የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w14 5/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ክፋትና መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?
    ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
  • አምላክ ክፋትና መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው?
    ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው?
  • መከራና ሥቃይ የበዛው ለምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
w14 5/1 ገጽ 16

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ይህን ዓለም እየገዛ ያለው ማን ነው?

ጦርነትን፣ ወንጀልን፣ ዓመፅንና የተፈጥሮ አደጋን የሚያሳዩ ሥዕሎች

ይህን ዓለም እየገዛ ያለው አምላክ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ መከራ ይኖር ነበር?

ብዙ ሰዎች የዚህ ዓለም ገዢ እውነተኛው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂ ይህ እውነት ቢሆን ኖሮ ምድር ይህን ያህል በመከራ ትሞላ ነበር? (ዘዳግም 32:4, 5) መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ከሆነ ዓለም ክፉ በሆነ ኃይል ቁጥጥር ሥር ነው።—1 ዮሐንስ 5:19⁠ን አንብብ።

ለመሆኑ አንድ ክፉ ኃይል የሰውን ዘር የመቆጣጠር ሥልጣን እንዴት ሊኖረው ቻለ? በሰው ልጆች ታሪክ መጀመሪያ ላይ አንድ መልአክ በአምላክ ላይ ያመፀ ሲሆን የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስትም ከእሱ ጋር እንዲያብሩ ገፋፋቸው። (ዘፍጥረት 3:1-6) እነሱም ሰይጣን የተባለውን ዓመፀኛ መልአክ ለመታዘዝ በመምረጥ ገዢያቸው አደረጉት። የሰው ልጆችን ለመግዛት ሕጋዊ መብት ያለው ብቸኛው አካል ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ቢሆንም ሰዎች በፍቅር ተገፋፍተው እንዲገዙለት ይፈልጋል። (ዘዳግም 6:6፤ 30:16, 19) የሚያሳዝነው ግን አብዛኛው የሰው ዘር በሰይጣን ማታለያ በመሸነፍ ልክ እንደ መጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት መጥፎ ምርጫ አድርጓል።—ራእይ 12:9⁠ን አንብብ።

የሰው ልጆችን ችግር መፍታት የሚችለው ማን ነው?

ክፉ የሆነው የሰይጣን አገዛዝ እንዲቀጥል አምላክ ይፈቅዳል? በፍጹም! አምላክ በኢየሱስ አማካኝነት ሰይጣን የፈጸማቸውን ክፉ ነገሮች ሁሉ ያስወግዳል።—1 ዮሐንስ 3:8⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ ከአምላክ ባገኘው ሥልጣን ተጠቅሞ ሰይጣንን ይደመስሰዋል። (ሮም 16:20) ከዚያም አምላክ የሰውን ዘር መግዛት ይጀምራል፤ እንዲሁም መጀመሪያ አስቦት የነበረውን ደስታና ሰላም የሰፈነበት ሕይወት ለሰው ልጆች ይሰጣቸዋል።—ራእይ 21:3-5⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 3 ተመልከት

www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ