የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 1/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለፍትሕ መጓደል ልንሰጥ የሚገባው ምላሽ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ሰዎች ፍትሕ ለማግኘት የሚያሰሙት ጩኸት ተሰሚነት ያገኝ ይሆን?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የፍትሕ መጓደልን መቋቋም ትችላለህ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • “አምላክ ፍትሕ ያዛባል?”
    ወደ ይሖዋ ቅረብ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 1/1 ገጽ 16
በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ እናትና ልጅ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

አምላክ ምን ዓይነት ነው?

አምላክ በዓይን የማይታይ መንፈሳዊ አካል ነው። ሰማያትን፣ ምድርንና ሕይወት ያላቸውን ነገሮች ሁሉ የፈጠረው እሱ ነው። አምላክን ማንም አልፈጠረውም፤ መጀመሪያም የለውም። (መዝሙር 90:2) አምላክ ሰዎች ወደ እሱ እንዲቀርቡና ስለ እሱ እውነቱን እንዲያውቁ ይፈልጋል።—የሐዋርያት ሥራ 17:24-27⁠ን አንብብ።

አምላክ የግል ስም ያለው መንፈሳዊ አካል ነው። በፍጥረት ሥራዎቹ ላይ በማሰላሰል አንዳንድ ባሕርያቱን ማስተዋል እንችላለን። (ሮም 1:20) ይሁንና ስለ አምላክ በሚገባ ለማወቅ ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ግሩም ባሕርያት እንድናውቅ ያስችለናል።—መዝሙር 103:7-10⁠ን አንብብ።

አምላክ ስለ ፍትሕ መጓደል ምን ይሰማዋል?

ፈጣሪያችን ይሖዋ የፍትሕ መጓደልን ይጠላል። ሰዎችንም ቢሆን የፈጠራቸው በራሱ አምሳል ነው። (ዘዳግም 25:16) ብዙዎቻችን የፍትሕ መጓደልን የምንጠላው ለዚህ ነው። በአካባቢያችን እየተፈጸመ ላለው የፍትሕ መጓደል ተጠያቂው አምላክ አይደለም። አምላክ ለሰው ልጆች የመምረጥ ነፃነት ሰጥቷቸዋል። የሚያሳዝነው ግን ብዙ ሰዎች የመምረጥ ነፃነታቸውን አላግባብ የሚጠቀሙበት ሲሆን ፍትሕ የጎደለው ድርጊትም ይፈጽማሉ። ይሖዋ ይህን ሲመለከት ልቡ እጅግ ያዝናል።—ዘፍጥረት 6:5, 6⁠ን እና ዘዳግም 32:4, 5⁠ን አንብብ።

ይሖዋ ፍትሕን ይወዳል፤ ስለሆነም የፍትሕ መጓደልን ለዘላለም ታግሦ አይኖርም። (መዝሙር 37:28, 29) መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ በቅርቡ ማንኛውንም ዓይነት የፍትሕ መጓደል እንደሚያስወግድ ይገልጻል።—2 ጴጥሮስ 3:7-9, 13⁠ን አንብብ።

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ በቅርቡ ፍትሕ እንደሚያሰፍን ይገልጻል

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 1 ተመልከት።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ