የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 10/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 10/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የአምላክ መንግሥት እንዲመጣ የምንጸልየው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክን መንግሥት ጠላቶች ድል ለማድረግ ሲገሰግስ

ስለ አምላክ መንግሥትና ወደፊት ስለሚያከናውናቸው ነገሮች የበለጠ ለማወቅ ትፈልጋለህ?

ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክን መንግሥት ጠላቶች ድል ለማድረግ ሲገሰግስ

ስለ አምላክ መንግሥትና ወደፊት ስለሚያከናውናቸው ነገሮች የበለጠ ለማወቅ ትፈልጋለህ?

የአምላክ መንግሥት በሰማይ የተቋቋመ መስተዳድር ነው። ይህ መንግሥት በምድር ላይ ጽድቅና ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል፤ ኢየሱስ መንግሥቱ እንዲመጣ እንዲጸልዩ ተከታዮቹን ያስተማራቸው ለዚህ ነው። ዓመፅን፣ ግፍን ወይም በሽታን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የሚችል የሰው መንግሥት የለም፤ ይህን ማድረግ የሚችለው እንዲሁም የሚያደርገው የአምላክ መንግሥት ብቻ ነው። አምላክ ልጁን ኢየሱስን የዚህ መንግሥት ንጉሥ እንዲሆን መርጦታል። በተጨማሪም ይሖዋ ከኢየሱስ ተከታዮች መካከል ከኢየሱስ ጋር አብረው የሚገዙ ሰዎችን መርጧል።—ሉቃስ 11:2⁠ን እና ሉቃስ 22:28-30⁠ን አንብብ።

በቅርቡ የአምላክ መንግሥት የአምላክን አገዛዝ በሚቃወሙ ሁሉ ላይ እርምጃ ይወስዳል። በመሆኑም የአምላክ መንግሥት እንዲመጣ ስንጸልይ አምላክ ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ አጥፍቶ በምትኩ የእሱ መንግሥት እንዲያስተዳድረን መለመናችን ነው።—ዳንኤል 7:13, 14⁠ን እና ራእይ 11:15, 18⁠ን አንብብ።

የአምላክ መንግሥት ለሰዎች ጥቅም ያስገኛል የምንለው ለምንድን ነው?

ኢየሱስ ርኅሩኅ ስለሆነ ከሁሉ የተሻለ ንጉሥ ነው። በተጨማሪም የአምላክ ልጅ እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ ኃይል አለው፤ በመሆኑም አምላክ እንዲረዳቸው የሚለምኑትን ሁሉ ሊረዳቸው ይችላል።—መዝሙር 72:8, 12-14⁠ን አንብብ።

የአምላክ መንግሥት እንዲመጣ ከልብ የሚጸልዩና ሕይወታቸውን ከአምላክ ፈቃድ ጋር አስማምተው የሚኖሩ ሁሉ ይህ መንግሥት ከሚያስገኘው ጥቅም ተቋዳሽ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ መንግሥት የሚናገረውን መማር ፈጽሞ የማያስቆጭ ነው።—ሉቃስ 18:16, 17⁠ን እና ዮሐንስ 4:23⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ