናውኑትን የስብከት ሥራ በበላይነት እየመራ ነው። የኢየሱስ ተከታዮች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ መንግሥት ምን እንደሚል ለሰዎች ያስተምራሉ። የአምላክ መንግሥት ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ እስከሚያጠፋበት ጊዜ ድረስ ተከታዮቹ የሚያከናውኑትን ሥራ መደገፉን እንደሚቀጥል ኢየሱስ ተናግሯል።—ማቴዎስ 24:14ን እና ማቴዎስ 28:19, 20ን አንብብ።

ኢየሱስ፣ እውነተኛውን የክርስቲያን ጉባኤ በመጠቀም ሰዎች የተሻለ ሕይወት እንዲመሩ እያደረገ ነው። እንዲሁም እነዚህ ሰዎች በዚህ ክፉ ሥርዓት ላይ ከሚደርሰው ጥፋት ተርፈው አምላክ ቃል ወደገባው አዲስ ዓለም እንዲገቡ ያደርጋቸዋል።—2 ጴጥሮስ 3:7, 13⁠ን እና ራእይ 7:17⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ